በአዲስ ትውልድ የመጣው ኢሕአፓ

0
1033

ኢሕአፓ በደርግ ዘመነ መንግሥት ብርቱ ‹ትግል› ያደርጉ ከነበሩ ፓርቲዎች መካከል ተጠቃሽና የማይረሳ ነው። ይህ ፓርቲ ታድያ ከኢሕአዴግ ወደ ሥልጣን መምጣት በኋላ የተበተነ ሲሆን፣ ባሳለፍነው ዓመት 2011 በስደት የቆዩት አባላቱ ተሰባስበው ዳግም ቀስቅሰውታል።

ከጅማ ዩኒቨርሲቲ በታሪክ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪውን የያዘው ቴዎድሮሰ ዘርፉ አሁን የኢሕአፓ ዋና ጸሐፊ ነው። የ30 ዓመት ወጣትም ነው። በሥም አንጋፋ የሆነውን ይህን ድርጅት በአመራርነት የተቀበለው በ2012 ታኅሳስ ወር ላይ ፓርቲው ባካሄደው ዘጠነኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንደነበር ያወሳል።

ፓርቲውን የተቀላቀለበትን ሁኔታ መለስ ብሎ ሲያስታውስ፣ የተለያዩ ምክንያቶች እንደነበሩት ይጠቅሳል። በተለይም ባደገበት ጎንደር አካባቢ የኢሕአፓ ጠንካራ ይዞታ የነበሩ ቦታዎች እንደነበሩ ያወሳል። ‹በተለይ ሪጅን ሦስት እና አራት በበለሳ እና አርማጨሆ የነበሩ ናቸው።› የሚለው ቴዎድሮስ፣ የተወለደበት አካባቢ በስፋት ታህት ኢዲዪ ይንቀሳቀሱበት የነበረበት ቦታ ስለነበር ስሞቹ በተደጋጋሚ ሲሰማ እንዳደገ አስታውሷል።

ኢሕአፓ መስከረም 12 ቀን 2011 በመርሻ ዮሴፍ እና ኢንጅነር ሰለሞን መሪነት ወደ አገር ቤት ሲገባ ታድያ ፓርቲውን ተቀላቅሏል። በእድገቱ እንዲሁም በሥራ አጋጣሚና በግል ዕይታውም የሶሻል ዴሞክራሲ አስተሳሰብ ደጋፊ በመሆኑ ወደ ድርጅት ለመሳብ እንደቻለ አንስቷል። የአዲስ ማለዳው ዳዊት አስታጥቄ የፓርቲውን ታሪክና ነባራዊ እውነቶች በሚመለከት ከፓርቲው ዋና ጸሐፊ ቴዎድሮስ ዘርፉ ጋር ተከታዩን ቆይታ አድርጓል።

ወደኋላ መለስ እንበል፤ የኢሕአፓ ዋና ጸሐፊ በመሆን መቼና አንዴት ነበር የተመረጥከው?
ኢሕአፓ ወደ አገረ ቤት ከተመለሰ በኋላ ለጠቅላላ ጉባኤ ዝግጅት ስናደርግ ነበር የቆየነው። በኋላም በታኅሳስ 4 እና 5 ጠቅላላ ጉባኤ በማድረግ የአመራሮችን ምርጫ በምስጢራዊ የድምፅ መስጠት ሂደት ተከናውኖ አዳዲስ አመራሮችን በተለይ ወጣት እና ሴቶችንም ጭምር ወደ ፊት ሲያመጣ የድርጅቱ ዋና ጸሐፊ ሆኜ ተመረጥኩኝ።

ከኔ ውጪ ብዙ ወጣት አመራሮችን ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ወደ ኃላፊነት አምጥተል። በዚህ ጉባኤ 70 በመቶ በላይ የሚሆኑት የአመራር ቦታዎች ለተተኪው ትውልድ የተላለፉበትም ጉባኤ ነበር።

