ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኮቪድ-19 ወቅት፣ የፈጠራ ሥራን ለመሥራት የቀረበውን ጥሪ ተቀብለው ብዙዎች ጠቃሚ ሐሳቦችን እያፈለቁ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጃክ ማ ተፅዕኖ አሳዳሪ የፈጠራ ሥራ ባለቤቶችን ለመደገፍ የአፍሪካን የቢዝነስ ጀግኖች የተሰኘ የድጋፍ ማዕቀፍ ማዘጋጀታቸውን እንደተናገሩ ገልጸዋል።
ስለሆነም በፈጠራ ሥራ የተሠማሩ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ( www.africabusinessheroes.org/en/ ) ላይ በመግባትና የድረ ገጹን መረጃ አንብበው በማመልከት፣ በቀጣና ደረጃ የውድድሩ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስ ቡክ ገጻቸው ጥሪ አቅርበዋል።



