የፌደራል ፀረ ሙስና ኮሚሽን ባለፈው ሳምንታት ሃብታቸውን ያላስመዘገቡ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን ስም ዝርዝር ለፌደራል ፖሊስ መላኩ ይታወሳል።
ሥማቸው የተላለፈው ባለሥልጣን ያለፉበትን ሂደት አስመልክቶ ከ አቶ መስፍን በላይነህ በፌደራል ፀረ ሙስና ኮሚሽን የሃብት ማሳወቅና ማስመዝገብ ዳሬክቶሬት ዳይሬክተር ጋር ቆይታ አድርገናል።
አቶ መስፍን ኮሚሽኑን ከተቀላቀሉበት 2002 ጊዜ ወዲህ በተለይም በዚሁ ዳይሬክቶሬት ውስጥ በተለያዩ የኃላፊነት ደረጃዎች ላይ አገልገለዋል። የተቋሙን አጠቃላይ ሁኔታ በተለይም የዳይሬክቶሬቱን እንቅስቃሴ ያደረገ ቆይታ ከ አዲስ ማለዳው ዳዊት አስታጥቄ ጋር አድርገዋል።
የፌደራል ፀረ ሙስና ኮሚሽን ከተቋቀመ ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ ተቋም ነው ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ምን ለውጥ አለ ብሎ መናግር ይቻላል?
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ከሚባለውም በላይ ለውጥ መጥቷል፡፤ ተጠሩነቱን ለአስፈጻሚ አካል መሆኑ ቀርቶ ለ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሆኑ በራሱ ትልቅ ውሳኔ ንወ፡፤ ይህ ራሱን የቻለ ትልቅ ለውጥ ነው።
ኮሚሽኑ የተጣለበትን ሃላፊነት ለማወጣት በቂ የበጀት እና የሰው ሃይል አቅማ አለው ብለው ያምናሉ?
ኮሚሽኑ የበጀት ችግር የለበትም ፤ በ2013 ለጋሽ ድርጅቶችም የራሳቸውን ድርሻ እየተወጡ ነው ያሉት። ኮሚሽኑ ግን እንደ ስያሜው መጓዝ ከፈለገ ከመንግስት ድጋፍ ይፈልጋል።ኮሚሽኑ የሚገባውን ስራ እንዲሰራ ከተፈለገ ባለ ድርሻ አካላት ያስፈፃሚ አካላት ድርሻ ከፍተኛ ነው ምክንያቱም አብዛኛው ወንጀሎች የሚፈጠሩት በአስፈፃሚ አካላት ነው።
ስራው ከፍተኛ ቁርጠኝነትን የሚጠይቅ ነው።የበላይ ሃላፊዎቻቸውን መልካም ፈቃድ ለማሟላት ችግር እያለ የለም እያሉ ሪፖርት ያደርጉ ነበር። ሙስናን ለመከላከል ዝግጁ ያልሆኑ አመራሮች አሉ። በእኔ እምነት በ2013 ተቋሙ የስነ ምክባር መከታተያ ክፍሎችን ለማደራጀት ፣ ለማብቃት፣ ለመከታተል ፣ ለመርዳት ፣ እና አብሮ ስራዎችን ለመስራት ቁርጠኝነት የሌለው ሃላፊ ቦታውን መልቀቅ አለበት። በተቋሙ ወስጥ የሚመደቡ ሰዎች ሳይፈልጉ ነው የሚመደቡት። ቦታው እንዲፈለግ ማድረግ እና አመኔታ እንዲኖረው መሰራት ያስፈልጋል።
