የኢስላም እምነትና ድንበር የለሽ ፍቅር የተሞላውን የኢትዮጵያ እንግዳ አቀባበል እንደ ውቅያኖስ ጥልቅ ከሆነው የታሪክ ማህደራችን ጠቅሶ ሊያስቃኘን ጁሀር ሳዲቅ ወዷል በዚህ ጽሑፉ ጥንታዊ በኢትዮ ያ እና በመሀከለኛው ምስራቅ መሀከል የነበረውን የንግድና ፖለቲካዊ ግንኙነት እንዲሁም የእስልምና እምነት ወደ ኢትዮ ያ የገባበትን ታሪካዊ አመጣጥ እንዲህ ባለ መልኩ አስቀምጦታለ
በጁሀር ሳዲቅ (ጋዜጠኛ)
ለመላዉ ለእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1442ኛዉ የነብዩ መሀመድ ሰዐወ ልደት መዉሊድ አደረሳችሁ እያልኩ …ወደ መንደርደሪያዬ አመራለሁ ።
ተጨልፎ ከማያልቀዉ የኢትዮጵያ ታሪክ ይህችን ወርወር አድርጊያለሁ. . ኢትዮጵያ anciently በነበራት ገናና ስልጣኔ አለማችን ላይ ካሉ እንደ ፋርስ ,ባዛንታይን እንደ ኦቶማን ተርኪሽ, ሮማን civilization በንግዱም በጦር ሰራዊትም ወዘተ እጅግ የገነነች ነበረች ;; ቀይ ባህር ዘይላ አዱሊስ እስከ ህንድ ዉቅያኖስ እስከ የመን ዳርቻ የኢትይጵያ trade roots ነበሩ ።ታዲያ ገናና በነበረችበት ዘመን የተለያየ ወቅቱ የሚጠይቀዉ የውጭ ግንኙነት foreign relationship ነበራት።
ከነዚህ አንዱ ከ አረብ የጎሳዎች ጋር የነበራት ግንኙነት ተጠቃሽ ነው። የንግድ ግንኙነታቸውም ጠንካራ ነበር ። በተለይ ከነብዩ የዘር ሀረግ የሚመዘዙት የአብድሸምስ ጎሳዎች ከኢትዮጰያ ጋር የነበራቸዉ ግንኙነት ረዥም ግንኙነት እንደነበራቸዉና ነገር ግን የኢትይጵያ ስልጣኔ ባለዉ ላይ እየጨመረ ከመሄድ ይልቅ ከ 558 እስከ 577 እየተፈረካከሠ ከመጣ በሗላ በ አረቦቹ በፋርሶችና በሌሎችም ሀይል የየመንን ክፍለ ግዛቷን ለቃ መሄዷእና አረቦች አካባቢ ያሉ ሀበሾች በተይም በንግዱ የተሠማሩ ሀበሾችና በባርነት የተገዙት የአረቡ ማህበረሰብ አካል ሆነዉ መቀላቀላቸው ላጴሶ ጌ ደሊቦ “ ዶ/ር የኢተዮጵያ ታሪክ የኢትይጵያና የኢትዮጵያዊያን የመነሻና የማንነት ግንዛቤ” በሚለዉ ድርሳናቸዉ ፅፈዋል።
ታዲያ በወቅቱ ከአረቦች ጋር በነበረ የባሪያ ንግድ ግንኙነት በባሪያነት የተሸጠችዉ የነብዩ መሀመድ ሰዐወ ቤተሰብ ለአባታቸዉ አብደላህና የአሚናህ አገልጋይ የነበረችዉ ኢትዮጵያዊትዋ ኡሙ አይመን (በረካ) ትገኝበታለች ። ነብዩ መሀመድ አባታቸው አብደላህና እናታቸዉ አሚናህ ገና በለጋ እድሜያቸዉ ሲሞቱባቸዉ ወላጅ አልባ orphan ሆኑ ከዛ በኋላ አጎታቸዉ የማሣደጉን ሀላፊነት ወሰዱ። በዚህ ወቅት ከእናት ባልተናነሰ ሁኔታ ኢትዮጵያዊቷ ኡሙ አይመን ተንከባክበው አሳድገዋቸዋል ።ታዲያ ነብዩ ይህች ኢትዮጵያዊት ሴት (በረካ) እንደ እናቴ ነች በማለት ገልፀዋቸዋል ።
