ባለፉት 24 ሰአታት ውስጥ ተጨማሪ 2 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

0
940

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገ የ2650 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ 2 ተጨማሪ ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ተገለፀ፡፡

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ እንዳስታወቁት ቫይረሱ እንደተገኘባቸው በምርመራ የተረጋገጠው ሁለቱ ሰዎች ወንድ ኢትዮጵያዊያን፣ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸውና እድሜያቸውም 24 እና 33 ሲሆን አንዱ ከትግራይ ክልል የድንበር ተሸጋሪ አሽከርካሪ እና መቐለ ለይቶ ማቆያ የነበረ፣ አንዱ ደግሞ ከሶማሌ ክልል ጂግጅጋ ለይቶ ማቆያ የነበረ መሆናቸውንም ጨምረው ተናግረዋል።

በተጨማሪም በትላንት እለት ተጨማሪ ሁለት ሰው ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 108 መድረሱም ታውቋል።

በአጠቃላይ እስካሁንም 41 ሺህ698 የላቦራቶሪ ምርመራ መከናወኑንም ከሚኒስትሯ መግለጫ ለማወቅ ተችሏል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here