የዓለም ባንክ የአንበጣ መንጋን ለመከላከል 500 ሚሊዮን ዶላር መመደቡን አስታወቀ

0
594

የዓለም ባንክ ግንቦት 13/2012 እንዳስታወቀው በአፍሪካ እና መካከለኛው ምሥራቅ ሰብሎችን እያወደመ ያለውን የበረሃ አንበጣ ለመዋጋት ለአገራቱ በእርዳታ እና ዝቅተኛ የወለድ መጠን ብድር የሚውል 500 ሚሊዮን ዶላር መድቧል።
የዓለም ባንክ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሆኑት ሆልገር ክሬይ፤ በአንበጣ መንጋው ክፉኛ የተጎዱ አራት አገራት ማለትም ጅቡቲ፣ ኢትዮጵያ፣ ኬኒያ እና ኡጋንዳ 160 ሚሊዮን ዶላር በአስቸኳይ ይደርሳቸዋል ሲሉ ለሮይተርስ ተናግረዋል።
የመን ሶማሊያና ሌሎች የተጎዱ አገራት ደግሞ እንደ አስፈላጊነቱ ገንዘቡ ይለቀቅላቸዋል መባሉም ተገልጿል።
የአፍሪካ ቀንድ ታይቶ በማይታወቅ አንበጣ ወረራ ላይ ይገኛል ያሉት ክሬይ፣ አዲሱ የኮቪድ 19 ኮሮና ቫይረስ ቀውስ ደግሞ ችግሩን እንደሚያባብሰው ነው የተናገሩት።
የዓለም ባንክ እንደሚለው አሁን የተከሰተው የአንበጣ መንጋ 23 የምሥራቅ አፍሪካ፣ መካከለኛው ምሥራቅና ደቡብ እስያ አገራትን አጥቅቷል። ይህም በ70 ዓመታት ውስጥ ከፍተኛው ወረርሽኝ ነው። በዚህም ሳቢያ በምሥራቅ አፍሪካ ወደ 23 ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ ለምግብ እጥረት ተጋልጧል።
የበረሃ አንበጣ በቀን እስከ 250 ኪሎ ሜትር ሊጓዝ ይችላል።

ቅጽ 2 ቁጥር 81 ግንቦት 15 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here