ነብዩ መሀመድም ባደጉና ባወቁ ጊዜ ኢትዮጵያዊቷ ኡሙ አይመን ከባርነት ነፃ በማዉጣት (ሁር) ነፃነታቸዉን አወጁላቸዉ ሆኖም ኢትዮጵያዊቷ (በረካ) ነብዩ መሀመድን ሰዐወ እና እስልምናን መርዳት አላቆመችም ። እስልምናንም በጠዋቱ ከተቀላቀሉት በረካ አንዷ ነች ። በተለያዩ ኢስላማዊ ዘመቻዎች ላይ ተሳትፎ አድርጋለች። ለወታደሮች ዉሀና ስንቅ በማቅረብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክታለች ።ስለዚህ በኢስላም ወደ ኢትዮጵያ አድርገን ስንመለከት እንደ ኡሙ አይመን የመሣሠሉ አይነት አንፀባራቂ ሰዎችን ታገኛላችሁ ።
ከዚህ ደግሞ ወጣ ብለን ስንመለከት የምናገኘዉ ኢትዮጵያዊዉ ቢላል ኢብኑ ረባህ /ሀበሺይ እናገኛለን ።
ቢላል ሀበሺይ በሳኡዲ አረቢያ በ 578 እና 582 መካከል የተወለደ ቤተሰቦቹም ኢትዮጵያዊያን ናቸዉ ።ቤተሰቦቹ በባሪያ ንግድ ዘመን የተሸጡት ቢላልም በባሪያነት ነበር የተወለደዉ ። ኢትዮጵያዊዉ ቢላል ኢብን ረባህ “የኡመያህ ኢብኑ ከለፍ”አገልጋይ ነበር ከለፍ የጣኦት አምላኪ የነበረ ሰዉ ነበር ። ኢትዮጵያዊዉ ቢላል የነብዩ መሀመድ ሰዐወ መምጣትና ኢስላማዊ መልዕክት በሰማ ጊዜ አለቃዉ ከያዘዉ የእምነት አምልኮ አስተሣሠቡ ቀየረ ወደ ሙሀመድም ሰዐወ ልቡ አዘነበለች ። የኢትይጵያዊዉ አለቃ ኡመያህም የቢላል አመለካከት በሰማ ጊዜ እጅግ ተናደደ በሸቀ እዉነት ነዉም ብሎ ጠየቀዉ የቢልም ምላሽ ልቡ የመሸፈቱ እዉነት ገለፀ ።የአለቃዉ ንዴት ጨመረ የአረብ አለቆች በተሠበሰቡበት በጠራራ ፀሀይ ቢላልን ይዞት ቀረበ አመለካከቱ ይቀይር ዘንድ ግርፋትን አስተናገደ ኢትዮጵያዊዉ አሻፈረኝ አለ. … ላላየዉ መሀመድ ሰዐወ ልቡ አመነታ በግርፋት አላምን ባለ ጊዜ የተናደደዉ አለቃዉ ኡመያ ቢላል ሀበሺይ ላይ ትልቅ ድንጋይ ደረቱ ላይ ጫኑበት. …..በል ተመለስ ሲሉትም . ..አሀደን አሀድ “አንድ የሆነዉ አምላክ አንድ የሆነዉ አምላክ “. .በማለት የልቡን ነገራቸወ በእንዲህ አይነት ሁኔታ ዉስጥ እያለ የቢላል ስቃይ ነብዩ መሀመድ ሰዐወ ጋር ወሬዉ ደረሰ ። ነብዩ መሀመድም አቡ በከር ስዲቅን ለኢስላም ትልቅ አስተዋፅኦ ማድረግ የምትፈልግ ከሆነ ቢላሉል ሀበሺይ(ኢትዮጵያዊዉን)በአስቸኳይ ከሚያሠቃየዉ አለቃዉ ገዝተህ ነፃ አዉጣዉ አሉት ። ከሊፋዉ አቡበከር ሳዲቅም በፍጥነት ወደ ስፍራዉ አመራ ኢትዮጵያዊዉ መራር ቅጣት እያስተናገደ ነበር አቡበከርም ለምን ይሄን ያህል ታሠቃየዋለህ ለምን አትሸጥልኝም? አለዉ ኡመያም ተስማማ አቡበከር አስፈላጊዉን ገንዘብ ከፍሎ ነፃ አወጣዉ ።