ብዙ ሰው ኢሕአፓን በእድሜ ከገፉ ሰዎች ጋር የማገናኘት አዝማሚያ አለው። በፓርቲያችሁ በአመራር ሆነ በአባልነት የወጣቶች ተሳትፎ ምን ይመስላል?
የድርጅቱ መሪ ሴት ነች። በአመራር ደረጃ እንደ ኢሕአፓ በአመራር ደረጃ ለወጣቶች እና ለሴቶች ቦታ የሰጠ የለም። በእድሜ ቢሆን 20ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ የሆናቸው አባለትን ሁሉ የያዘ ነው።
እንደሚታወቀው ኢሕአፓ አንጋፋ ፓርቲ ነው። አንጋፋዎቹ፣ ቀደምት የድርጅትም አመራርና አባላትም ኃላፊነት ለአዲሱ ትውልድ በማስተላለፍ ነገር ግን ስንቶች የወደቁለትን ፓርቲ ከጎን በመደገፍ እየተሠራ ነው።

ኢሕአፓ ጭልጥ ካለ ከግራ ዘመን የፖለቲካዊ ርዕዬተ ዓለም አስተሳሰብ ወደ ሶሻል ዴሞክራሲ የተሸጋገረው መቼ ነው?
ኢሕአፓ መጀመሪያ ይከተል ከነበረው የማርክሲስታዊ አስተሳሰብ ማለትም ከጨቋኝ ተጨቋኝ እሳቤ የተለቀቀ የመጀመሪያው ፓርቲ ነው። ይህም በ1976 በቋራ ተካሂዶ በነበረው ስብሰባ ላይ ነበር። የፓርቲን ርዕዪተ ዓለም ወደ ሶሻል ዴሞክራሲ አስተሳሰብ እንዲቀየር የሆንውም በዚያ ጉባኤ ነበር።

ይህም ተራማጅ የነበረ ፓርቲ መሆኑን ያመላከተበት ነበር። በቋራው ጉባኤም በወቅቱ የነበረው የትግል ስልት አዋጭ አለመሆኑን ገምግሞ ነበር። የጨቋኝ ተጨቋኝ ትርክት ለአገር ግንባታም አዋጭ መሆንን ተነስቶ ነበር። ስለዚህ ለዚያም የሚሆነው መሀሉን የያዘውን የሶሻል ዴሞክራሲ አስተሳሰን ተቀብሎ ነበር።

በፌዴራሊዝም ዙሪያ የኢሕአፓ አቋም ምንድን ነው?
እንደ ኢሕአፓ ለዚህ አገር የሚስማማው መልክአ ምድራዊ አቀማመጥን እና የሕዝቦችን ማኅበራዊ ሥነ ልቦና መሰረት ያደረገ የፌዴራል አወቃቀር መሆን አለበት ብሎ ያምናል። ምክንያቱም ብሔር ተኮር የሆነው የፌዴራላዊ አወቃቀር ላለፉት 27 ዓመታት ተሞክሮ እንዳልሠራ በተግባር ተረጋግጧል።

የኢትዮጵያ በታኝ ኃይሎች ያቋቋሙት ነው ነው ብለን እናምናለን። ኢትዮጵያን ቅኝ ለመግዛት ሙከራ ያደረገችው ጣሊያን ኢትዮጵያን ለስድስት ለመክፈል አዘጋጅታ የነበረውን እቅድ ነው ዘጠኝ ክልል በማድረግ የሕወሓት የፌደራላዊ አወቃቀር ለመኮረጅ የሞከረው። ይህ ደግሞ የአገርን ነባራዊ ሁኔታ እና የማኅበረሰብን የብሔር ፌዴራሊዝም የ‹እኩል ያልሆነ እኩልነቶችን› የፈጠረ ስርአት ነው።