በየተቋማቱ አንዳንድ አስፈፃሚ አካላት ‹‹የስነምግባር መከታተያ ክፍሎች ቢደራጁ ተብሎ ሃሳብ ሲነሳለት ከወጪ ጋር ያያይዘዋል›› ነገር ግን የስነ ልቦና ድህንት ካልሆነ በቀር ለዚህ የሚወጣው ወጪ ሙስና በሃገሪቱ ላይ ከሚያደርሰው ኪሳራ አንጻር አዚህ ግባ የሚባል አይደለም። የስነ ምግባር መከታተያ ከፍሎችን በፌደራል መስርያ ቤቶች ውስጥ ፣ በፌደራል የልማት ድርጅቶች ውስጥ፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ ውስጥ በእያንዳንዷ ተቋም ላይ ማደራጀት የምርጫ ጉዳይ አይደለም። ምክር ቤቶች ለምን የስነ ምግባር መከታተያ ከፍሎች አይኖሩም ብለው ሲጠይቁ አይታዩም ድክመት አለ። ነገር ግን የአስፈፃሚው አካልም ከባድ ተፅዕኖ አለው።ከዚህ በፊት የአሰራር ጥናት እንሰራ ነበር እኛ ፣ የሃብት ማሳወቅን እና መከታተልን ስራ እንዲሰራው ይደረጋል። ይሄ ግን ካልተፈፀመ ከባድ ነው። መመርያው አንድ የፌደራል መስርያ ቤት ሃብት ምዝገባ በተቋም ውስጥ እንዲሰራ ማድርግ ግዴታ ጥሏል።
በአፋር ክልል፣የጋምቤላ፡ ሱማሌ ክልል እና አዲስ በተቋቋመው ሲዳማ ክልል ለምን በሃብት ማስመዝገቡ ሂደቱ አልተካተቱም?
ከጀመሩት ቆይተዋል ያው ቀድሞ ስንለው እንደነበረው ይሄ አዳጊ ክልሎች በሚለው ማለት ነው። በዛም ኮሚሽኑ የራሱን ጥረት እያደረገ ነበር ግን አልተቻለም ነበር።የአመራር ቁርጠኝነት ይጠይቃል። በነገራችን ላይ በየጊዜው የሚሾሙ የመንግስት አካላት የስነምግባር ፀረ ሙስና ኮሚሽነሮችን፣ የርዕሰ መስተዳድሩን፣ የምክር ቤቱን የአስፈፃሚውን አካል መልካም ፍቃድ ይፈልጋል ህግ ነው እና ከዚህ አኳያ ተጓቷል እንግዲህ በዚህ አመት ቃል ገብተዋል አሁን ባለፈው በነገራችን ላይ ጷግሜ ውስጥ ስብሰባ ወይንም የጋራ ውይይት ነበረን የክልልም የፌደራልም እዛ ላይ ቃል ኪዳን ገብተዋል።
በነገራችን ላይ የጋምቤላ ክልላዊ መንግስት በተመሳሳይ እንደዚህ አይነት ባህሪ ነበረበት አሁን የመጡት የክልል መስተዳድር መሰረታዊ ለውጥ አምጥተው አዋጅ ወጥቶ እንዲተገበር አድርገዋል።አሁን ሪፖርቶቻቸውን ሲያቀርቡ በግንባር ቀደምነት በመልካም የተደነቁ ክልሎች ውስጥ አንዱ የጋንቤላ ክልላዊ መንግስት ነው። ስለዚህ የክልል ርዕሰ መስተዳድር የበላዩን ድርሻ ይወስዳሉ።
ሌሎቹም በዚህ አመት የሚተገብሩት ይመስለኛል።እዚህ ላይ የሚዲያውም ትብብር ወሳኝ ነው። ምክንያቱም ለአፋር ህዝብ ሙስናን ከመከላከል አኳያ የግልፅነትና ተጠያቂነት አሰራር መዘርጋት ይገባዋል፣ ለሱማሌ ክልልም በተመሳሳይ ይገባዋል ።ለሲዳማም እንዲሁ። ስለዚህ የሚዲያውም ድርሻ ሊኖር ይገባል ብዬ አምናለሁ።
አንድ የመንግስት ባለስልጣን ሀብት ያስመዝግብ ሲባል የትኞቹን የቤተሰብ አባሎቹን ነው የሚያስመዘግበው?
