ኢትዮጵያ በሶስት ወራት ውስጥ ከ 14,800 በላይ ከስደት ተመላሾችን ተቀብላለች

0
1048

ኢትዮጵያ ከመጋቢት ወር ጀምሮ እስከ ሰኔ ባለው ጊዜ ውስጥ ከ 14,800 በላይ ኢትዮጵያዊያን ከስደት ተመላሾችን መቀበሏን አለም አቀፍ የፍልሰተኞች ድርጅት አስታውቋል፡፡

ድርጅቱ ባወጣው መረጃ መሰረት ከስደት ተመላሽ ኢትዮጵያዊያዊያኖቹ 3,700 ከጅቡቲ ፣ 3000 ያህል የሚሆኑ ከሳውዲ አረቢያ ፣ 2,350 ከሶማሊያ፣ 640 ከሊባኖስ እንዲሁም 560 ከኬንያ ሲሆኑ በተጨማሪም ባለፈው ሳምንት አለም አቀፍ የፍልሰተኞች ድርጅት አይ.ኦ.ም ፣ የተባበሩት መንግስታት የህፃናት መርጃ ድርጅት ዩኒ.ሴ.ፍ እና የቀይ መስቀል ቡድን 647 የሊባኖስ እና 270 የሳውዲ አረቢያ ተመላሾችን አዲስ አበባ አየር ማረፊያ ውስጥ በመቀበል ረገድ ድጋፍ ማድረጋቸውም ታውቋል፡፡

አይ.ኦ.ኤም እንደገለፀው ከሆን ባሳለፈነው ሳምንታት ውስጥ 2,408 ስደተኞች ወደለይቶ ማቆያ ተቋማት የገቡ ሲሆን ከእነሱም ውስጥ 647 ከሊባኖስ ተመላሾች(646 ሴት እና 1 ወንድ) በአዲስ አበባ ለይቶ ማቆያ ውስጥ እንዲገቡ ተደርገዋል፡፡ ሌሎች ተመላሾች ደግሞ  144 ተመላሾች በሰመራ ፣ 682 (449 ወንድ ፣ 233 ሴት) በጅግጅጋ ፣ 82 (59 ወንድ ፣ 23 ሴት) በሞያሌ እንዲሁም 583 (553 ወንድ ፣ 30 ሴት) ከስደት ተመላሾች በመተማ ለይቶ ማቆያዎች ውስጥ እንደሚገኙም ድርጅቱ አስታውቋል፡፡

እንዲሁም  ከ 6,600 ለሚበልጡ በየለይቶ ማቆያዎቹ ለሚገኙ  ስደተኞች ቀጥተኛ ድጋፍ እየተደረገ ሲሆን ድጋፉም ወደ አገር ውስጥ ከማስገባት ጀምሮ እስከ ለይቶ ማቆያ ተቋማቱ ድረስ የመጓጓዣ አገልግሎት፣ ምዝገባ፣ ምግብ-ነክ ያልሆኑ ዕቃዎች፣ ምግብ፣ ቫይረሱን ከመከላከል የሚያግዙ ግል ግብዓቶችን፣ የድጎማ አበል ተጨማሪ መጓጓዣ ወጪዎች ድጋፍ፣ ቤተሰብን የማፈላለግ እና መልሶ የማገናኘት ስራ እንዲሁም የአእምሮ ጤና እና የስነ-ልቦና ድጋፍ ከሚያዚያ ወር መጀመሪያ ጀምሮ በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡

በተጨማሪም በአዲስ አበባ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ኹለት የላቦራቶሪ ሰራተኛዎችን በማሰማራት የ COVID-19 ላቦራቶሪ ምርመራዎችን በመደገፍ በተጨማሪም የቡሌ ሆራ ዞን ጤና በከተማዋ መግቢያ እና መውጫ ላይ ለሚከናወን የኮቪድ 19 ምርመራ ኹለት የመለያ ማዕከል ለማቋቋም  ድጋፍ ተደርጓል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በአዲስ አበባ በለይቶ ማቆያ ድገፍ እና እንክብካቤ ላይ  የሰለጠኑ 34 የፊት መስመር ሰራተኞች ተሰማርተው ለስደተኞቹ የአዕምሮ ጤና እና የሥነ ልቦና ድጋፍ በመስጠት ላይ የሚገኙ ሲሆን በተጨማሪም በሞያሌ ሌቶ ማቆያም ተመሳሳይ ድጋፍ እና እንክብካቤ በመሰጠት ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here