‹‹ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተገናኘ በፌዴራል ደረጃ በ114 መዝገቦች ከ3 ሺ በላይ ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ተመስርቷል›› ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ

0
874

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ፤ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተገናኘ በተለያዩ ቦታዎች በተፈጠረው ሁከት በሰው እና በንብረት ላይ የደረሰውን ጉዳት በኹለት  ወር ውስጥ በቅንጅት የምርመራ ሥራ በማከናወን በፌዴራል ደረጃ በ114 መዝገቦች ከ3 ሺ በላይ ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ መመስረቱን አስታወቀ።

 

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የ2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት በእቅድ ዝግጅት ምዕራፍ፣ ሕግን ከማስከበር እና የወንጀል ህጉን ከማስፈጸም እንዲሁም የሕግ ማዕቀፎችን አስመለክቶ በተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

 

በመግለጫው ላይም ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር )  ወደ ዐቃቤ ሕግ ከተመሩ መዝገቦች መካከል በፍርድ ቤት ክርክር እየተደረገባቸው ያሉ 33,714 መዝገቦች ላይ በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ክርክር የተደረገ  መሆኑን ጠቅሰዋል።

 

በሦስት  ወራት ውስጥ የመጨረሻ የፍርድ ቤት ውሳኔ ያገኙ 2480 መዝገቦች ሲሆኑ ከዚህ ውስጥ በ2371 መዛግብት ላይ ተከሳሾቹ የጥፋተኛነት ውሳኔ የተሰጠባቸው መሆኑን የተናገሩት ጢሞቲዎስ፤ቀሪዎች ተከሳሾች ደግሞ በነጻ እንደተሰናበቱ ጠቁመዋል፡፡

 

ከዚህ በተጫማሪም የኢኮኖሚ ወንጀሎች በተመለከተ ጥፋተኛ ተብለው የተያዙ ሰዎችን በፍርድ ውሳኔ መሰረት ማስቀጣት ብቻ ሳይሆን በወንጀል ስራቸው ያገኙትን ሀብት ይዘው እንዳይቀጥሉ በማድረግ ሀብት የማስመለስ ተግባር ላይ አትኩሮ የሚሰራ የስራ ክፍል በአዲስ መልክ መደራጀቱን ጢሞቲዎስ አስታውቀዋል።

 

በመሆኑም  የሥራ ክፍሉ በሠራው ሥራ 412 ሚሊዩን ብር የሚገመት ገንዘብ ወደ መንግስት ለማስመልስ በሂደት ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡

መረጃው የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ነው

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here