በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 25 ተጨማሪ ሰዎች ኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው

0
752

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ 1843 የላብራቶሪ ምርመራ ሃያ አምስት (25) ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በአጠቃላይ በሀገሪቱ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ ሰማንያ ሰባት (187) መድረሱን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ሁሉም ኢትዮጵውያን ሲሆኑ ሃያ አራቱ ወንዶች አንዷ ሴት መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን እድሜያቸውም ከ17 እስከ 65 ዓመት ነው፡፡

አዳዲሶቹ ታማሚዎችም 3ቱ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው፣ 3ቱ  በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው እንዲሁም 19ኙ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክም ሆነ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው መሆናቸውን የጤና ሚኒስቴር ጨምሮ አስታውቋል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here