ቢላል በይፋ ነብዩ መሀመድ በመከተል እስልምናን ተቀላቀለ. ..ከዚህ ጊዜ አንስቶ የነብዩ መሀመድ ተወዳጅ ባልደረቦች መሀከል ቢላል አንዱ ነበር ። ኢትዮጵያዊዉ ቢላል በነብዩ መሀመድ ሰዐወ (ሙአዚን)በእስልምና ለሠላት አምልኮት እንዲመጡ ጥሪ የሚያደርግ ሆኖ ተሾመ ሁኔታዉ/ሹመቱ/ ብዙ ነገሮችን ያካተተ ነበር በመጀመሪያ አረቦች ከኛ በላይ ሰዉ የለም የሚሉ ነበሩ በቆዳ ቀለማቸው ይመኩ ነበር ።ቢላል ሙአዚን ተጣሪ አድርገዉ ሲሾሙት እንዴት ለአንድ ጥቁር ለዛዉም ባሪያ ለነበረ ሰዉ ሹመት ይሰጣል ይሄ አረብን ማዋረድ ነዉ በማለት አጉረመረሙ እንደምክንያት ካቀረቡት ነገር ቃሎቹን በደንብ አይላቸዉም ይሰባብራል ኮልታፋ ነዉ የሚል ነበር ። ነብዩ መሀመድ ሰዐወ በአረቦቹ ዘረኝነት በጣም ተበሳጩ በመጀመሪያ ጥቁር ነጭ ቢጫ ሁሉም በአላህ ፊት እኩል ነዉ ካሉ በኋላ ከእናንተ የምትሰሩትን መልካም ስራ እምነታችሁ እንጂ የቆዳ ቀለማችሁ ለፈጣሪ ምንም ፋይዳ የለዉም በማለት ዘረኝነት ከገማ ነገር በሙሉ የገማ ጥንብ ናት በማለት ገለፁ ። አፉ ይኮላተፋል በሚጣራ ሰአት/አዛን ሲያደርግ ላሉት ደግሞ የቢላል አዛን ከዚህች ምድር አልፋ የጀነት ሰዎቹ ሁሉ ያዉቁታል/ይሠሙታል ፈጣሪም ያዉቀዋል በማለት አለዘቧቸዉ አረቦቹም ሳያመነቱ ተቀበሉ ። ትንሽ ስለ ማዕረጉ በለብ ለብ ልለፈዉ በኢስላማዊ የሀዲስ አስተምህሮ “ሙአዚኖች የምፅአቱ /የዉመል ቂያማ ላይ አንገተ ረዥሞች መሆናቸዉ ይገልፁና እናንተ በምድር ላይ ስትኖሩ ሰዎችን ወደ ኔ ስትጣሩ ነበር ኑ በማለት ይጠራቸዋል ይላል privileged ናቸዉ ከነዚህ አንዱ ኢትዮጵያዊዉ ቢላል መገኘቱ ነዉ ።ሌላዉ ነብዩ መሀመድ በመገረም ለቢላል ጠየቁት አንተ ቢላል ገነት ዉስጥ ኮቴህ ሰምቸዋለሁ እኔ የማላዉቀዉ ምን ሰርተህ ነዉ አሉት. …… ከዚህ ባለፈ አዲሱን አሀዳዊ ሀይማኖት ለመርዳት ዘመቻዎች ላይ ተሳትፏል ።በመጨረሻም ኢትዮጵያዊዉ ቢላል ወደ ሶሪያ አቀና በደማስቆ ከቆየ በኋላ በ638/642 መካከል እንዳለፈ የህይወትና ታሪኩ የዳሠሡ ድርሳናት ይገልፃሉ ። ታዲያ በደማስቆ ቢላልን የሚዘክሩ ሀዉልቶች መስጂዶች ተቆማቶች ተሠይመዉለት ይገኛል ። አትዮጵያ በነዚህ ኢትዮጵያ ግፋ ቢል በቱሪስት መስህብነት እንኳ ገንዘብ ለማግኛ እንኳ ስትጠቀም አልታየም ።በቱሪዝሙ ማዋል ለምን አልተቻለም ? …..ይሄ ለባህልና ቱሪዝምና ለእስልምና ጉዳዮች እተወዋለሁ ።
ምንጮች ……..