የብሔር ተኮር ፌዴራሊዝምን የምትትቹ ከሆነ በጥናት ላይ የተመሰረተ ምን አማራጭ አቅርባችኃል?
አንድ ኢሕአፓ በፕሮግራማችን ውስጥ አማራጭ ይሆናል ብለን ያቀረብነው መልክአ ምድርን መሰረት ያደረገ የፌደራል አወቃቀርን ነው። በዚህም አወቃቀሩ ወደ 17 የእስተዳደር መዋቅሮችን ያማከለ እንዲሆን እንፈልጋለን። ግን በዋናነት ታሪክ እና ባህልን መሰረት አድርጎ መሆን አለበት።

ስለዚህ ኢሕአፓ አቋም ተቀይሯል ማለት ይችላል?
በኢትዮጵያ ማእቀፍ ውስጥ የሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት እናምናለን። ቀድሞም ቢሆን ሌሎች እንደ ሕወሓት እና ሻዕብያ ያሉ ድርጅቶች እስከ መገንጠል ብለው ሐሳቡን ሲለጥጡት የኢሕአፓ አቋም ግን የትኛውም ብሔር ብሔረሰቦች ጥያቄ በኢትዮጵያ ማእቀፍ ውስጥ ይፈታል ብሎ የሚያምን ድርጅት ነበር። አሁንም ቢሆን የፓርቲው አቋም ያው ነው።

በታሪክ እንደምናውቀው ኹለት ዓመት ሙሉ የኢሕአፓ ሠራዊት በኤርትራ የታገተው ኢትዮጵያ ኤርትራን ቅኝ ገዝታለች ብላችሁ ተቀበሉ በሚል ጉዳይ ነው። ነገር ግን አሁንም ቢሆን በኢትዮጵያ አንድነት ውስጥ የሁለም ብሔር ብሔረሰቦች መብት እና ሌሎች የልማት ጥያቄዎች ይፈታሉ ብለን እናምናለን። መገንጠል የሚለውን አንቀበልም።

የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 39ን አትቀበሉም ማለት ነው?
የብሔር ብሔረሰብ እኩልነት፣ መብት የሚለውን እንቀበላለን። ነገር ግን እስከ መገንጠል የሚለውን ትናንትም አልተቀበልንም፣ ዛሬም አንቀበልም።
መብት ስንል ከመገንጠል ውጪ የሚነሱ ማንኛውንም ጥያቄ መስተናገድ አለበት። እንዲውም የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር ጭምር በአምስት ቋንቋዎች ተተርጉሞ መቅረብ አለበት። ምክንያቱም ለአገር አንድነት የጋራ ስሜት ጠቀሜታ እንዳለው ስለምናምን።

የፓርቲያችሁ ሥያሜ አሁንም ‹አብዮታዊ› የሚል ቃል አለው። የፖርቲው ርዕዮት ተቀይሮ ሳለ ዛሬም ‹አብዮት› የሚል ቃል ማስቀመጡ ለምን አስፈለገ?
እሱ እንደ አረዳድህ ነው። ‹አብዮት› ማለት ስር ነቀል ለውጥ ማለት ነው። ግን ያ ስር ነቀል ለውጥ እንዴት ይሁን የሚለው ነው። የድርጅቱ አብዮትን የሚያካሄድበት መንገድ እንጅ ሥያሜው ላይ አይደለም።

የ60ዎቹ ትውልድ አብዮትን በጉልበትና በመገዳደል ያካሄደ ቢሆንም፣ አሁን ግን ስር ነቀል ለውጥን በሐሳብ የበላይነት በማማን ለውጥ ይመጣል ብሎ የሚያምን ነው።

ኢሕአፓ እንዴት ወደ አገር ቤት ተመልሶ ለመታገል ወሰነ? ምን አስቻይ ሁኔታ አለ ብሎ ነው?
እንደ ኢሕአፓ ወደ አገር ውስጥ ስንገባ ሙሉ ለሙሉ ባይሆንም የተሻለ ፖለቲካዊ ምህዳር አለ ብለን ገምግመን ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ስርዓት አልበኝነት መፈናቀል እና ሞት እየተስተዋለ ነው። ይህ ሁኔታ ሰላማዊውን የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ምህዳር የሚረብሽ በመሆኑ መንግሥት የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥ አለበት ብለን እናምናለን።

