“በአፍሪካ ለልጆች ተስማሚ የፍትሕ ሥርዓትን ተደራሽ ማድረግ” በሚል መሪ ቃል የዘንድሮው የአፍሪካ ሕፃናት ቀን ታስቦ ይውላል

0
443

በየዓመቱ ሰኔ 9 ቀን የሚከበረው የአፍሪካ ሕፃናት ቀን በዚህ ዓመት “በአፍሪካ ለሕፃናት ተስማሚ የፍትሕ ሥርዓትን ተደራሽ ማድረግ” በሚል መሪ ቃል ታስቦ እንደሚውል የአፍሪካ ኅብረት አስታውቋል።

የአፍሪካ ኅብረት የሕፃናት ቀን አስተባባሪ ኮሚቴ እና የኅብረቱ አባል ሀገራት ለሕፃናት ተስማሚ የሆነ የፍትሕ ሥርዓትን ለመፍጠር የሚያስችሉ መሠረታዊ ግብዓቶችን በተመለከተ ለባለድርሻ አካላት መድረክ በማዘጋጀት ቀኑን አስበው እንደሚውሉም ተገልጿል።

የአፍሪካ የባለሙያዎች ኮሚቴ በሕፃናት መብት እና ደህንነት ጉዳዮች ላይ በፌስቡክ ቀጥታ የሚተላለፍ ዌቢናር (በኢንተርኔት የሚደረግ የቪዲዮ ሴሚናር) እንደሚያካድም ለማወቅ ተችሏል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here