እንግዲህ በሀብት ማሳወቅና ማስመዝገብ አዋጅ ቁጥር 668/2002 አንቀፅ 4 መሰረት ማንኛውም የህዝብ ተመራጭ፣ የመንግስት ተሿሚ እና የመንግስት ሰራተኛ የራሱ እና የቤተሰቦቹን በተለይም የትዳር ጓደኛውን 18 አመት በታች የሆኑ ልጆቹን ጉዲ ፈቻ ልጁን ጨምሮ ሀብት እና የገቢ ምንጩን ያስመዘግባሉ ይላል።
ከዚህ ውስጥ ምንድን ነው የሚመዘገበው ከተባለ ሀብትን በተመለከተ በእኛ የፍትሃብሄር ህግ በግልፅ ተቀምጧል ።ሀብት የተባሉት የሚንቀሳቀስ፣ የማይንቀሳቀስ እዳን እና ቁጠባን ይጨምራል ። የማይን ቁሳቁስ ደግሞ ማንኛውም መሬት ላይ ያለ ነገር በሙሉ የሳር ጎጆ ቤትም ቢሆን ይካተታል ስለዚህ በየትኛውም መሬት ላይ ያረፈ ቤት ባዶ ቦታን ጨምሮ ይመዘገባል።
የእርሻ ይዞታ ካለ ይመዘገባል፣ ከኢቨስትመንት ስራ ጋር ትስስር ያለው መረጃ ሁሉ ይመዘገባል። ተንቀሳቃሽ ተሸከርካሪ ያሉ ጉዳዮች ሁሉ ከሞተር ሳይክል ጀምሮ ሙሉ መረጃን አካቶ ይመዘገባል፣ እንስሳትም ይመዘገባሉ፣ ጌጣጌጦችም እንደ አልማዝ እና እንቁ በማንኛውም መጠን፣ ወርቅ ከ50 ግራም በላይ ከሆነ ይመዘገባል፣ ከእድል ሎተሪ ከተገኘም፣ ይመዘገባል።አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ያልተገባ ሀብት ያፈሩና እዚህ አገር ያለው እከሌ ነው የላከልኝ በማለት ለማጣጣል ይሞክራል ስለዚህ የላከልህን አሳውቅ፤ አንደኛ የሚላከው ብር በመንግስት የፋይናንስ ተቋማት ስር ማለፍ አለበት። የትኛውም ባንክ ውስጥ ማለፍ አለበት።ካልሆን እንደ ጥቁር ገበያ ነው የሚቆጠረው። አሁን ካለው ሁኔታ ጋር ተያይዞ ያለው አንዱ ችግር ይሄ ነው።
ሌላው እዳ ይመዘገባል ባለእዳ ሲበደር የሆነ ንብረት አስይዞ ነው።ስለዚህ እዳም እንደ ሀብት ይቆጠራል። በዚሁ አግባብ ደግሞ የማይመዘገቡ አሉ ለምሳሌ አንደኛው የተወረሰ ሀብት ሆኖለወራሹ ያልተከፋፈለ ከሆነ አይመዘገብም፣ በቅንጦት እቃነት የማይፈረጁ መሰረታዊ የቤት ቁሳቁሶች አይመዘገቡም። ይህም ማለት አሁን ለምሳሌ ማንኪያ አይመዘገብም የወርቅ ካልሆነ በስተቀር።ማንኪያ ከሆነ ይመዘገባል ብቻ አንድ ባለስልጣን ሀብት አስመዝግብ ሲባል የሚያስመዘግበው የእርሱን፣ የባለቤቱንና የልጆቹን ብቻ ነው። ነገር ግን ያለውን ሀብት በወንድሙ ፣ በእናቱ ስም በአባቱ ስም ሊያደርግ ይችላል ለማን እነደዚህ ተወሰነ በነገራችን ላይ በእኛ እምነት ይሄ ሀሳብም ሊሆን ይችላል። አንድ የመንግስት ባለስልጠን በራሱ ሀብት አያስመዘግብም ቅርብ በሆነ ዘመድ ወይም ወዳጅ ነው የሚያስመዘግበው የሚል ሊኖር ይችላል። ግን ይሄን በሁለት መልኩ ልመልሰው አንደኛው ዛሬ አለመተማመን በጣም ጎልቶ የወጣበት አግባብ ነው ያለው አይደለም በወዳጅ ዘመድ በቤተሰብ ውስጥ እንኳን መተማመን እየጎደለ ነው ያለው።
