በኮቪድ ምክንያት ከማረሚያ ቤት እንዲለቀቁ ተወስኖላቸው እስካሁን በማረሚያ ቤት የሚገኙ እንዳሉ ታወቀ

0
327

የኮሮና ቫይረስ ወደ ኢትዮጲያ መግባቱን ተከትሎ አንድ ዓመት እና ከዛ በታች የማረሚያ ቤት የቆይታ ጊዜ የቀራቸው እንደሚለቀቁ ከምግስት ወገን ቢነገርም ስም ዝርዝራቸው ተላልፎ እስካሁን ያልተፈቱ ግለሰቦች መኖራቸው ታወቀ፡፡

የታራሚ ቤተሰቦች ለአዲስ ማለዳ እንዳስተወቁት በመንግስት ውሳኔ መሰረት ሁሉም መለቀቅ እየነበረባቸው ሳይለቀቁ የቀሩ እንዳሉ እና ለዚህም ምክንያት ደግሞ ምንድን እንደሆነ በሚጠይቁበትም ወቅት ይቅርታ ቦርድ አላየውም መለቀቅ የሚችሉት ደግሞ ይቅርታ ቦርድ ተቀብሎት ሲፈርምበት ብቻ ነው የሚል ምላሽ ከማረሚያ ቤት እንዳገኙ ለማወቅ ተችሏል። አሁን ደግሞ ይሄን ለማድረግ የይቅርታ ቦርድ አባላቶች መሰብሰብ አለመቻላቸው እንዳይለቀቁ አድርጓቸዋል፤ በማለት ተደጋጋሚ ምላሽ ከማረሚያ ቤቱ እየተሰጣቸው እንደሆነ የታራሚዎቹ ቤተሰቦች ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል፡፡

በመጀመሪያዎቹ የኮቪድ 19 የኢትዮጵያ የገባበት ወቅት ለታራሚዎቹ ተወስኖ የሚለቀቁት ታራሚዎች ስም ዝርዝር የወጣው ከሶስት ወር በፊት እንደሆነ የሚገልጹት ቤተሰቦች ነገር ግን ይለቀቁ ከተባሉት እና ስማቸው ከተላለፉ ሰዎች ውስጥ 17 የሚሆኑት እንዳልተለቀቁ ተናግረዋል፡፡

የታራሚ ቤተሰቦች ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት የታራሚዎችን መለቀቅ ለማወቅ የቻልነው የሚሉት ዕንዲለቀቁ ተብሎ ስም ዝርዝራቸው የቃሊቲ ማረሚያ ቤት በር ላይ ተዘጋጁ ተብሎ 50 ለሚሆኑ ታራሚዎች ተለጥፎ ነበር በዛ ምክንያት ነው ብለዋል፡፡

የታራሚዎቹ ቤተሰቦች እንደሚሉት አሁን ከዚህ ቀደም ከነበረው የበለጠ ስጋት ላይ ነን ፤ ምክንያቱም አሁን ባለው ኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ መስፋፋት ምክንያት የማንም ቤተሰብ ከማንም ጋር መገናኘት ባለመቻሉ ምክንያት ያሉበት ሁኔታ ለማወቅ ተቸግረናል ብለዋል፡፡

ቤተሰቦቹ እንደሚሉት አሁን ላይ ይለቀቁ ከተባሉት ውስጥ ከ 4ወር አስከ 1 አመት የሚቀራቸው ያሉበት ሲሆን ከማረሚያ ቤቱ የሚሰጠው ሃሳብ ለይቅርታ ቦረዱ ስም ዝርዝራቸውን ማረሚያ ቤቱ እንዳስተላለፈ እና እነርሱ ሲመቻቸው ነው የሚያዩት ስለዚ እነርሱ አይተው ምላሽ እስከሚሰጡን የግድ መጠበቅ አለብን እንደሚሏቸው ተናግረዋል፡፡

እኛ በተደጋጋሚ ብንጠይቅም አጥጋቢ ምለሽ ባለማግኘታችን ምክንያት ወደ ይቅርታ ቦርድ በመሄድ ለምን ብለን እንዳንጠይቅ ወደ ውስጥ መግብት አይቻልም በማለት እንደሚመልሷቸው ተናግረዋል፡፡

ይንም አይነት ጥያቄ ቢኖራችሁ በ ኢሜል ነው ማቅረብ የምትችሉት በማለት መልስ እንደሰጧቸው ነገር ግን እንደዚያም ቢያደርጉ ከተገቢው አካል ተገቢ ምላሽ ማግኘት እንዳልቻሉ እና ጭንቀት ውስጥ መሆናቸውን ለአዲስ ማለዳ የታራሚዎቹ ቤተሰቦች ተናግረተዋል፡፡

ከታራሚ ቤተሰቦች ቀረበውን ጥቆማ እና ቅሬታ በሚመለከት ያነጋገርናቸው የጠቅላይ አቃቤ ህግ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ዝናቡ ቱሉ ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት ከሆነ ከኮሮና ቫይረስ ጋር እንዲለቀቁ ተብለው የተወሰነላቸው ታራሚዎች ሁሉም እንደተለቀቁ እና የቀረ እንደሌለ ተናግረዋል፡፡ የይቅርታ ቦርድ መፈረም ባለመቻሉ እና በዛ ምክንያት ነው ሊለቀቁ ያልቻሉት የሚለው ምክንያት ትክክል እይደለም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ዝናቡ እንደሚሉት ከሆነ ስም ዝርዝራቸው ወጥቶ ሳይለቀቁ ቀሩ ቢኖሩ እንኳን ሊሆን ሚችልበት ምክንያት ያላለቀ እና ያላስጨረሱት ነገር ኖሮ ሊሆን እንደሚችል እንደሚገምቱ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል፡፡

ከዘም በተጨማሪ ከሶስት አመት በታች ፍርደኛ የሆኑት ማናኛውም ሰው እንዲለቀቁ ተደርጓል፤ ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ግን እየገጠመን ያለው ችግር በአንድ ክስ ከ3 አመት በታች ተፈርዶባቸው በሌላ ክስ ደግሞ ገና ፍርድ ቤቱ ቆይቶ ፍርድ ሒደቱን እንዲከታተል ውሳኔ የተላለፈባቸው የትኛውም ታራሚ ያላለቀ የፍርድ ሒደት ከመኖሩ ጋር ተዳምሮ በማረሚያ ቤት እዲቆዩ የሚደረግበት አሰራር መኖሩን ተናግረዋል።

ቅጽ 2 ቁጥር 85 ሠኔ 13 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here