ትምህርት ሚኒስቴር ኹለት የግል ትምህርት ቤቶችን አገደ

0
1263

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ ትምህርት ሚኒስቴር ያወጣውን የክፍያ መመሪያ ተላልፈው የተገኙ ኹለት የግል ትምህርት ቤቶች ለግዜው መታገዳቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

 

እገዳው የተላለፈባቸው ትምህርት ቤቶች አንድነት ኢንተርናሽናል እና ሄሌኒክ-ግሪክ ማሕበረሰብ ትምህርት ቤት ናቸው፡፡

 

በትምህርት ቤቶቹ ላይ ውሳኔ የተላለፈው ትምህርት ቤቶቹ የተቀመጠውን መመሪያ ተግባራዊ ባለማድረጋቸው የወላጅ ኮሚቴዎች ተደጋጋሚ አቤቱታ በማቅረባቸው እንደሆነ ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

 

ከዛሬ ጀምሮ መንግስት ( ትምህርት ሚኒስቴር) ያወጣውን መመሪያ ከወላጅ ኮሚቴ ጋር በመነጋገር ፈጥኖ ሪፖርት እስኪያደርጉ ድረስ ትምህርት ቤቶቹ ምንም አይነት የትምህርት ስራ እንዳይሰሩ መታገዳቸውም  ተገልጿል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here