ከ 460 ሚሊዮን በላይ መዝገቦች በግንቦት ወር ብቻ መሹለካቸዉ ተገለጸ

0
697
በግንቦት ወር ሪፖርት በተደረጉት የሳይበር ጥቃቶች 460 ሚሊዮን መዝገቦች ሾልከዉ መገኘታቸዉን አይቲ ገቨርናንስ /IT Governance/ ይፋ ማደረጉ ተገለፀ፡፡
 
ይህ ቁጥር በይፋ ሪፖርት ከተደረጉ ክስተቶች ብቻ የተገኘ መረጃ በመሆኑና ቁጥሩ ከዚህ እጅግ ከፍ እንደሚል ተነግሯል፡፡
 
የሳይበር አደጋ እና የግላዊ መረጃ አያያዝ መፍትሔዎች አቅራቢ የሆነው የአይቲ ገቨርናንስ በዓለም ዙሪያ ካሉ የተለያዩ አገልግሎቶች መካከል ተፅእኖ የሚያሳድሩ እና በይፋ የወጡ የሳይበር ክስተቶች በመነሳት ሪፖርቱን እንዳጠናቀረ ጠቁሟል፡፡
 
በፈረንጆቹ 2020 ብቻ 400 የሚሆኑ የጥቃት ሪፖርቶች መውጣታቸዉን የገለጸዉ ተቋሙ ሪፖርት ከሾለኩ መዝገቦች ውስጥ ሁሉም ሚስጥራዊ ወይም ግላዊ የሆኑ መረጃዎችን የያዙ አለመሆናቸዉን አስታዉቋል፡፡
 
ከተከሰቱት ተጋላጭነቶች ውስጥ 39 የሚሆኑት የሳይበር ጥቃቶች ፣ 37 የዳታ ጥሰቶች ፣ 17 የራንሰምዌር ጥቃቶች እንዲሁም ስድስት የሚሆኑት በዉስጥ አዋቂዎች የተፈጸሙ ወይም ሌሎች የሳይበር ጥቃት ዓይነቶችን በሚል አስቀምጧቸዋል፡፡
 
የሾለኩት መዝገቦች ለመረጃ መንታፊዎች እዚህ ግባ የሚባል አገልግሎት ባይሰጡም እየጨመረ ስለመጣዉ የሳይበር ጥቃት ከፍተኛ ትኩረት እንድንሰጥ እና አስፈላጊዉን ጥንቃቄ እንድናደርግ ማንቂያ ተደርጎ ተወስዷል፡፡
 
ተቋሙ በሚያቀርበዉ ወርሃዊ ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት በመጋቢት ወር 67 የሳይበር ጥቃት ክስተቶች አማካኝነት 832 ሚሊዮን መዝገቦች የሾለኩ ሲሆን ከዚያ በፊት በየካቲት ወር በ 6 ክስተቶች አማካኝነት 623.5 ሚሊዮን መዝገቦች ለጥቃት መጋለጣቸዉን ታዉቋል፡፡
 
አሳሳቢዉ ጉዳይ በብዙ አጋጣሚዎች ተጠቂዎቹ ስለተፈጸመባቸዉ የመረጃ ጥቃት ከብዙ ጊዜያት በኋላ የሚያዉቁ ሲሆን አንዳንዴ ስለተፈጠረዉ ክስተት ጭራሽ እንደማያዉቁ ነዉ የተነገረዉ፡፡
 
ሌሎች ደግሞ የገንዘብ ቅጣቶችን በመፍራት እና ደንበኞቻቸውን አመኔታ ላለማጣት የሳይበር ጥቃት ክስተቶችን ሪፖርት አያደርጉም መባሉን ከኢትዮጵያ መረጃ ደህንነት ኤጄንሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here