በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ አምስት ዞኖችና አንድ ልዩ ወረዳ ክልል ለመመስረት ያቀረቡት ጥያቄ ጸደቀ

0
595

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኙ አምስት ዞኖችና አንድ ልዩ ወረዳ በጋራ አንድ ክልል ለመመስረት ቀደም ሲል ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ጥያቄ አቅርበው እንደነበር ተገልጿል።

በዚህም መሰረት ምክር ቤቱ ውይይት ካደረገ በኋላ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስፈጻሚነት ሕዝበ ውሳኔ እንዲደራጅ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ በሙሉ ድምጽ ማጽደቁን ኢዜአ ዘግቧል።

ጥያቄውን ያቀረቡት የከፋ፣ ቤንች፣ ሸኮ ፣ምዕራብ ኦሞ፣ ዳውሮ፣ ሸካ ዞኖችና የኮንታ ልዩ ወረዳ ናቸው ተብሏል።

ዞኖቹ ተቀራራቢ ቋንቋ፣ ባሕል፣ ታሪክና መልካምድራዊ አቀማመጥ ስላለን አንድ ላይ ብንሆን የተሻለ ነው በማለት ጥያቄ አቅርበው እንደነበር ዘገባው አስታውሷል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here