ግን እኮ ‹ለውጥ› መጣ ከተባለበት ጊዜ አንስቶ በአገሪቱ እየተፈፀሙ ያሉ አሰቃቂ ግድያዎች፣ መፈናቀሎች፣ መንግሥታዊ በደሎች ሲፈፀሙ ምንም ያላችሁት ነገር የለም? ምንድነው ምክንያታችሁ?
በእርግጥ የተጠቀሱት ችግሮች እንዳሉ እንረዳለን። የተቻለንን እያደረግን ነው። ግን ዋናው ችግር የኛ አገር ሚዲያዎች እንደሚታወቀው ከተወሰኑ ግለሰቦች ወይንም መንግሥት የሚዘውራቸው የተግባቦት አውታሮች ናቸው። መግለጫ ስንጠራ እንኳ ሊመጡልን አልቻሉም። ግን ብዙ ጥረት ማድረግ እንደሚኖረን እናምናለን።

ሥያሜ ለመቀየር እንዴት አላሰባችሁም? ሕዝባዊ መሠረታችሁስ የትኛው የኅብረተሰብ ክፍል ነው?
ለብዙ ሁኔታዎች ሥያሜ ለመቀየር ለጊዜውም ቢሆን አልተወሰነም። ወደፊት ግን በጠቅላላ ጉባኤ የሚታይ እና ውሳኔ የሚሰጥበት ይሆናል፤ ሥያሜው እንዲሁም አርማው።
የኢሕአፓ መሠረት ጭቁኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው። ምናልባት ወደኋላ እንዳይመልሰን በድህነት አረንቋ ውስጥ ክንውን ብዙኀኑን የኅብረተሰብ ክፍል ማለታችን ነው።
በደህ እና ሃብታም በመካከል ያለውን ልዩነት ማቀራርብ ይገባል የሚል እምነት አለን። ለዚህም ሶሻል ዴሞክራሲ አስተሳሰብ መፍትሔ ይሰጣል በሚለው እናምናለን።

ሶሻል ዴሞክራሲ ምን ማለት ነው?
ሶሻል ዴሞክራሲ ለኢትዮጵያ ሕዝብ አኗኗር፣ ስሜት እና ባሕል የሚስማማ አስተሳሰብ ነው።
እስከ አሁን ድረስ ኢሕአፖ ውህደትም ሆነ ቅንጅት የመፍጠር ፍላጎት አላሳየም። የመስመር አንድነት ያለው ፓርቲ የለም ብሎ ነው ወይስ ሌላ ምክንያት አለው?
የምርጫ ቦርድ ቅንጅት፣ ውህደት እና ግንባር የሚፈጠርበት የራሱ አሰራር ቢኖርም ፓርቲውም የራሱ አካሄድ አለው። ይህ ሥልጣን የጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔን የሚፈልግ ነው። በኢትዮጵያ አንድነት የሚያምኑ እና የሶሻል ዴሞክራሲ አስተሳሰብን ከሚቀበሉ ፓርቲዎች ጋር ግን ተባብሮ ለመሥራት ግን ዝግ አይደለንም።

ኢሕአፓ የት አካባቢ ነው ቢሮዎችን ከፍቶ እየተንቀሳቀሰ ያለው?
ለጊዜው በሦስት ክልሎች ምለትም በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በደቡብ እንዲሁም በኹለቱ የከተማ አስተዳድሮች በአዲስ አበባና በድሬዳዋ ነው እየተንቀሳቀሰ ያለው። ነገር ግን በአፋር፣ በቤንሻንጉል እና በጋምቤላ እንቅስቃሴዎች እያደረግን ነው። በአጠቃላይ 12 የሚደርሱ ጽሕፈት ቤቶች አሉን።

