ባለፉት 24 ሰአታት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 85 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተገለፀ፤ ተጨማሪ 1 ሰውም በቫይረሱ ምክንያት ህይወቱ አልፏል

0
948

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰአታት ውስጥ በተደረገ 2,926 የላብራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 85 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ መገኘቱን እንዲሁም የአንድ የ30 አመት ኢትዮጵያዊ ህይወት ማለፉን የጤና ሚኒስቴር ሚኒስቴሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል፡፡

ይህም በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙትን ሰዎች ቁጥር 1,252 ያደረሰው ሲሆን በቫይረሱ ሳቢያ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥርም 12 ደርሷል፡፡

ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች 51 ወንድ እና 34 ሴት ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ ከ1 ወር እስከ 65 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙም መሆናቸው ታውቋል፡፡

ከእነሱም ውስጥ 72 ሰዎች ከ አዲስ አበባ፣
4 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣
5 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣
1 ሰው ከ አማራ ክልል እንዲሁም 3 ሰዎች ከሶማሊያ ክልል መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በትናንትናው እለት 8 ሰዎች (3 ከኦሮሚያ ክልል እንዲሁም 5 ከአዲስ አበባ) ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን ይህም በአጠቃላይ በሀገራችን ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥርን 217 አድርሶታል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here