Dr, abdurahman al sheha billal the Abyssinian :- On light Many colors Islamic view point on Racism .
Nehemia, and Randall Lee Pouwels:- The History of Islam in Africa. South Africa
Cairo News. …… about bilal the companion of the prophet .
ነብዩ መሀመድ እና ምድረ ኢትዮጵያ !
ከላይ በገለፅኩት መሠረት ነብዩ መሀመድ ሰዐወ አዲሱ አሀዳዊ ሀይማኖት እስልምና በሳኡዲ አረቢያ አወጀ ።ሆኖም ግን ነብዩ መሀመድ በገዛ ወገናቸዉ ከፍተኛ ተግዳሮት አጋጠማቸዉ ። የቁረይ ሽ ሹማምንቶች በነብዩ መሀመድ ላይ የአመፅ ጥሪ አካሄዱ። ነገር ግን ነብዩ መሀመድ አረቦች ቅድመ እስልምና የነበሩበት inhuman የሆነ አካሄድ በተለይ ሴትን ልጅ ከነ ሕይወቷ እንደተወለደች የሚቀብሩበት የጨለመ አካሄዳቸውና በመካ ዙሪያ ያሰባሠቧቸዉ ሠዉ ሠራሽ አማልክቶች ጣኦታቶችን በጥብቅ ማዉገዙን ህዝቡን ማንቃቱን ከጓዶቻቸዉ ጋር በመሆን አፋፋሙት። ከጊዜ ወደ ጊዜ የሠዉ አመለካከት እየለወጡ መጣ ቁረይሾቹ ይህንን በተመለከቱ ጊዜ የወቅቱ ገዥዎች እነሱ ነበሩና ተግዳሮቱ በዛ ከተወለዱበት ሀገራቸዉም መዉጣት መሠደድ የግድ ሆነ በዚህ ወቅት ነብዩ ተናገሩ ወዳጆቼ ሆይ በሀበሻ ምድር እጅግ ፍትሀዊ ታማኝ ከሱ ዘንድ ማንም የማይበደልበት እዉነተኛ ንጉስ አለና ወደዛ ተሠደዱ በማለት ከሰሀቦቻቸዉ የተወሰኑት ወደ መዲናና ቁጥራቸው ( ….)የሚደርሱት ደግሞ ወደ አርዱል ሀበሻ(የኢትይጵያ ምድር) በቀይ ባህር አድርገዉ ሸኟቸዉ ። ኢብኑ ኢስሀቅ የተባሉ ዘጋቢ በዘገቡት መሠረት በ615 አካባቢ ወደ ኢትዮጵያ ከመጡት የመጀመሪዎቹ ተጓዦች 11 ወንዶችና 5 ሴቶች መሆናቸዉ ገልፀዋል በስማቸውም. .. እንደሚከተለዉ ነዉ ።ሰአድ ኢብኑ አቢ ወቃስ, ጀህሽ ኢብን ሪያብ, አብደላህ ኢብኑ ጀህሽ, ጃዕፈር ኢብን አቡጣሊብ (የተጓዦቹ መሪ) ኡስማን ,ሩቂያ የነብዩ መሀመድ ሰዐወ ልጅና የኡስማን ሚስት, ሀይፋ ኢብን ኡትባ, ሰህላ ቢንት ሱሀይል, ዙበይር. .ሙስአብ ኢብን ኡመይር, አብዱራህማን ኢብን አዉፍ, አቡ ሰላማ አብደላህ ብን አሳድ ,ኡም ሰላማ, ኡስማን ኢብን ማዕዙን, አማር ቢን ራቢያ,ለይላ ብንት አስማህ. ….የአሚር ሚስት ይገኙበታል ።
