ኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ለሰራተኞቹ አንቡላንስ ማዘጋጀቱን አስታወቁ

0
367

በኢትዮጵያ የተከሰተውን የኮቪድ-19 ወረርሺኝ ተከትሎ የኢመደኤ አባላት የቫይረሱ ምልክት ከታየባቸው ወደ ጤና ተቋማት ማድረስ የሚያስችል አንቡላንስ ማዘጋጀቱን በኢመደኤ የጤና ዴስክ አስተባባሪ እስራኤል አለማየሁ ገልጸዋል፡፡
አስራኤል እንዳሉት ተቋሙ የራሱን አንቡላንስ ወደሥራ ማስገባቱ በጤና ተቋማት ያለውን የአንቡላንስ እጥረት ከመቅረፍ አኳያ የሚጫወተው ሚና የጎላ ነው ብለዋል፡፡
አጀንሲው ካሉት መኪናዎች ውስጥ አንድ ላንድክሩዘር መኪና አንቡላንስ የሚያስፈልገውን ግብዓቶች አሟልቶ እንዲዘጋጅ በማድረግ ለአገልግሎት እንዲውል ማድረጉን አስተባባሪው ተናግረዋል፡፡
አምቡላንሱ ኦክሲጅን፣ ደረጃውን የጠበቀ ስትሬቸር፣ ሳይረን፣ የድንገተኛ አደጋ ህክምና መስጫ ግብአቶችን /Emergency Medication/ ያሟላ እና የመጀመሪያ እርዳታ መስጠት የሚችሉ ባለሙያዎችን የያዘ መሆኑንም አስተባባሪው ጨምረው ገልጸዋል፡፡
በሌላ በኩል አንቡላንሱ ለኮቪድ-19 በሽታ ተጠርጣሪ ለሚሆኑ የኤጀንሲው አባላት ከሚሰጠው አገልግሎት በተጨማሪ ለነፍሰጡር እናቶች እና አደጋ ለሚያጋጥማቸው የተቋሙ አባላትን ወደ ጤና ተቋም የማድረስ አገልግሎት ለ24 ሰዓት እንደሚሰጥም ታውቋል፡፡
ኢመደኤ የኮሮና ቫይረስ ወደ አገራችን ከገባ ጊዜ ጀምሮ የአባላቱን ደህንነት ለመጠበቅ እና እንደሀገር እየተወሰዱ ያሉ የመከላከል ሥራዎችን ለማገዝ የተለያዩ ሥራዎችን ሲሠራ ቆይቷል።
ኤጀንሲው የቅደመ ጥንቃቄና መከላከል እርምጃዎችን ሲወስድ የቆየ ሲሆን ይህ የአንቡላንስ አገልግሎትም አንዱ የመከላለከል እርምጃ አካል ተደርጎ የሚወሰድ ነው፡፡

ቅጽ 2 ቁጥር 77 ሚያዝያ 17 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here