የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ መስከረም 12/2013 እያካሄደው ባለው በ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ አስቸኳይ ስብሰባ በጠቅለይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) የቀረቡትን የሚኒስትሮች ሹመት አጽድቋል፡፡
-
ቀነዓ ያዴታ (ዶ/ር) የኢፌዴሪ የሀገር መከላከያ ሚኒስትር
2. ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ
3. ሳሙኤል ሁርቃቶ (ዶ/ር) የኢፌዴሪ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር
4. ታከለ ኡማ (ኢ/ር) የኢፌደሪ ማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር
በዚህ መሠረትም ምክር ቤቱ የቀረበውን ሹመት በአምስት ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል፡፡
በተጨማሪም ምክር ቤቱ የ40 የከፍተኛ ፍርድ ቤት እጩ ዳኞችን ሹመት በ5 ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምፅ እንዲሁም የ50 የመጀመሪያ ፍርድ ቤት እጩ ዳኞችን ሹመት ደግሞ በ3 ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል፡፡
እጩ ዳኞቹም በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት መዓዛ አሸናፊ አማካኝነት በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለመሃላ መፈፀማቸውን ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡



