የአዲስ ዓመት ሸመታ

0
766

አዲስ ዓመት ሲመጣ የአገራችን መልከዓ ምድር በአደይ አበባ በማሸብረቅ የአደስ ዓመት መምጣትን ያበስራሉም። ምድር በአደይ አበባ ስታሸበርቅ፤ በከተማ የሚገኙ የገበያ ማዕከላት ደግሞ የሸማቾችን ቀልብ ሊስብ ይችላል ባሉት ነገር፤የዓውደ ዓመቱ ሙዚቃዎች በማስደመጥም ያደምቃሉ፤ ያሰውባሉ።

ሸማቾቹም የአዲስ ዓመትን መምታት በጥሩ ሁኔታ እንደ በዓሉ ስያሜ በአዲስ ተስፋ ለመቀበል ቤታቸውን ከማስጌጥ አንስቶ ለዓውደ ዓመቱ ያስፈልጋል የሚሉትን ፤አቅማቸው በፈቀደውን መጠን ለመሸመት ደፋ ቀና ይላሉ። ለመብላት እና ለመጠጣት ያስፈልገናል ያሉትን ሁሉ ከመሸመት ባሻገር ወደ ለልጆቻቸው እና ለራሳቸው አዳደስ አልባሳትንም ይሸምታሉ።

የሸመታው ጉዳይ በዓሉ ሳምንት ሲቀረው ወይም የበዓሉ መዳረሻ ቀናቶች ዋዜማ ጀምሮ ሩጫው እና ሽርጉዱም ለጉድ ይሆናል።የገበያ ማዕከናትም የበለጠ በሸማቾች ሲጨናነቁ ይስተዋላል።

የ አዲስ ዓመት ገበያ ሸመታ
ሙሉነሽ ካሳ የተባሉ እናት ከጨርቅ የተሰራ ጥቁር የፊት ጭምል (ማስክ ) አድረገው መርካቶ አካባቢ ከሚገኘው አንድ መደብር ሲገበያዩ አገኛናቸው። እንዴት ነው ገበያው የሚል ጥያቄም አነሳንላቸው እርሳቸውም‹‹ተመስገን ነው ለዚህም መድረሳችን ጥሩ ነው ገበያ ያው እንደምታይው ነው ዘንደሮ ጥሩ ነው ብዙም የተወደደ ነገር የለም ሽንኩርት ነው እሱም ከባለፈው ጊዜ ይሻላል›› ሲሉ መልሰዋል።

ምንም እንኳን የኮቪድ 19 ወረርሽ እንዳይስፋፋ የሰዎች መራራቅ እንደ መፍትሔ ቢነገርም በተዘዋርንባቸው ቦታዎች ላይ የሰዎች መጨናቅ እንደነበር አዲስ ማለዳ ታዝባለች።በተለያዩ ቦታዎች ላይ የአዲስ ዓመት ሸመታ ምን ይመስላል ብላ ቅኝት አድርጋ ነበር። በቅኝቷም ለበዓል የዶሮ እና የበግ የገበያ ሁኔታን ዳስሳለች።

የበሬ እና በግ ዋጋ
የገበያ ቅኝት ካደረግንባቸው ቦታዎች ውስጥ የዊንጌት እና አዲሱ ገበያ አካባቢ የሚገኙት የገበያ ስፍራዎች የበግ እና በሬ መሸጫ ዋጋ ምን እንደሚመስል የገበያ ቅኝት ያረገቸው አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው ነጋዴዎቹ የዘንድሮው ገበያ በጣም መቀዛቀዙን እና የዋጋ ጭማሪ ሳይሆን እንደውም ከአምናው ጋር ሲነጻጸር ቅናሽ ማሳየቱን ከነጋዴዎች ተረድታለች።

ለገበያ የቀረቡትን በጎቹ ሳር ሲያበሉ ያገኘናቸው አንድ ነጋዴ ሲናገሩም‹‹የዘንድሮው ገበያ ቀዝቃዛ መሆኑን እና ባለፈው አመት አንድ በግ እስከ 7 ሺህ ብር መሸጣቸውን አስታውሰው ዘንደሮው ግን ከ2000 ጀምሮ እስከ 5 ሺህ ብር ነው እየሸጡ መሂናቸውን›› ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።
ከዊንጌት ከፍ ብሎ ወደ ኢዲሱ ገበያ አካባቢ በሚገኘው የበሬ መሸጫ ቦታ ላይ ደግሞ የበሬ ዋጋ ከ12ሺህ ጀምሮ 38 ሺህ ብር እየተሸጠ እንደሆነ ነጋዴዎች ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

አይ መርካቶ!
አገር ከየጓራው ወጥቶ
አንችን ብሎ ነቅሎ መጥቶ
ግሳንግሱን ጋዙን ሞልቶ
ኀልቁ መሳፍርትሽ ፈልቶ
ባንች ባዝኖ ተንከራቶ

አይ መርካቶ በማለት ሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድህን የግጥም ስንኝ ወደ ቋጠረላት መርካቶም በማቅናት አዲስ ማለዳ የዘንደውሮውን የዶሮ ገበያ ዋጋ ምን ይመስላል በማለት ቃኝታለች።