አገር አቀፍ ፓርቲ ሆኖ በሦስት ክልል እና በኹለት ከተማ አስተዳደር እየተንቀሳቀሱ እንዴት አገር ለመምራት እና መንግሥት ለማቋቋም ይቻላል? ለተሳትፎ ወይስ አገር ለመምራት የሚል ጥያቄ ያስነሳል። በተያያዘ ምናልባትም ምርጫ መራዘሙ ለፓርቲው ያመጣው ጥሩ ነገር አለ?
ጽሕፈት ቤት መክፈት የተዳራሽነት ጉዳይ ቢኖረውም በራሱ ግብ አይደለም። አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታም እንኳን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ተደርቦ ከፀጥታና ከሌሎች ጉዳዮች ጋር ተያይዞ እንደልብ መንቀሳቀስ እና ማደራጀት ቀላል አይደለም። አንዳንድ ቦታዎች ላይ እኮ እንዳትገቡ፣ እንዳትደርሱ የሚሉ ሁሉ አሉ። ጽንፈኛ ኃይሎች ዛሬም እያስቸገሩ ነው። ግን ሁኔታዎች እንደሚቀየሩ ተስፋ እናደርጋለን።

በተያያዘ ምርጫው መራዘሙ ለእኛ ወርቃማ አጋጣሚ ነው። ወደ አገር ከገባን አጭር ጊዜ ነው። በቂ የሆነ እንቅስቃሴ ብናደርግም ከፊታችን ለሚጠብቀን አገራዊ ምርጫን በተመለከተ በአምስት ዓመት እቅዳችንም ያስቀመጥነው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቂ መቀመጫ ለማግኘት ነው።

ምክንያቱም አገዛዝን በአንዴ ማስወገድ አይቻልም። በአቋራችም ወንበርን መሻትም የምንፈልገውን ዴሞክራሲያዊ አገር አይፈጥርም። ስለዚህ በቂ ውክልና ማግኘት ከዚያ ግን መንግሥት የመሆን ርዕይ አስቀምጥናል። ተሳትፎ ሳይሆን የእውነት አገር መምራትን ነው የምናስበው።

የቀደመው ኢሕአፓ አባለት ጥንካሬ እና የአሁን ዘመኖቹ እንዴት ነው?
የምናነጻጽረው በዓላማ ማለትም በኢትዮጵያ አንድነት፣ በችግር እኩልነት፣ ለደሃው በመቆም ባላቸው የመንፈስ ጥንካሬ ነው። በኋላ በተግባር የሚታይ ቢሆንም አሁንም ይህ ስሜት እንዳለ እናምናለን።

የቀደመው ኢሕአፓ ከአሁኑ ይለያል። በተራዘመ ትግል ፍል እናገኛለን። በከተማ እና በገጠር ትልቅ ትግል ላይ ስለነበር የወጣቶች ስሜት የተለየ ነበር። በኢሕአፓ በፍፁም ቁርጠኝነት የማይታለፍ ጠንካራ እምነት አሁንም ቢሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ ከአገዛዝ መውጣት አለበት ብሎ ያምናል።

የመሬት ባለቤትነትን በተመለከተ የኢሕአፓ አቋም ምንድነው?
መሬት የሕዝብ መሆን አለበት። በግልም፣ በወልም ቢሆን የመሬት ባለቤት ሕዝብ መሆን አለበት እንላለን። መሠረታዊ አገልግሎቶች ትምህርት፣ ጤና ወዘተ ለማቅረብ ሲባል እንዲሁም ለሌሎች ሕዝባዊ አገልግሎቶችን ለማድረስ ሲባል።

