በኹለት ወራት ለሕዳሴው ግድብ ከ272 ሚሊየን ብር ተሰብቧል

0
706

ባለፈው ሀምሌ አንድ በጀመረው የ2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሁለት ወራት በአገር አቀፍ ደረጃ ከ272 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር ላይ ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ገቢ ተሰብስቧል ተባለ።

የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር ኃይሉ አብርሃም ዜጎች ለሕዳሴው ግድብ በተለያዩ ጊዜያት ድጋፍ ሲያደርጉ መቆየታቸውን አስታውሰዋል። ገንዘቡ የተገኘው በቦንድ፣ በስጦታ እና በ8100 አጭር የጽሁፍ መልዕክት ገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብሮች መሆኑንም ገልጸዋል።

ባለፈው ነሐሴ ወር ከ152 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ በመሰብሰብ የግድቡ ግንባታ ሥራ ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ብቻ ከፍተኛ ገንዘብ ማግኘት ተችሏል ነው የተባለው። እንዲሁም በሐምሌ ወርም ከ119 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር በላይ ለሕዳሴው ግድብ ግንባታ ገቢ መሰብሰቡን ተገልጿል።

በአጠቃላይ ከተሰበሰበው ገንዘብ ውስጥ ዲያስፖራው ባለፉት ሁለት ወራት ከ5 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉም ታውቋል። እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ በ2013 በጀት ዓመት ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ከ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ለመሰብሰብ ታቅዷል ብለዋል።

ቅጽ 2 ቁጥር 98 መስከረም 9 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here