የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ክፍለ ከተሞችን እና ወረዳዎችን እንደገና ሊቋቋሙ ነው

0
1181

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን በዛሬው ዕለት ጥቅምት10/2013 ስምንተና ኛ ዓመት 1ኛው መደበኛ ጉባኤ የአስፈጻሚ አካላት የ2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ይገመግማል፡፡

በዚህም ጉባኤ፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ክፍለ ከተሞችን እና ወረዳዎችን እንደገና የማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት በማካሄድ የውሳኔ ሃሳብ ያስተላልፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪ በምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ አቅራቢነት ልዩ ልዩ ሹመቶችን እንደሚያፀድቅ የምክር ቤቱ የፕሬስ እና የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር  አዲስዓለም እንቻለው መግለጻቸውን ኤሜን ነው የዘገበው፡፡

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here