ማራቶን ሞተር በኮቪድ-19 ምክንያት 200 ሚሊዮን ብር ማጣቱን ገለጸ

0
1026

የኮቪድ-19 በኢትዮጵያ መከሰትን ተከትሎ በኢትዮጵያ የሃዩንዳይ ተሸርካሪዎች አስመጪ እና መገጣጠሚያ ኩባንያው ማራቶን ሞተርስ 200 ሚሊዮን ብር ማጣቱን አስታወቀ።

የማራቶን ሞተርስ ባለቤት የሆኑት አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት ከትንሽ እስከ ትልቅ የሚባሉ የንግድ ተቋማት ገቢያቸው እያሽቆለቆለ እንደሚገኝ እና ማራቶን ሞተር ኢንጅነሪንግም ኮቪድ በኢትዮጵያ ከተገኘበት የመጀመሪያዎቹ ቀናት ጀምሮ አስካሁን 200 ሚሊዮን ብር ገቢ ማጣቱን አስታውቋል፡፡
የማራቶን ሞተር ኢንጅነሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ስራ አስኪጅ አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ የኮቪድ-19 በኢትዮጵያ መከሰት በንግዱ አለም የተሰማሩ ድርጅቶችን በምጣኔ ሀብት ረገድ በከፍተኛ ደረጃ እንደጎዳው ተናግረዋል፡፡ የኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ ከተከሰተ ወዲህ የንግድ ሥራዎች ከትርፍ ወደ ኪሳራ መግባታቸውን ኃይሌ ጠቁመዋል፡፡

ከማራቶን ሞተርስ በተጨማሪ በሆቴል አገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩት ኃይሌ ካሏቸው ስድስት ሆቴሎች በኪቪድ-19 መከሰት ምክንያት ሥራ ፈተው እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡ ነገር ግን በሆቴሎቹ ስር ለሚተዳደሩ 3 ሺህ ሰራተኞች ሥራ ቢፈቱም ደምወዝ እየተከፈላቸው እንደሚገኝም ኃይሌ ለአዲስ ማለዳ አስታቀዋል። በዚህም ለ3 ሺህ ሰራተኞች በየወሩ 6 ሚሊዮን ብር ደምወዝ እንደሚከፍል ኃይሌ ጠቁመው፤ በዚህም ገቢ በመቀነሱ የብድር መጠኑ እየጨመረ መሔዱንም አያይዘው ተናግረዋል፡፡
የኮቪድ-19 መከሰትን በኹለት መንገድ እንደሚረዳው እና ጉዳት እንዳለው ሁሉ በሌላ በኩል ሌላ መልካም እድል እንደሚኖረው ዕምነት እንደላቸውም ያስታውቃሉ፡፡ በወረርሽኙ ኢትዮጵያ በከፍተኛ ሁኔታ የተጎዳችው በሆቴልና ቱሪዝም ኢንድስተሪ መሆኑን እንደሚምን ኃይሌ ገልጿል፡፡

ይህ የሆነበት ምክንያት ደግሞ የኢትዮጵያ ቱሪስት ደንበኞች በብዛት የመመጡት ከጣሊያን፣ ከፈረንሳይ፣ ከሆላንደ፣ ከጀርመን፣ ከአመሪካ እና ከኢስያ አገራት በመሆኑ እና እነዚህ አገራት በኮቪድ-19 ወረርሽኝ በከፈተኛ ሁኔታ በመጎዳቸው መሆኑን ኃይሌ አመላክቷል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት የቱሪዝም ፖሊሲ እና ስትራቴጂ ትኩረቱን ያደረገው የኢትዪጵያን ቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎችን በአለም ዓቀፍ ቱሪስቶችቤ የገቢ ምንጭ ማድረግ እንደሆነ የሚገልው ኃይሌ ይህ አይነት ሰትራቴጂ አዋጭ አንዳልሆነና ትክክል አለመሆኑ ይጠቁማል፡፡

የሀገሪቱን ቱሪዝም ለማሳደግ በቱሪስት መዳረሸ ቦታች ላይ መሰረተ ልማት ስራዎችን መስራት፣ የሆቴሎችን ብዛትና ጥራት ማሳደግ እና በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ሀይል አለመኖሩ ዋነኛ የዘርፉ ችግር መሆኑን ገልጾ፣ እነዚህን ችግሮች መክረፍ እንደሚገባ ጠቁሟል፡፡

ኃይሌ በኮቪድ-19 ወረርሽን መከሰት ድርጅቶቹ ገቢያቸው ስለቀነሰ፣ መንግስት ብድር እንዳራዝምለት እና ወለድ እንድሰረዝለት ለመጠየቅ ማሰቡነም ጠቁሟል፡፡ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በዚህ ከቀጠለና ስርጭቱ ካልተገታ እና መንግስት ጣልቃ ካልገባ ኃይሌ ከሶስት ወር ብኋላ ለሰራተኛ ደምወዝ መክፈል እንደማይችል ጠቁሟል፡፡
የኢትዮጵያ መንገስት ሌሎች ሀገሮች ኬኒያ፣ ሩዋነዳ እናኡጋንዳ ያሉ ምን አደረጉ የሚለውን ማየት ኃይሌ እንዳለበት አመለካክቷል፡፡ መንግስት ግብር መዝለል እነዳለበትና ይህም የተሻለ መፍትሔ መሆኑን ኃይሌ ተናግሯል፡፡

ማራቶን ሞተር ኢንጅነሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በ2000 የተመሰረተ ሲሆን፣ ማራቶን በይፋ ሥራ ጀምሮ የተለያዩ ተሸከርካሪዎችንና የተሸከርካሪ መለዋወጫ እቃዎችን ወደ ኢትዮጵያ ማስገባት የጀመረው በ2001 ነበር፡፡ ይህም በዘርፉ ከፍተኛ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ከሚንቀሳቀሱ የአገር ውስጥ ኩባንያዎች ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል።

ማራቶን ሞተርስ ከደቡብ ኮሪያው የተሸከርካሪ አምራች ኩባንያ ሀዩንዳይ ጋር ቀድሞ በገባው ውል መሰረት መኪኖችን የመገጣጠም ስራም በመጀመር በከፍተኛ ወጪ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ተሸከርካሪዎችን በአገር ውስጥ ለመገጣጠም እንደሚሰራም የሚታወቅ ነው።

ቅጽ 2 ቁጥር 85 ሠኔ 13 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here