በነገራችን ላይ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት እንግዶች በጣም ከባባድ የነብዩ የቅርብ ቤተሰብ ናቸዉ የራሳቸዉ የነብዩ ልጅ ኢትዮጵያን አይታለች ባርካታለች ከበረከታችንም ተቋድሳለች ሌላዉ ሶስተኛዉ ከሊፋ የሆነዉ ኡስማን ነዉ ነብዩ በአንድ ንግግራቸዉ ከሎጥ በኋላ ከነ ቤተሠቡ የተሠደደ ቢኖር ኡስማን ነ ብለዋል ከሊፋዉ ከነ ቤተሠባቸዉ ነዉ ያለምንም ስጋትና ፍርሀት ልክ እንደቤታቸዉ ነበር ወደ ኢትዮጵያ የገቡት. …….ሌላኛዉ የአጎታቸዉ ልጅ ጀዕፈር የስደተኞቹ መሪ እንዲሁም የኩፋ የፋርስ የጦር መሪ የነበረዉ የነብዩ ተወዳጅ ጓደኛ ሰአድ ኢብን አቢ ወቃስ የኢትዮያን ምድር በረከት ተቋድሰዋል ኢትዮጵያም ዱአቸዉን አግኝታለች ። ታዲያ ይሄ የትኛዉም ሀገር አልታደለም ምናልባት ኢትዮጵያ ካልሆነች በቀር. …..በዚህ እሴታችን. .. ኮራሁስ ልንኮራም ይገባል ። በእስልምናዉም በክርስትናዉም በሙሴ ሀይማኖትም የተመረቀች በረከት ያገኘች ሀገር ኢትዮጵያ!
ታዲያ እግዶቹ ወደ ኢትዮጵያ ምድር ከረገጡ ጀምሮ ነብዩ መሀመድ ሰዐወ ካሏቸዉ ነገር ምንም የተለወጠ ነገር ባለማየታቸው ነዉ ንጉሱ አክባሪ እዉነተኛ ፍትሀዊ መሆኑ ነዉ ንጉሠ ነገስቱ ነጃሺ (አስሀማ ኢብን አብጃር) እንግዶቹን በጥሩ አቀባበል ተቀበለ ። ነገር ግን ሙስሊሞቹ ወደ ሀበሻዉ (ኢትዮጵያዉ) ንጉስ ጋር መሠደዳቸዉ ቁረይሾቹ ሲሠሙ የግር እሳት ሆነባቸዉ መሪዎች ትላልቅ ስጦታዎችን ማታለያዎችን ይዘዉ ንጉሱ እንግዶቹ አሳልፎ ይሰጣቸዉ ዘንድ ለመጠየቅ አምር ኢብን አስ እና ኡማረተ ብን ወሊድን ወደ ኢትዮጵያ መልክተኞች አድርገዉ ሰደዱ ።