ፌስ ቡክ በኢትዮጵያ  ምርቶችን መሸጥ እና መግዛት የሚያስችል የፌስ ቡክ መገበያያ መድረክ ጀመረ

0
863

የፌስ ቡክ ኩባንያ  የግብይት መድረክ ኢትዮጵያውያን የሚፈልጓቸውን ምርቶች በቀላሉ በፌስ ቡክ ገጻቸው አማካኝነት መግዛት እና መሸጥ የሚያስችል መገበያያ መድረክ አዘጋጀ።

በኢትዮጵያም አገልግሎቱ ከዚህ ወር መጨረሻ ጀምሮ በሂደት  ተደራሽ የሚሆን እና እስከ  ሕዳር ወር መጨረሻ  ድረስ  ግን  ሙሉ ለሙሉ እንደሚጀመር ታውቋል።

የአገልግሎቱን መጀመር አስመልክቶ የፌስ ቡክ የምስራቅ አፍሪካ እና የአፍሪካ ቀንድ የሕዝብ ፖሊሲ ዋና ኃላፊ የሆኑት ሜርሲ ንድግዋ  ‹‹በኢትዮጵያ እያደገ የመጣውን የኤሌክትሮኒክ ግብይትን የሚያግዝ የፌስ ቡክ መገበያያ መድረክ በማስጀመራችን ደስታ ይሰማናል፣ የፌስ ቡክ ገጽን በመጠቀም ኢትዮጵያውያን የተወሰነ ግብይት እያከናወኑ እንደሆነ ስለምናውቅ የፌስ ቡክ ኩባንያም ደህንነቱ እና አስተማማኝነቱ የተጠበቀ አዲስ የግብይት መተግበሪያ ለኢትዮጵያውያን ማቅረቡ ትልቅ ስኬት ነው›› ብለዋል።

በአዲሱ የፌስ ቡክ መተግበሪያ ምርቶችን ለመግዛትም  በግብይት መተግበሪያው ላይ ያለውን የግብይት መድረክ ቁልፉን በመጫን ወይም የፊስ ቡክ ግብይት ድህረ ገጽን በመጎብኘት የሚፈልጉትን የዕቃ ዓይነት ከዝርዝሮቹ መኻል በዓይነትም ሆነ በቦታ መምረጥ እንደሚቻል ኩባንያው ለአዲስ ማለዳ በላከው መግለጫ ላይ አስታውቋል።

ዝርዝር ተጨማሪ  መረጃ ማግኘት ከፈለጉም ከታች የሚገኘውን የመግለጫውን ዝርዝር ጉዳይ መመልከት  ትችላላቸሁ።

ላላው አማራጭም የሚፈልጉትን የምርት ዓይነት በቀጥታ ገብተው መጻፍ ይችላሉ፡፡
የግብይት ቁልፉን ሲጫኑ ተጨማሪ ዝርዝሮችን የሚያሳይ ሲሆን በሜሴንጀር አማካኝነትም መልእክቶችን ለሻጮች መተው ያስችላል፡፡

በተጨማሪም የሻጩን አጭር ግለ -ታሪክ(Profile) በመጫን ስለ ሻጩ መረጃ ማግኘት እና የሽያጭ ደረጃ ድልድሉን( Rating )ማየት የሚያስችል ሆኖ ግዢና ሻጮች ስለ ክፍያ እና ለሎች ዝርዝር ሁኔታውን መረጃ የሚለዋወጡበት መድረክ ነው ፡፡

ስለግብይት መተግበሪያው አሰራር ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ከታች ያለውን ድህረ,-ገጽ ይጎብኙ መጎብኘት ይችላሉ፡፡.

https://www.facebook.com/marketplace/learn-more/buying
በፌስ ቡክ መተግበሪያ እንዴት መሸጥ ይቻላል ?

በፌስ ቡክ ግብይት መተግበሪያ መድረክ መሸጥ ቀላል ነው፡፡ሻጩ የሚሸጣቸውን እቃዎች ዝርዝር ሲለጥፍ ፌስ ቡክ ገጽ ላይ ለሁሉም ግልጽ ሆኖ በግብይት መድረክ፡በኒውስ ፊድ፣በፌስ ቡክ ሰርች፣በፌስ ቡክ ግሩፕ፣በሰርች ኤንጅን ይታያል፡፡ ሻጮች ለመሸጥ የሚፈልጉትን እቃዎች አባል በሆኑባቸው የፌስ ቡክ ግሩፕ ላይም መለጠፍ ይችላሉ፡፡

ሻጮች የሚሸጧቸውን እቃዎች ፎቶ በማንሳት ወይም ከፎቶ ስብስባቸው ውስጥ በመምረጥ ፣የእቃውን ዓይነት እና ዝርዝር ሁኔታ፣ዋጋ በመለጠፍ እና እቃው የሚገኝበትን ቦታ በማሳወቅ የፌስ ቡክ ገጻቸው ላይ መለጠፍ ይችላል፡፡ ከዚያም መግዛትም ሆነ መሸጥ የሚፈልግ ማንኛውም ሰው መልእክት በመተው ለመገበያየት ይችላሉ፡፡ በግብይት መድረኩ ምን ያህል የንግድ ልውውጥ እንደተከናወነ ሻጩ ማየት የሚችልነት እድልም በ “Your Items” section.( በእቃዎ ዝርዝር ክፍል) ቁልፍ አማካኝነት ማግኘት ይቻላል፡፡በተጨማሪም ከዚህ በፊት ለሽያጭ የቀረቡት እና የአሁኖቹን እቃዎችን ጨምሮ፣ሲለዋወጧችው የነበሩ መልእክቶችንም የማየት እድል የሚሰጥ ነው፡፡

ለመሸጥ የሚፈልጉ ከሆነ በፌስ ቡክ የግብይት መተግበሪያ መድረክ ደረጃ በደረጃ የሚገበያዩበትን አካሄድ ከፌስ ቡክ መረጃ ማእከል ማግኘት ይቻላል፡፡

ዝርዝሮቹን በሚለጥፉበት ወቅት ካሉት የተለያዩ ምድቦች ውስጥ ለይቶ በትክክል ማስቀመጣችንን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡

ይህም ሰዎች ምርቱን በቀላሉ ለማግኘት ያስችላቸዋል፡፡
የእቃዎቹን ዋጋ በሚለጥፉበት ወቅት የእቃውን እውነተኛ ዋጋ ማወቅ እና አሁናዊውን የእቃውን ይዞታ መገንዘብ እና ተወዳዳሪ ሂሳብ መለጠፍዎን እንዳለቦት ይመከራል፡፡

የሚለጥፉት ዋጋ “OBO”, which stands for “Or Best Offer”,የተሻለ ፣ ምርጥ አማራጭ ሆኖ በመቅረብ ገዢውን መሳብ እና ለመደራደር የሚጋብዝ እንዲሆን ይገባል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here