ቢያስቀምጥ እንኳን ሰውየው ሰላም የለውም። ጠዋትና ማታ ሰው ስለአገር፣ ስለቤተሰብ ስለሰላም ሲያስብ እርሱ ስላከፋፈለው ሀብት ነው የሚያስበው። ስለዚህ ሊኖር ይችላል ግን አሁን ካለው ሁኔታ አንፃር ዋና ሙሰኞች በሌሎች አካላት ሀብታቸውን አያፈሩም ብዬ ባልከራከርም ግን ሀብትን በሌላ አካል ማስመዝገብ፣ የቁጠባ ሂሳብ መክፈት፣ መኪና መግዛት፣ ቤት መስራት፣ አክሲዎን መግዛት እና ሌሎችም ሊኖሩ ይችላሉ ግን ቁጥሩ አነስተኛ ነው ብዬ ልውሰደው። ምክንያቱም ስጋት ነው በራሱ።
ሌላው ሃብትያፍራ ችግር የለውም አንድ መታወቅ ያለበት ነገርግን ቅድም ያልኩት ይመዘገባል ከዚያም የተመዘገበው ይረጋገጣል። ሲረጋገጥ በሁለት መንገድ ነው የሚረጋገጠው ።አንዱ ኮሚሽኑ እራሱ ከጠረጠረ ሲሆን ሁለተኛው ይሄ ባለስልጣን ከየት ተነስቶ የት እንደመጣ ይታወቃል ከህዝብ አይንና ጆሮ የተለየ አይደለም ህብረተሰቡ ምን አይነት እንግዳ የሆነ ሀብት እንደሚያንቀሳቅስ ያውቃል። ስለዚህ የህብረተሰቡ አይንና ጆሮ ወሳኝ ነው ጥቆማ ካቀረቡ ኮሚሽኑ ጥቆማውን ተቀብሎ አረጋግጦ የተረጋገጠው ሀብት የሰውየው አለመሆኑን በፍርድቤት ከተረጋገጠ ለጠቋሚው 25 በመቶ ይከፈላል ይላል ህጉ።
በነገራችን ላይ በእኛ አገር ወንጀለኛን መጠቆም ህጋዊ፣ የሞራል የዜግነት ግዴታ ነው። የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ኤጀንሲ ግን ከዚህ ለየት አድርጎታል ለአግባብ ሀብት ያፈሩ አብዝተው የደበቁትን ጠቁመው ፍርድ ቤት ቀርበው ማስረዳት ካልቻሉ ምንጩ እንዳልታወቀ ሀብት ይቆጠርና ከተወረሰው ሀብት ላይ 25 በመቶ ያገኛል ነው የሚለው። ስለዚህ በዚህ አካሄድ ከተሰራበት ያዳክመዋል።
አሁን ኮሚሽኑ በውስጡ ጠንካራ ባለሙያዎችን እንደሚያደራጅና በክህሎትም በእውቀትም እንደሚያሰለጥነው ሁሉ በሀብት አስመዝጋቢ ተቋማት በሁሉም የመንግስት ተቋማት የሚሰሩ የስነምግባር መከታተያ ክፍሎችንም የዛኑ ያህል ማብቃትና ማደራጀት ያስፈልገዋል። እኛ በከፊልም ቢሆን ትግሉን ልንመራ ነው የሚገባው አሁን ምንድን ነው እያደረግን ያለነው ጥቆማዎች በመንግስት ሰራተኞች እንዲሰጥ የስነምግባር መከታተያ ክፍሎች እንዲደራጁ ያደረግንበት አግባብ ሰፊ ነው። ስለዚህ ከህዝብ አይን እና ጆሮ የሚደበቅ አንዳችም ነገር የለም። ስለዚህ ህዝቡ እንዲነሳሳ በቁጭት በፀረ ሙስና ትግሉ ላይ እንዲሳተፍ ካደረግን ይሄ አጀንዳ አይሆንም።
ከዚህ አናጻር የሌሎች አገሮች ልምድ ምን ያሳያል?