አመራርን የማግዘፍ አባዜ፣ በአንድ የእዝ ሰንሰለት መመራት፣ ኢ-ዴሞክራሲያዊ አካሄድ የመሳሰሉት እና ኢሕአፓ አሁን ተፋትተዋል ወይስ እንዳለ ነው?
ፍፁም የተለየ ነው። እንኳን ዛሬ፣ ከአገር ተሰድዶ ተግፍቶ ከወጣም በኋላ የተለወጠ ነገር ነው። አመራር የወል፣ አሳታፊ የሆነ ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ የሚከወን ነው።
የግለሰብ መሸጦነትን በፍፁም አንቀበልም። ያ መሸጦነት ሄዶ ሄዶ ግለሰባዊ አምባገነንነትን ያመጣል። ይህ እንደ ድርጅትም ሆነ እንደ አገር መቀየር አለበት ብለን እናምናለን። ኢሕአፓም የግለሰብ መሸጦነት እንዲፈለፈል አያደርግም።

ኢሕአፓ ወደ ግማሽ ምዕተ ዓመት የተጠጋ እድሜ እያስቆጠረ ነው። ለመሆኑ እስከ አሁን ምን እየሠራ ነበር?
ብዙ ሰው የማያውቀው ትልቅ እውነት፣ አገር ውስጥ ላለፉት 25 ዓመታት የፖለቲካ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ኢሕአፖ ከጀርባ ነበር። በተለይ ኅብረ ብሔራዊ ፖርቲዎች ለነበሩት ምሳሌ ለማንሳት በ1997 ምርጫ ወቅት ቅንጅት እና ኅብረትን ደግፈናል። እነዚህን ድርጅቶች የማነሳው አሁን በሕይወት ስለሌሉ ነው።

ከሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ህልፈት በኋላም ሸንጎ የሚባል እንቅስቃሴ ነበር። እሱ የኢሕአፓ እንቅስቃሴ ነበር። ከዚያም በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ከወጡ በኋላ የነበርውን የዳያስፖራ እንቅስቃሴ ሲያስተባብር ነበር። ማንም ሕሊና ያለው ሰው የማይክደው ጉዳይ ነው።

ኢሕአፓ ከትጥቅ ትግል በ1984 ተገፍቶ ከወጣ በኋላ ዝም ብሎ የተኛ ፖለቲካዊ ፓርቲ አይደለም።

ፓርቲው ይህንን ግዙፍ ዓላማ ለወጣቶች ለማስተላለፍ የሄደበት ርቀት ምን ይመስላል?
ትውልድን ማያያዝ እንዳለብን እና ከቀደምቶቻችን ልምድ በመውሰድ ሙሉ ለሙሉ ወደ አገር ውስጥ በመመለስ ፖለቲካዊ ትግሉን ለማካሄድ እየሠራን ነው። ኢሕአፓ የሌለበት ክልል የለም። የኢሕአፓ አባላት ያልተገረፉበት፣ ያልተገደሉበት፣ ያልተሰቃዩበት ክልል የለም።

ያ ዋጋ የተከፈለበት ጉዳይን እኛ በቀላሉ መመንዘር እንችላለን። ብሔር ተኮር የሆኑ ፓርቲዎች ኢሕአፓን ሲያስቡ ጭንቀት ውስጥ ይገባሉ። እነሱ በሚያስቡት እና ብሔርን መሰረት አድርገው ‹የሽቀላ ፓለቲካ›ን እንደሚያራምድ ፓርቲ አይደለም፣ ኢሕአፓ።

1983 የተደረገውን ለውጥ ተከትሎ ሁሉም ፓርቲዎች ሲጋበዙ ኢሕአፓ አልተጋበዘም። ይባስ ብሎ በቻርተሩ ጊዜ የኢሕአፓ አመራር የነበሩ ጓዶች አዲስ አበባ ለድርድር ሲመጡ እነ አበራ ከማነአብ እና ገነት ግርማ (የግርም ወልደ ጊዮርጊስ ልጅ) ያሉት ቦሌ አየር ማረፊያ ሲደርሱ ታሰሩብን።

እንደ ገና ኹለተኛው ልዑክ ካይሮ ላይ ትራንዚት ሲያደርጉ በሻዕቢያ እና በወያኔ እንዲሁም በሆስኒ ሙባረክ ሴራ ተይዘው የጉዞ ሰነዳቸው ተቀምቶ እንዲንገላቱ ሆኗል።
ሁሌም ኢሕፓን ከሰላማዊው መንገድ በመግፋት የተጠመዱት የኢትዮጵያ ግዢዎች ናቸው። ከሰላማዊው የፓለቲካ መድረክ የተገፋ የመጀመሪያው ድርጅት ነው።