ወደ ንጉሱም ቀረቡ የሆኑ ወንጀለኞች ከጎሳችን ወጥተወ እናንተጋር ተደብቀዋል እነሱን እንዲሠጡን ነዉ አሉ ነገር ግን ንጉሱ ብልህ አስተዋይ በመሆናቸዉ ሁለቱም ወገኖች በችሎታቸዉ አቁመዉ እንዲናገሩ አደረጉ. ………የቁረይሽ መልክተኞች ንጉስ ነጃሺን ለማማለል ከሰገዱለት በሗላ ንጉስ ሆይ እነዚህ ሰዎች የአባቶቻቸውን እምነት አርክሰዉ ነዉ የመጡት የአንተንም ሀይማኖትህ ያረክሳሉ በተለይ ስለ ክርስቶስ ብለዉ ለኮስ አደረጉት ህዝቡ ይፈልጋቸዋል በማለት
ንጉሱን ለማሣመፅ ሞከሩ ብልሁ ንጉስ ግን የነሱን ጉትጎታ ሣይሰማ ከችሎቱ ያሉትን ሙስሊሞች ስለ እምነታቸዉ እምነታቸዉ ምን እንደሚያዛቸው እና ስለ ክርስቶስ ጠየቃቸዉ. . የሙስሊሞቹ መሪ ጀዕፈር ቀረቦ አስረዳ እምነታችን ኢስላም ይባላል እሱንም ይዞልን የመጣዉ የአላህ መልዕክተኛ (መሀመድ)ሰዐወ ይባላል ። ከዛ በፊት እኛ ሴቶቻችን በሕይት እንቀብር ነበር ለጣኦታት እንሠግድ ነበር ወላጆቻቸዉ የሞቱባቸዉ ልጆች ገንዘብ እንወስድ ነበር እንዋሽ ነበር
ጉልበት ያለንን የሌለዉን እናጠቃ ነበር ነገር ግን መልክተኛዉ ይዞልን የመጣዉ ከዚህ የተሻለና እነዚህ ነገሮችን የሚነቅፍ ሲሆን የምንገዛዉ የሠማዩ አንድ አምላክ ብቻ ነዉ እንድናመልክ እምነታችን የሚያዘን አለ ጃዕፈር ። ጃዕፈር ስለ ክርስቶስ ደግሞ ቀጠለ ክርስቶስ በኛ በቁርአን በሱረቱል አል ኢምራን እንደተገለፀዉ የሠማዩ አምላክ መለኮታዊ ሀይል የተቸረዉ ከመርየም በድንግልና የተወለደ መሆኑን ነዉ የሚያስተምረን በማለት ቋጨ ። ታዲያ ነጃሺ በሙስሊሞቹ ሀሣብ በመስማማት መደለያና ስጦታ ይዘዉለት የመጡት የቁረይሽ መልክተኞችን ሙስሊሞቹ እንግዶቼ ናቸዉና አሳልፌ አልሰጥም በማለት ከነ ያዙት ስጦታቸዉ ወደ መካ መለሣቸዉ ።
ለሙስሊሞቹ ደግሞ በኢትዮጵያ ሙሉ ነፃነት ሰጥቷቸዉ ወደ ሀገራቸዉ እስኪመለሱ እንዲቆዩ አደረጉ ። በዚህ ታሪክ ዉስጥ የምናገኘዉ ትልቁ ነጥብ መላዉ አረቢያ የነብዩ ጎሳዎች ቤተሠቦች የመካ ሠዎች እና የተወለዱባት (መካ) እስልምና ሳትቀበልና በእስልምና ሣታምን እዉቅና ሣትሰጥ ባለ ገናናዋ ሀገራችን ኢትዮጵያ ግን ከአለም ቀዳሚዋ ለእስልምና እዉቅና የሠጠች ሀገር በመሆን ስሟ ከእስልምና ጋር ተያይዞ ይነሣል።
በስደትም የመጀመሪያ ስደት ያስተናገደች ሀገር ነች ኢትዮጵያ !