የሌሎች አገሮች ልምድ እንደኛ አገር የመረጃ ስርአታቸው ደካማ አይደለም ጠንካራ ነው። ለምሳሌ ኢንዶኔዢያን እንውሰድ ኢንዶኔዢያ ከ270 ሚሊየን በላይ ህዝብ ያላት አገር ናት። ተመሳሳይ የሙስና መከላከል ስርአት ነው የምንከተለው። ነገርግን እነሱ ጋር የመረጃ አሰባሰብ ስርአታቸው ጠንካራ ነው። ማንኛውን ዜጋ ከየትኛውም ጥግ ሆኖ ኮሚሽኑን ያገኘዋል መጠቆም ካለበትም በማህበራዊ ድህረገጽ ተጠቅሞ ይጠቁማል።
የሚፈልገውንም መረጃ ይወስዳል። ስለዚህ የእኛ አገር አሰራር በቴክኖሎጂ አልዳበረም። ስለዚህ የአገራችን ወጣት ቁጥር እጅግ ከፍተኛ ነው። ማህበራዊ ድህረገፆችን ተጠቅመን ልንደርሰው ይገባል እንጂ እንደ ድሮው አካሄድ ና መስክር ፈርም ፎርም ሙላ ብንለው ከባድ ነው። የሚሆነው እናም በቴክኖሎጂ አለመደገፉ የራሱን ጫና ፈጥሯል። አሁን ኮሚሽናችን በዚህ አመት ካቀደው እቅድ ውስጥ ቴክኖሎጂን በስፋት መጠቀም ማህበራዊ ድህረገፅን ማስፋፋት ይገኝበታል። የሀብት ማሳወቅ እና ምዝገባ ስርአት በነገራችን ላይ በቴክኖሎጂ ተደግፏል። ለምሳሌ የመዘገብኩትን ልልቀቅ ይላል እራሱ ሲስተሙ፣ ዜጎችን በኢሜል መረጃ ልቀበል መረጃ ልስጥ ይላል፣ ስለዚህ የህግ ድጋፍ ይፈልጋል።
ስለዚህ ቴክኖሎጂው ትንሽ አልተሰራበትም። አሁን ህዝቡ ሙስናን ተፀይፏል። ማንም ሙስናን አይፈልግም ምክንያቱም ቤተሰብን ያፈርሳል፣ ምሁራንን ዝቅ ያደርጋል፣ ቤተሰብ ሲታሰር ልጆች ስነ ልቦናዊ ጫና ይደርስባቸዋል እና ሙሰኛው ከመቀጣቱም ባለፈ በትውልድ ላይ የሚጭነው ጫና ከፍተኛ ነው። ስለዚህ አሁን ከወጣቱ የሚደበቅ ነገር የለም። ያነባል ለመረጃም ቅርብ ነው። ለመጠቆምም ቅድመ ሁኔታ አያስቀምትም ።አሁን የተቸገርነው እኮ ነባሩ ቅድመ ሁኔታ ያስቀምጣል ወዳጄን፣ አጎቴን፣ በስራ ያገኘሁትን ሰው እንዳላስቀይመው እያለ ትስስር ውስጥ ይገባል ወጣቱ ግን ከዚህ አይነት አስተሳሰብ ወጥቷል ነፃ ነው።
አንድ ነገር ነው። የሚታየው እርሱም ኢትዮጵያ ውስጥ ግልፅነት እና ተጠያቂነት ልንገነባ ይገባል። ስለዚህ እኔም የበኩላን ድርሻ ልወጣ የሚል ነው። ጥቆማን በተመለከተ በነገራችን ላይ ጠንካራ ህግ አለን የወንጀል ምስክሮችና የጠቋሚዎች ጥበቃዎች 699/2010 ጠንካራ ነው። የተለያዩ ጠንካራ ጥበቃዎች ይረጉለታል ይላል ግን አልተሰራበትም።
የብሄራዊ መታወቂያ ሙስናን ከመዋጋት አንፃር ምን ፋይዳ አለው