በመርካቶ ‹‹ዶሮ ተራ›› ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዶሮ ሲገበያዩ ያገኘናቸው አድማሱ ሻንቆ የተባሉ ጎልማሳ ሰው በቀኝ እጃቸው ኹለት የታሰሩ ዶሮዎች ይዘዋል፤ የዘንድሮ የዶሮ ዋጋ እንዴት አገኙት ብለን የጠየቅናቸው ሲሆን እርሳቸውም የዘንድሮው ዋጋ ጥሩ የሚባል እንደሆነ እና ኹለቱን ዶሮዎችን በ600 ብር እንደገዙም ነግረውናል።

አለሙ አርጋ የተባሉ ነጋዴ ደግሞ ‹‹ዘንድሮ ምን እንደሆነ አላውቅም አንድ ዶሮ ከ280 እስከ 350 ብር እየተሸጠ መሆኑን አንስተው ምክንያቱ ግን ግልፅ አለመሆኑን ተናግረዋል። አምና እስከ እስከ 500 ብር መሸጡን አስታውሰዋል። ዶሮ ወጥ ለመስራት አስፋጊ የሆነው የሀበሻ እንቁላል ስድስት ብር ሲሸጥ የፈረንጅ እንቁላል ደግሞ በ5ብርከ50 ሳንቲም ሲሸጥ ተመልክተናል።

አንድ ኪሎ ነጭ ሽንኩርት በ70 ብር ሲሸጥ።በአንፃሩም የአንድ ኪሎ ሽንኩርት ዋጋ ከ28 ብር እስከ 33 ብር ሲሸጥ ተመልክተናል።
የምግብ ቅቤም ከ240 ብር እስ 300 ብር ዋጋ ተቆርጦለት ተመልክተናል።

የባህል አልባሳት
ከጊዜ ወደ ጊዜ የባህል አልባሳቶቻችን በተለዪ ዲዛይን እየተሰሩ ለበዓል እና ለሌሎች ዝግጅቶች ተመራጭ እየሆኑ ከመጡ ሰነባብተዋል። በበዓል ቀን ቢሆንም ሴቶቻችን ምርጫ የሚያርጉደት የባህል ልብስ ዋጋን በተመለከተው የገበያ ዳሰሳ አድገናል።

በመርካቶ ሸማ ተራ የሀገር ባህል ልብስ መሸጫ መደብሮች ውስጥ በተለያዩ ቀለማት ደምቀው የሸማኔ እጅ ያረፈባቸው አልባሳትን ተመልክተናል። ነጋዴዎች ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት ከሆነም ኮቪድ 19 ወረርሽኝ ስራቸውን ከሚጠበቀው በላይ ጫና እንደፈጠረባቸው ነው ያስረዱት። የሰዎች እንቀስቃሴ መገደብ እንደ ሰርግ እና ሌሎች ፕሮግራሞች እንዳይደረጉ መከልከላቸው ገበያውን ከሚገባው በላይ ጎድቶታል ይላሉ።

ከዚህ ቀደም ከ2ሺህ ጀምሮ እስከ 15ሺህ ብር ይሸጥ የነበሩ የሴቶች የባህል አልባሳት በአሁን ወቅት ዋጋቸው ቀንሶ ከ1 ሺህ 500 ብር ጀምሮ እስከ 8 ሺህ ብር እየተሸጡ እንደሆነ ነጋዴዎቹ ነግረውናል።

ሌላው አዲስ ዓመትን ተከትሎ የሚመጣው የትምህርት ቤቶች መከፈት ጉዳይ ፤ ሸማቾች ለልጆቸው የሚሆኑ ነገሮችን እንዲገበዩም ያርጋቸው ነበር።ወቅቱ መቼ ትምህርት እንደሚጀመር ይፋ አለማድረጉንም ተከትሎ ከዚህ በፊት የነበረው የትምህር ቁሳቁስ ፍላጎት መቀነሱን ነው ያነገርናቸው ነጋዴዎች የሚያረዱት።
ወትሮ ይሟሟቅ የነበረው ገበያ መፍዘዙን የሚመሰክረው አመዴ ተራ አካባቢ የህጻናት እና አዋቂዎችን ቦርሳ ሲሸጥ ያገኘነው ሽኩር ተማም አንዱ ምስክር ነው።ነገር ግን የተማሪዎች ቦርሳ ዋጋ ከ250 ብር ጀምሮ እየተሸጠ እንደሆነ ለማወቅ ችላለች።

በአጠቃላይ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ የሰዎችን የመግዛት አቅም በመፈታን የፈለጉትን እና ያሻቸውን እንዳያርጉ ያገዳቸው ሲሆን በዚህ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ገበያ ላይ ተፅዕኖ እያደረሰ መሆኑን አደስ ማለዳ ከነጋገቻቸው ሸማቾች ጀምሮ እስከ ነጋዴዎች ለመረዳት ችላለች።

በመሆኑም ይህ ወረርሽኝ ጠፍቶ ያለ ጭንቀት ከዚህ ቀደም ሰዎች በዓላትን ከቤተሰብ ፣ከዘመድ አዝማድ እና ከጎረቤታቸው ጋር በመጠያየቅ እና በመሰባሰብ በዓሉን የማሳለፍ ምኞታቸውን አልሸሸጉም።

ቅጽ 2 ቁጥር 97 መስከረም 2 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here