ኮሚሽኑ የ10 ዓመት መሪ የልማት ዕቅዱ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን ገለጸ

0
336

የኢፌዴሪ ኘላንና ልማት ኮሚሽን ከተጠሪ ተቋማቱ (የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ እና የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲቲዩት) ጋር በመሆን የ2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸሙን የተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በመግለጫውም ከዋና ዋና ተግባራት መካከል በኮሚሽኑ የተዘጋጀው የረጅም እና የመካከለኛ ጊዜ ሀገራዊ የልማት ዕቅድ ዝግጅት ከወትሮው ለየት ባለ ተሳትፎ መዘጋጀቱ ተመላክቷል፡፡ በተለይም የ10 ዓመት መሪ የልማት ዕቅዱ በመጠናቀቅ ላይ መገኘቱ መልካም የተግባር ጅምር መሆኑን ነው ኮሚሽነሯ ፍፁም አሰፋ (ዶክተር) ያስታወቁት፡፡

የመንግሥት የልማት ፕሮጀክቶችን አፈፃፀም ሐሳብ ከማመንጨት ጀምሮ በዕውቀት ለመምራት የሚያስችል አዋጅ ጸድቋል፡፡ በሀብት አጠቃቀም፣ በጥራት እና በመፈጸሚያ ጊዜ ክፍተት ይታይ የነበረውን የልማት ፕሮጀክቶች አስተዳደር ሥርዓት በእጅጉ ሊቀይር በሚችል ዝርዝር መዘጋጀቱም በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡

ኮሚሽኑም አደረጃጀቱን በማሻሻል ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር ሥራውን በማስጀመር ሂደት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ በሀገራዊ የልማት ዕቅዱ ውስጥ የክልሎችን የልማት አቅም በየኢኮኖሚ ዘርፉ በመዳሰስ በሀገር ደረጃ አንድ የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ ለመፍጠር መካተት የሚገባቸውን ዝርዝሮች ያካተተ ጥናትም ተሠርቷል፡፡

የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲቲዩት በሩብ ዓመቱ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በመረጃ ላይ የተመሠረተ ለፖሊሲ ዝግጅት ግብዓት የሚሆኑ ጥናቶችን መሥራቱም ተመላክቷል፡፡

ኮሚሽኑ ከተጠሪ ተቋማቱ ጋር ከሚሠራቸው ሰፋፊ ሥራዎች ጎን ለጎንም የተለያዩ ጥናቶችን እና ትንበያዎችን በማከናወን ለፖሊሲ ውሳኔ የሚያግዙና የሚቀናጁ ሥራዎችን በጋራ በማቀድ በትብብር እየሠራ እንደሆነም አስታውቀዋል፡፡

የአረንጓዴ አሻራ አካል በሆነው የችግኝ ተከላና የተተከሉትን የመንከባከብ ተግባር፤ በሸገር እና እንጦጦ ፓርክ ተሞክሮዎችን ወደተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የማስፋፋት ተልዕኮ አካል በሆነው ገበታ ለአገር ፕሮግራም ላይ መላው ሠራተኛ የአንድ ወር ደመወዙን መለገሱም በሩብ ዓመቱ ከተከናወኑ ተግባራት መካከል መሆናቸው በመግለጫው ተካትቷል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here