የብሄራዊ መታወቂያ ማለት እኮ ማንኛውም ሰው የትም ቢሄድ የሚታወቅበት፣ ወንጀል ብትሰራ እንኳን ተከታትሎህ የሚሄድ ነው። ስለዚህ በተለያዩ ቦታዎች የተለያየ ማንነት እንዳይኖርህ ያደርጋል።አሁን የተወሰነ መረጃ ነው ወደሲስተም የገባው ለምሳሌ ሀብት ያለው መኪና ያለው ነው ወደ ሲስተም የገባው የብዙ ዜጋ መረጃ እኮ ገና ነው ፣አቅርቦቱ አልተሟላም።
የተወሰነ መረጃ ነው ወደ ሲስተም የገባው። የብዙ ሰዎች መረጃ ገና ሪሶርስ አልተሟላም። ለምሳሌ በኢትዮጲያ ሰባት ቤት ያለው ሰው ሰባቱም ቤት በአንድ ኮድ ስር ነው የሚዘጋጀው፣ እሱ ጥሩ ነው።
ኮሚሽኑ የመክሰስ ስራውን ለፌደራል ፖሊስ አሳልፎ መስጠቱ ኮሚሽኑን ጥርስ አልባ ያደርገዋል የሚሉ አሉ የርሶዎ ሀሳብ እዚህ ላይ ምንድን ነው?
ነገሩ ሰዎች እንደሚሉት ጥርስ አልባ ሆኖ አይደለም ነገር ግን ቆምብሎ በማስተዋል ነገሮችን ከመረጃ ጋር ማያያዝ ያስፍልጋል።
የሙስና ወንጅል ሲሰራ በግልፅ የሚታይ አይደለም የሙስና ወንጀል በግልጽ የሚታይ አይደል በጣም ውስብስብ እና ረቂቅ ነው። በየጊዜው ህግ ቢወጣ እንኳን ህጎችን በመጣስ ወይም ከህግ ስር እስከ መሽሎክሎ የሚደርስ ነው።ስለዚህ በብልሹ አሰራር ላይ በጥናት ያልተመሰረት ክስ ወይም ምርመራ እስከምንደረስ ሊሄድ ነው ወይ ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል።
በሰዎች ወይም በተቋማት ጥርጣሬ ሳይገኝ ወይም ጥቆማ ሳይደረግስ የሚደረግ ምርመራ እስከምን የሚያስኬድ ነው? አሁን እኮ የይቅርታ ዘመን ነው ተብሎ አይደል ? የይቅርታ ዘመን ከሆነ እኮ ሰዎችን በድንገት ተነስተው መታሰር የለባቸውም ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩም ቢሆኑ ሳናጣራ አናስርም ማለታቸውን በጣም ነው የማመሰግናቸው ከመሪ እንደዚህ አይነት ቋንቋ ሲወጣ ደስ የሚል ነው ሃሳቡ በራሱ ገዢ ነው። በአሰራር በኩል ግን ጉድለት ሊኖር ይችላል ።
ዋናው ነገር ማጣራት ነው ማጣራት ማለት እኮ የተለየ ነገር አይደለም በመረጃ ላይ መመስረት ነው።
እንደ ዲሞክራሲ ተቋም ባለሙያነቴም የምርመራ ምዝገባ እና የብልሹ አሠራር ጥናት አይለያዩም ስለሆነም በመጀመሪያ ጥናት ማድረግ በመቀጠል ክፍተት ከተገኘ ወደ ምርመራ መሄድ ነው እንጂ ዝም ብሎ ፋይል መሰብሰብ ብቻ ነው።
