ሱዳን ታላቁ የህዳሴ ግድብ ከገጠማት የጎርፍ አደጋ ጋር እንደማይያያዝ ገለፀች

0
389

ሱዳን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በሀገሯ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ከሚገኘው የጎርፍ አደጋ ጋር እንደማይያያዝ አስታወቀች።
የሱዳን የመስኖ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በቅርቡ በሱዳን በደረሰው የጎርፍ አደጋ ላይ የሚያሳድረው ምንም ተጽዕኖ እንደሌለ አስታውቋል።
ዋና ከተማ ካርቱም ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የሱዳን የመስኖ ሚኒስትር ያሲር አባስ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታው ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ ሱዳንን ከጎርፍ ይጠብቃል ብለዋል።

የመስኖ ሚኒስትሩ አያይዘውም ሱዳን ከዚህ ችግር እንድትወጣ አለም አቀፉ ማህበረሰብ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
የአሁኑ የጎርፍ መጥለቅለቅ ባለፈው ምዕተ ዓመት ውስጥ ከተከሰቱት የከፋ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን በዚሁ ምክንያት በ 43 መንደሮች ውስጥ የሚኖሩትን ከአደጋው ለማሸሽ መቻሉን የሲቪል መከላከያ ሊቀመንበሩ ኦመር ሳኢድ አስታውቀዋል።

ሱዳን የጎርፍ አደጋው ባለፉት ሳምንታት ውስጥ በቲኒሹ የ 100 ሰዎች ሕይወት መቅጠፉ እና 40 ሺህ ቤቶች መውደማቸውን ተከትሎ ለሶስት ወር የሚቆይ ብሄራዊ አስቸኳይ የጊዜ አዋጅ ማወጇ ይታወሳል።

የሱዳን የጸጥታና የመከላከያ ምክር ቤት ስጋት የደቀነው ጎርፍ ሀገሪቱን የተፈጥሮ አደጋ ቀጠና እንዳደረጋት አስታውቆ ነበር።
በዚህ አመት ኢትዮጵያን ጨምሮ የምስራቅ አፍሪካ በሀገራት ከፍተኛ የሆነ የዝናብ መጠን እያስመዘገቡ እንፈሚገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
የጎርፍ አዳጋው ሰለባ የሆነችው ሱዳን ታድያ እስካሁን ጎርፉ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰዎች ላይ ጉዳት አድርሷል ብላለች። አናዶሉ እና ሲጂቲኤንን ምንጭ አድርጎ ኢዜአ ዘግቧል።

ቅጽ 2 ቁጥር 97 መስከረም 2 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here