የቀድሞ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢ/ር) በህገ ወጥ መንገድ የተሰጠ ምንም አይነት ቤት የለም አሉ

0
921

 

ለዚህ ምላሽ ለመስጠት ተገቢው ቦታ ላይ ባልገኝም ከዚህ የመጓተት ፖለቲካ አስተሳሰብ መውጣት አለመቻል ግን ትልቅ ህመም እንደሆነ ይሰማኛ ያሉት የቀድሞው የአደስ አበባ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢ/ር)  የመሬት ወረራን በተመለከተ ከመጀመሪያዋ ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻዋ እለት ድረስ ጠንካራ የሆነ እርምጃ ስንወስድበት የቆየንበት ጉዳይ ነው ሲሉ ምላሻቸውን በማሕበራዊ ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።

 

በተለያዩ ጊዜዎች የወሰድናቸው እርምጃዎችም ህያው ምስክሮች ናቸው  ያሉት ታከለ እኛ ህገወጥ የመሬት ወረራን ለመከላከል እርምጃ ስንወስድ የዛሬ ተቺዎች የሰብአዊ መብት ተነካ፣ ዜጎች ተፈናቀሉ ብለው ዘመቻ ከከፈቱብን ውስጥ ነበሩም ብለዋል።

 

ለ20ሺህ አርሶአደሮች የተሰጡ የኮንዶሚኒየም ቤቶች ከአንድ ዓመት ተኩል በፊት በካቢኔ የተወሰነና የተተገበረ ነው።

በድብቅ የተተገበረም ሳይሆን በመንግስት ሚዲያም በይፋ የተገለፀ ነበር በማትም ገልጸዋል።

 

ከመሬታቸው ተፈናቅለው ሜዳ ላይ ከወደቁ በራሳቸው መሬት ላይ በተሰራ ህንጻ ዘበኛ እና ተሸካሚ ሆነው ከቀሩ 67 ሺህ አባወራዎች መሃል የከፋ ችግር ላይ ለወደቁት 20 ሺህ ኮንዶሚንየም ቢያንስ እንጂ የሚበዛ አይደለምም ብለዋል።

 

ከዚህ ውጭ በህገወጥ መንገድ የተሰጠ ምንም አይነት ቤት የለም፤ ይህ ሥራችን በተደጋጋሚ በይፋ ስንናገር እንደነበረው የምናፍርበት ሳይሆን የምንኮራበት ነው ሲሉም አስታውቀዋል።

 

አንድም ቀን በግፍ ለተፈናቀሉ አርሶአደሮች የመቆርቆር ስሜት አሳይቶ የማያውቅ ቡድን ዛሬ የአርሶአደሮችን ጉዳት ለተቀባይነት ማግኛ መጠቀሚያ ሲያደርገው ማየት ያሳዝናል።ነገር ግን በሃሰተኛ እና በተጋነነ መረጃ ጠንካራ መምሰል እንጂ መሆን አይቻልም ሲለም ምላሻቸውን አክለዋል።

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here