በኢትዮጵያ በኮቪድ 19 ምክንያት ሕይወታቸው ካለፈ ዜጎች 28 በመቶው የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ሕሙማን እንደሆኑ የፌዴራል ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።
ጽሕፈት ቤቱ ይህ የሆነው ሕሙማኑ መድኃኒታቸውን በማቋረጣቸው ነው ብሏል። የጽሕፈት ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ፅጌርዳ ክፍሌ እንዳሉት፣ መገናኛ ብዙኀን አብዛኛውን ጊዜያቸውን ለኮቪድ -19 መስጠታቸው ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ እንዲዘነጋ ምክንያት ሆኗል ብለዋል።
አያይዘውም ሁሉም መገናኛ ብዙኀን ኹለቱንም ቫይረሶች በሚመለከት በተመጣጣነ መልኩ ሽፋን እንዲሰጡ አሳስበዋል። የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ሕሙማንም መድኃኒታቸውን በአግባቡ እንዲወስዱ ያሳሰቡ ሲሆን፣ የሕክምና ተቋማትም ችግሩን በደንብ እንዲያጤኑትም መጠየቃቸውን ኢትዮ ኤፍ.ኤም ዘግቧል።
ቅጽ 2 ቁጥር 102 ጥቅምት 7 2013



