አለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም “IMF” በኮሮናቫይረስ ምክንያት ኢትዮጵያ የሚደርስባትን የኢኮኖሚ ጫና ለመቋቋም እንዲያስችላት የ411 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገ

0
904

አለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም “IMF” ሐሙስ ሚያዝያ 22/2012 በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ለሚከሰት የአደጋ ስጋትን ለመከላከል የሚያስችል የ411 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለኢትዮጵያ መፍቀዱን አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም ተቋሙ እንዳስታወቀው ኢትዮጵያ በጥቅምት ወር 2012 ጠይቃው የነበረውን የ12 ሚሊዮን ዶላር  የእዳ ክፍያ ማራዘም ጥያቄን በመቀበል እስከ ሰኔ ወር 2014 ድረስ እንደሚራዘም መፍቀዱንም ገልፅዋል፡፡

የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በኢትዮጵያ እያስከተለ ያለው የጤና ስጋት እንዲሁም በምጣኔ ሀብቷ ላይ የሚያደርሰው ጫናን ከፍተ ነው፡፡ ይህ ወረርሽን በጊዜው ካልተገታ በጤና እና በማህበራዊ ግንኙነት ላይ የሚያደርሰው ውድመትን ቀላል እንደማይሆንም ተቋሙ አሳስቧል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here