የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ በለይቶ ማቆያ የሚገኙ ዜጎችን አያያዝ መጎብኘት ጀመሩን አስታወቀ

0
704

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ በለይቶ ማቆያ የሚገኙ ዜጎችን አያያዝ እና እንክብካቤ ላይ ቁጥጥር ለማድረግ ጉብኝት መጀመሩን የገለፀ ሲሆን ቦርድ በለይቶ ማቆያ የሚገኙ ዜጎችን በዛሬው እለት መጎብኘት የጀመረ መሆኑን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

በዚህም ጉብኝት መንግስት ለዜጎች የሰጠው ትኩረት እና ዜጎች ያሉበት አጠቃላይ ሁኔታ እንዲሁም ከሰብዓዊ መብት አንጻር እየተከናወኑ ያሉት ስራዎች ላይ ግምገማና
ክትትል እንደሚደረግ የሚጠበቅ ሲሆን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈጻጸም ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ለመቆጣጠርም ቦርዱ ክትትል እያደረገ
መሆኑንም ጠቅስዋል።

በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመቆጣጠር መንግስት ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም የሚከታተል መርማሪ ቦርድ መቋቋሙ ይታወቃል።

በዚህም መሰረት ቦርዱ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈጻጸም ወቅት የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ተከታትሎ በህግ ፊት ማቅረብ እንዲሁም በዚህ ምክንያት ወደ ማረሚያ የሚገቡ ካሉም ከታሰሩበት ተገቢነት አንጻር በመመልከት የምርመራ ውጤቱን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የማቅረብ ሃላፊነት አለበት እናዳለበትም መግለጫ ላይ ተጠቁሟል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here