ፍርድ ቤቱ በልደቱ ላይ ክስ እስከሚመሰርት መርማሪ ፖሊስ እንዲሰጠው የጠየቀውን ተጨማሪ ጊዜ ውድቅ አደረገ

0
534

ልደቱ አያሌው ላይ ፖሊስ ሲያካሂድ የቆየውን ምርመራ ማጠናቀቁን ገልፆ አቃቤ ህግ ክስ እስከሚመሰርት ድረስ 14 ቀን ተጨማሪ ጊዜ ይሰጠኝ ሲል ፍርድ ቤቱን የጠየቀ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ የፖሊስ ጥያቄ የህግ አግባብነት የለውም ሲል ውድቅ አደረገ።

 

ፍርድ ቤቱ የፖሊስ የምርመራ መዝገብ መዘጋቱን ገልፆ  ልደቱ አያሌው በሌላ መዝገብ የዋስትና ጥያቄያቸውን እንዲያቀርቡ አዟል።

 

ለአራተኛ ጊዜ በቢሾፍቱ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት የቀረቡት ልደቱ አያሌው ”ፍርድ ቤቱ የጤናዬን ሁኔታ ከግምት ውስጥ ማስገባት አለበት፣ ከዚህ በፊት ያቀረብኩት የህክምና ማስረጃ የልብ ህመምተኛ መሆኔን ተከትሎ ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ ተጋላጭ እንደሚያደርገኝ ተጠቅሶ የተፃፈ ቢሆንም፥ በፖሊስ ጣቢያ የኮቪድ-19 ምርመራ አልተደረገም፣ ጤናዬን ከግምት ውስጥ ያስገባ ርቀትን የጠበቀ አያያዝ አልተደረገልኝም፣ በተጓዳኝ ደግሞ በአንድ መፀዳጃ ቤት 50 እስረኞች እንደሚጠቀሙና ይህም ለጤናዬ አደጋ ነው‘ ማለታቸውን ፋና ዘግቧል።

 

”ፖሊስ እስከ ዛሬ ሲያከናውን የነበረው ምርመራ አዲስ ውጤት ያልታከለበት፣ አስተባብረሃቸዋል የተባሉ ተባባሪዎች ያልተያዙበት እና ምስክሮቼ ያልቀረቡበት ነው‘ በማለት መቃወሚያዎችን ያሰሙ ሲሆን ፖሊስም እስካሁን ሲያከናውን የነበረው ምርመራ በእጃቸው ላይ የነበሩ የስልክ መልዕክቶችን እንዲሁም በእጃቸው ላይ የተገኘ የሽግግር መንግስት መመስረቻ ሰነዶች ውጤትን በመዝገቡ ማካተቱን አስታውቋል።

 

እንዲሁም  ”ምርመራዬን አጠናቅቂያለሁ፣ ይህም መዝገቡንም አቃቤ ህግ መርምሮ ክስ እስከሚመሰርት ድረስ ተጨማሪ 14 ቀን ይሰጠኝ‘ ብሎ የጠየቀ ቢሆንም ፍርድ ቤቱም ”በዚህ መዝገብ ላይ ምርመራ መጠናቀቁን በመግለፅ በወንጀለኛ መቅጫ ስነስርዓት ህግ አንቀፅ 59 1 እና 2 መሰረት ያቀረብከው ጥያቄ አግባብነት የሌለውና ያጠናቀከው መዝገብ ተጨማሪ ጊዜ የማያሰጥ ነው፣ ጥያቄህም የህግ አግባብነት የለውም‘ ሲል ውድቅ አድርጎበታል።

 

ይሁንና በዛሬው ዕለት በሁለት ጠበቃ ተወክለው የቀረቡት ልደቱ አያሌው የጠየቁት የዋስትና ጥያቄ በዚህ የተዘጋ መዝገብ ሳይሆን በሌላ መዝገብ ማቅረብ ይችላሉ ሲል የመርማሪ ፖሊስ መዝገብን መዘጋቱም ተሰምቷል።

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here