የሰዎችን ሕይወት በማስገበር መቀጠል ትክክል አይደለም ብሎ ገምግሞ ነው ሌሎች ፓርቲዎችን ወደ መደገፍ የገባው። ለጽሕፈት ቤት ኪራይ፣ ለሥራ ማካሄጃ፣ የአመራሮች ውጪና ጉዞ ሁሉ በመሸፍን ሲያግዝ ቆይቷል። ብሔር ነክ የሆኑትን በኅብረት በኩል፣ ኅብረ ብሔራዊ የሆኑትን ደግሞ በቅንጅት በኩል ሲያግዝ ቆይቷል። በዚህም የኢሕአፓ አባላት ከፍተኛ መዋዕለ ነዋይ አፍስሰዋል። የጓዶቻቸውን ዓላማ ዳር ለማድረስም አየታገለ ነው።

የኢሕአፓ ዋናው ግብ የኢትዮጵያ ልማት እና ዴሞክራሲ እንዲሰፍን ነው እንጂ እንደ ሌሎች ፓርቲዎች ጅምላና ችርቻሮ ንግድ ሳይቀር መቆጣጠርና በሕዝብ ሥም የንግድ ተቋማትን ከፍቶ ለግለሰቦች መፈንጫ እንዲሆን ማድረግ አይደለም። በፊትም ቢሆን ኢሕአፓ በሚንቀሳቀስባቸው ቦታዎች ወፍጮ ቤት እና የምንጭ ማጎልበት ሥራ ሲሠራ የነበረ ሕዝባዊ ድርጅት ነበር። ዛሬም ይህንኑ ነው የሚያስቀጥለው።

ኢሕአፓ ለተፈጠረው ችግር ብቻ ነው ሥሙ የሚነሳው። ግን ከዚያ በላይ ኢሕአፓ ያበረከተው ግዙፍ አስተዋፅኦም አለ።
በኢትዮጵያ ሚዲያ ውስጥ ኢሕአፓ አሁንም ድረስ ከአገር ጥፋት፣ እርስ በእርስ የመገዳደል እና ትርምስ ጋር ብቻ እንዲቆራኝ ተደርጓል። በ17ቱም የደርግ ዘመን ሆነ የ27 ዓመት የወያኔ ዘመን ሆን ተብሎ ሥም ማጥፋት ሲደረግበት ሰንብቷል።

በኢትዮጵያ ለደረሰው ጫፍ የወጣ ጥላቻ እንዲሁም መገዳደል፣ በአጠቃላይ ለሆኑት ጥፋቶች ኢሕአፓ ይቅርታ አይጠይቅም እያልከኝ ነው?
‹ማንን ነው ይቅርታ የምንጠይቀው?› የሚለው ነው ዋናው ጉዳይ። ይሄ ሚዲያ ስላገኘ የሚዘባርቀውን ትንንሹን ‹ኤሊት› ተብዬውን ተወው። ግን በወቅቱ ለተፈጠሩት ጥፋቶች ኢሕአፓም ድርሻ ነበረው ብለን አምነን በጠቅላላ ጉባኤ ተወስኖ የኢትዮጵያ ሕዝብን ይቅርታ ጠይቀናል።

ግን ይሄ ይቅርታ ጨፍጫፊውን ደርግ እና ሌሎች ገዢዎችን አይጨምርም። በዘመኑ የነበሩ ኃይሎች ሁሉ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ በማቀጨጭ ለተፈፀመው ሞት አግባብ ያልነበረ አካሄድ ይቅርታ መጠየቅ ያለባቸው ናቸው። ኢሕአፓ በዘጠነኛው ጉባኤ ይቅርታ ጠይቋል። አገዛዙን ግን አይጠይቅም ።

