በ24 ሰአት ውስጥ ተጨማሪ 24 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የጤና ሚኒስትር አስታወቀ

0
724

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰአታት ውስጥ በተደረገ 3460 የላብራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 24 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት  በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች 18 ወንድ እና 6 ሴት ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ ከ4 እስከ 57 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

ከእነዚህም 24 ሰዎች ውስጥ 9ኙ ሰዎች ከአዲስ አበባ ሲሆኑ 5ቱ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው 4ቱ ደግሞ ምንም አይነት የውጪ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያልነበራቸው መሆኑ ታውቋል፡፡

በተጨማሪም 7ቱ ሰዎች ትግራይ ክልል ሲሆኑ 4ቱ የውጪ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው ሲሆኑ ከእነሱም ውስጥ 1 ሰው በመቐለ ለይቶ ማቆያ ያሉ 6ቱ ደግሞ ማይካድራ ለይቶ ማቆያ ያሉ ናቸው፡፡

ቀሪዎቹ 8 ሰዎች ከአማራ ክልል ሲሆኑ የውጪ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው እና መተማ ለይቶ ማቆያ የሚገኙ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ይህም በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙትን ሰዎች ቁጥር 389 ያደረሰው ሲሆን በትናንትናው እለት 2 ሰዎች ከአማራ ክልል ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 122 መድረሱም ዶክተር ሊያ መግለጫ ለማወቅ ተችሏል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here