በግንቦት ወር ከ21 ሺሕ በላይ ዜጎች የጎርፍ አደጋ ሊደርስባቸው እንደሚችል ተገለፀ

0
709

በመጪው ግንቦት ወር 21 ሺሕ በላይ ዜጎች የጎርፍ አደጋ ሊደርስባቸው እንደሚችል የብሔራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ገለፀ።
የጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት ስጋት ባለባቸው አካባቢዎች ያሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች ንቁ ሆነው መጠበቅ እንዳለባቸው ኮሚሽኑ አሳስቧል። የብሔራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ይከሰታል ተብሎ በሚታሰበው የጎርፍ አደጋ ቅድመ ማስጠንቀቂያና መከላከል ዙርያ መግለጫ ሰጥቷል።
የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ዳመና ዳሮታ እንዳሉት፣ በሚያዚያ ወር 2012 በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የጎርፍ አደጋ እና የመሬት መንሸራተት መከሰቱንም ተናግረዋል። በድሬዳዋ ከተማ በደረሰ የጎርፍ አደጋ 4 ሰዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ፣ 53 ቤቶች ሙሉ በሙሉ ፈርሰዋል። ኹለት ሺሕ የሚጠጉ ቤተሰቦች ለምግብ እጥረት ተጋልጠዋል ብለዋል።
በተመሳሳይ በደቡብ ኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል እንዲሁም በሶማሌ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በደረሰ የጎርፍ አደጋ እና የመሬት መንሸራተት፣ 219 ሺሕ 698 ሰዎች መጎዳታቸውን ጠቅሰዋል። ከ108 ሺሕ በላይ ሰዎችም መፈናቀላቸውን ዳመና ተናግረዋል። ኮሚሽኑ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ሜትዮሮሎጂ ኤጀንሲ ባገኘው መረጃ መሠረት፣ አደጋው የሚቀጥል መሆኑን ገልፀዋል።
ከዛም በተጨማሪ በግንቦት ወር ብቻ ከ 21 ሺሕ በላይ ሰዎች ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ ስጋት መኖሩን ምክትል ኮሚሽነሩ አሳስበዋል።

ቅጽ 2 ቁጥር 79 ግንቦት 1 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here