በአዲስ አበባ ዘመናዊ ቤቶችን የመገጣጠም ሥራ በመጪዎቹ ወራት ይጀመራል ተባለ

0
335

በአዲስ አበባ ከተማ ዘመናዊ መኖረያ ቤቶችን የመገጣጠም ስራ በቅርቡ እንደሚጀመር የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር አስታወቀ።
የመኖሪያ ቤቶቹን ለመገንባት በቅርቡ የመሰረተ ድንጋይ የተቀመጠ ሲሆን አሁን ላይ ደግሞ ቤቶቹ የሚገጣጠሙበት ቦታ የማጽዳትና የማመቻቸት ሥራ እየተካሄደ መሆኑ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ዴኤታ መስፍን አሰፋ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው መስፍን እንደገለጹት ከሆነመ የቤቶቹ መገጣጠም ሥራ በመጪው ህዳርና ታህሳስ ወራት ውስጥ ይጀመራል ብለዋል።
የቤቶቹ አሰራር የአገሪቱን የቤቶች ልማት ወደ ዘመናዊነት የሚቀይር ከመሆኑን ባለፈ ግንባታው የሚፈጀው ጊዜ፣ወጪና የዜጎችን የመኖሪያ ቤት ፍላጎት በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመመለስ የሚያስችል መሆኑን ሚኒስቴር ዴኤታው አስታውቀዋል ።

በተጨማሪም ሥራውን በተቋራጭነት ከወሰዱት ድርጅቶች ጋር በመነጋገር አዳዲስ የቤቶች ልማት ቴክኖሎጂን ወደ ክልል ከተሞች ለማስፋፋት ልምድ እንዲወሰድበት የመገጣጠሚያ ሂደቱ ክፍት እንደሚሆን መስፍን አስረድተዋል።

በቀጣይም በአሥር ዓመታት ውስጥ አምስት ሚሊዮን ቤቶችን ለመገንባት መታቀዱንም ገልጸዋል።
እንዲሁም በአዲስ አበባ የሚካሄደው ዘመናዊ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ቴክኖሎጂ በሁሉም ከተሞች ለማስፋፋት ስትራቴጂ ተቀርፆ ወደ ተግባር መገባቱን ሚኒስቴር ዴኤታው ጠቁመዋል ሲል የዘገበው ዋልታ ኢንፎርሜሽን ነው።

ቅጽ 2 ቁጥር 102 ጥቅምት 7 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here