ኮሚሽኑ በራሱ እና በውጭ አቅም ጥናቶችን አስጠንቶ ወደ ምርመራ የማይላኩ እና ግብዓት የማይሆኑ ከሆነ ለምን ወጭስ ይወጣል? አንዳንዱ እንደ መስፈራሪያም ያያዋል።የሙስና ወንጀል ምርመራ ልዩ ትኩረት ያስፍልገዋል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ሚዲያውም ነገሩን ወጥረው መያዝ አለባቸው።፡
በአጠቃላይ ግን ማንም ይስራው ማን የጋራ ውጤት እናስመዘግባለን ከተባለ መረጃ ላይ መመስረት ያፈልጋል።እንደመፍት ግን ከሙስና ጋር በተያያዘ ማስተማር፣ መካላከል፣ መመርመር እና መክሰስ የሚለውን ሂደት በማስኬድ በአንድ ቢመሩ ተመጋጋቢ ናቸው።
በመግስት ሃላፊነት ሆነው ሃሳብን አለማስመዝገብ ገቢን አለማሳወቅ እንደ ሙስና ወንጅል ይቆጠራል።
በእኛ በኩል አንድ የመንግስት ባለስልጣን ሃበቱን ሳያስመዘገብ ቀርቶ ተጠያቂ መሆኑ ሊታሰበብበት ይገባል
ኮሚሽኑ ሀብታቸውን የላስመዘገቡ ባለስልጣናትን ስም ዝርዝር ለፌደራል ፖሊስና ለጠቅላይ አቃቢ ህግ ልኳል የመጨረሻ ውጤት ምንድንው የሚሆነው?
እንግዲህ በአዋጁ መሰረት ሀብት ለማስመዝገብ የተጠየቀ የመንግስት ባለስልጣን ህጉን እንደጣሰ ተቆጥሮ በሙስና ወንጀል ይጠየቃል ይላል። ከዚያ በፊት በተራዘመለት ጊዜ ካላስመዘገበ 1 ሺህ ብር ይቀጣል ይላል። አሁን 184 ባለስልጣናት የሚጠየቁት በሙስና ወንጀል ነው የሚሆነው እሱ የፍትህ አካላት ስራ ነው። የፍተህ አካላት ተጠያቂነትን ከማስፈጸም አንፃር ትኩረት ሊሰጥ ይገባል። ባለስልጣን ተብሎ ህግን ለማስከበር ተቀምጦ ህግን ካላከበረ አንደት ህግ ያስከብራል የሚለው መታየት አለበት። የኮሚሽኑ ድርሻ በተደጋጋሚ ጠይቋል ነገር ግን ኮሚሽኑ ፈቃደኛ ያልሆኑትን አሳልፎ ከሰጠ የፍትህ ተቋማት በፍጥነት ለምን አያስፈጽሙም የሚለውን ህዝቡ መጠየቅ አለበት።
በመጨረሻ ማለት የሚፈልጉት ካለ እድሉን ልስጥዎት?
ማለት የምፈልገው በ2013 በጀት ዓመት ማንኛውም የመንግሰት ሰራተኛ አዲስ ተቀጣሪ ይሁን ተሿሚ እንዲሁም የህዝብ ተመራጭ ሀብቱን የማስመዝገብ ግደታ አለበት። ሌላው አሁንም በ2013 በጀት ዓመት ማንኛውም የመንገስት ሰራተኛ ከሚሰራው ስራ ጋር የጥቅም ግጭት የሚፈጥር የግል ስራ መስራት አይችልም። ምክንያቱን ህጉን ለራሱ በሚመች መልኩ ለመራው ችላል ተብሎ ስለሚታሰብ ነው።
ቅጽ 2 ቁጥር 98 መስከረም 9 2013



