በትግራይ ክልል በአራት ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ተገለፀ።

0
1009

በትግራይ ክልል በተደረገ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ በ4 ሰዎች ላይ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የትግራይ መገናኛ ብዙሀን ኤጀንሲ ዘግቧል፡፡

በክልሉ ከዚህ ቀደም በቫይረሱ ተይዘው ሪፖርት የተደረገ ቁጥር እንዳልነበር የሚታወስ ሲሆን የክልሉ ጤና ቢሮ እንዳስታወቀው ከተደረጉት 608 ምርምራዎች ውስጥ 4 ሰዎች ላይ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው እና በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ እንደነበሩም ለማወቅ ተችሏል።

ይህም መረጃ የጤና ሚኒስትር ዛሬ በ24 ሰአት ውስጥ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል ካላቸው 25 ሰዎች ውጪ መሆኑም ታውቋል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here