ግን እኮ በወቅቱ ለተፈጠረው የቀይ ሽብር እና ነጭ ሽብር ጣጣ የመጀመርያውን ጥይት በመተኮስ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ወደ መጠፋፋት እንዲያመራ ያደረገው ኢሕአፓ ነበር ተብሎ ይነሳል?
የመጀመሪያውን ጥይት ማን ተኮሰው የሚለውን ጉዳይ ኢሕአፓ የማስረዳት ሸክም የለበትም። በጊዜው የሕግ የበላይነትን የሚያሰፍን ፍርድ ቤት፣ ፖሊስ እና ሌሎች የፀጥታ አካላትን አገዛዙን ይመሩት የነበሩ የእነ መንግሥቱ ኃይለማርያም ጉዳይ ነው። ይህ አካል ነበር ሥራውን መሥራት የነበረበት።

ይህ ኢሕአፓ ያነሳቸውን የዴሞክራሲ እና የፍትሃዊ ልማት ተጠቃሚነት እንዲሁም የብሔር እኩልነት ጥያቄዎችን በማሳነስ ማን ተኮሰው በሚል ማደናገር ተገቢ አይደለም። መጠፋፋቱ ልክ አይደለም ብሎ ማንሳት ነው ያለብን። ኢሕአፓ የሸቃዮች ሐሳብ ነው ብሎ ያምናል።

ኢሕአፓ የሥልጣን ጥም እንጂ ለአገር አንድነት ቁብ የሚሰጠው ድርጅት አይደለም። ለዚህም በሶማሊያ ወረራ ወቅት ከዚያድባሬ ጦር ጋር አብሯል የሚል ክስ በተደጋጋሚ ይነሳል። ለዚህስ ጉዳይ ይቅርታ አትጠይቁም?
ኢሕአፓ እንደ ሌሎች ድርጅቶች ሕወሃት እና ሻዕብያ አገር በማስገንጠልም ሆነ አገር በመሸጥ ወይም ከጠላት ጋር በማበር የሚወነጀል ድርጅት አይደለም።
እኛ ውዝፍ ስለሌለብን ችግር የለብንም። ግን ቁጭ ብለን እውነቱን እንነጋገር ከተባለ፣ እንነጋገር ችግር የለብንም። በመጽሐፍ ፅፎ ስላወጣ የሚቀየር ሀቅ አይኖርም። በእጄ ዝንብ እንኳን አልገደልኩም እያሉ የሚመፃደቁ ናቸው፣ ኢሕአፓን የሚወነጅሉት።

በሶማሊያ ጉዳይ ኢሕአፓ የሶማሌ ጦርነትን ደግፎ አብሮ ቆሟል የሚሉት ጉዳዩን በሚገባ ባለመረዳት የመጣ ነው። በዚህ ጉዳይ ኢሕአፓ ከሶማሊያ ጀርባ ሆነው ሲወጉን አይተናል የሚሉ ሁሉ አሉ።
የሆነው ግን በሀረር ኢንተር- ዞን ውስጥ የነበሩ ጥቂት አመራሮች በኩል የኢሕአፓን ማዕከላዊ ኮሚቴ ሳያማክሩ የወሰዱት አቋም ነበር። ይኸውም እዚያ አካባቢ የነበሩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ለሶማሌ ጦርነት በተመለከተ የኢሕአፓን አቋም አጥብቀው በጠየቁበት ወቅት የተሰጠ የአንድ ኢንተርኔት ዞን፣ ወይም የመጨረሻው አመራር መዋቅር እንጂ የኢሕአፓ አቋም ነው ብሎ መውሰድ አይቻልም። ግን በዚያ ጦርነት የኢምፔሪያሊስቶች እጅ ያለበት ጦርነት ነበር ብለናል።

ኢህአፓ ከሃገር ክህደት ጋር በተገናኘ በፍጹም የሚታማ ድርጅት አይደለም። መቼም የትም ቦታ ለይ

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here