በመጀመሪያ ዙር የመጡት ስደተኞች ወደ ሀገራቸዉ ተመለሱ ነጃሺም ነብዩን ዘይሩልኝ በማለት ላከ መልክተኞቹም ለነብዩ አደረሱ ነብዩም በደስታ እንዲህ በማለት ለነጃሺ ዱአ አደረጉለት ይላል…ዱአዉ “ አላሁመግፊር ሊነጃሺ” 3ቴ አማርኛ “ፈጣሪ ሆይ ለነጃሺ ምህረት አድርግለት “ የሚል ነዉ ሆኖም ግን በመካ የታሠበዉ ሠላም ሊያገኙ አልቻሉም በድጋሚ ሁለተኛዉ ስደት በ631 በድጋሚ ወደ 104 የሚደርሱ ስደተኞች ላኩ . … እስልምናም በኢትዮጵያ መሠረት ያዘ. …ቱርካዊዉ (አል አዝም):- rihlate al habesha(the Ethiopian voyage) በተሠኘዉ ጽሁፉ ከአጠቃላይ ስደተኞች 21 የሚደርሱ ኢትዮጵያዊያን ነበሩበት በማለት ገልጿል .ስደተኞቹ ወደ ሀገራቸዉ ሲመለሱ የንጉስ አስሀማ የወንድም ልጅ ዙ ማኽጃር አልሀበሻ ከሰባ ሁለት በላይ ምርጥ ወታደሮች ለነብዩ መሀመድ ላኩላቸዉ በማለት (ዶር ላጴሶ ጌ ደሌቦ ) ገልፀዋል ገፅ 59 የኢትይጵያ ታሪክ 2010 ምናልባትም እነዚህ ወታደሮች ነብዩ መሀመድ ወደ መካ ባደረጉት የፈትህ(የመክፈት)ዘመቻ ላይ ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳ ደርጉ ይታመናል ።
ነብዩ መሀመድ ሰዐወ በቀዉላቸዉ(በንግግራቸዉ) ኢትዮጵያን እንዳትነኩ በማለት ለሀገሪቱም ለህዝቡም ያላቸዉ ቦታና ለማሣየት በቅቷል ምናልባት አትንኩ የተባለ ቦታ ከኢትዮጰያ ከመካና መዲና ዉጪ ያለ አይመስለኝም ይሄም ለየት ያደርጋታል ብቸኛ በነብዩ ፍትሀዊ እዉነተኛ ንጉስ የተባለዉ የኢትዮጵያዉ ንጉስ ነጃሺ ብቻ ነዉ።
ሌላዉ ለየት የሚያደርገት ነገር ኢትዮጵያ የነብዩ መሀመድ መዉሊድ(ዉልደት) በብሔራዊ በአላቸዉ አድርገዉ ከሚንቀሳቀሱ ሀገሮች ተርታ ትገኛለች ።በአሉ በየ አመቱ በሱኒ ሙስሊሞች ዘንግ በአረቢክ ካሌንደር መሠረት በረቢዑል አወል ቀን 12ላይ የሚከበር ነዉ ወሩም ቀኑም ነብዩ መሀመድ ሰዐወ የተወለዱቀት ስለሆነ ነዉ።
መዉሊድ በኢትዮጵያ ረቢዑ እስኪያልቅ ይደገሣል በየመንደሩ በየ መስጂዱ ይከበራል ።
መዉሊድ ታሪካዊ አመጣጡ በታቢኢ በተባሉት ትዉልዶች እንደተጀመረና በ13ኛዉ ክፍለዘመን እንደሠፋ ይነገራል በኢትዮጵያ ከ16ኛዉ ክፍለ ዘመን ቀደምብሎ በሀረር እንደተጀመረ ቀስ በቀስ ወሎ እና አማራ ክልል ትግራይ በጉራጌ ቀጥበሬና አብሬት እና በስልጢ በመሻኢኮቹ(በከፍተኛ የሀይማኖት አባቶች ) እንደሚከበር እና በዚህ እለት ሙስሊሞቹ በግ ግመል የመሣሠሉ እርድ እንደሚፈፅሙና ለሚስኪኖች እንደሚያበሉ እንዲሁም ዚክር በግጥም የነብዩ መሀመድ ሰዐወ ገድሎች እያወሱ እንደሚያሣልፉ በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ማህበራዊ ፖለቲካዊ ሀይሚኖታዊ ታሪክ ዙሪያ ጥናት አድርጎ የፃፈዉ Islam in Ethiopia (ኢስላም በኢትዮጵያ ዉስጥ) በሚል ባዘጋጀው ድርሳኑ ገልጷል ።
ባጠቃላይ ከዚህ ፅሁፍ ወደ ታች ቁልቁል ሽቅቡን የወረድኩት ኢትዮጵያ ቀላል አናድርጋት ባለ ትልቅ ታሪክ ባለገናና ስልጣኔ መሆኗን ነዉ ዛሬ እነዚህ እሴቶች ልንጠቀምባቸዉ ይገባል ።
ምንጮች. ..
ኡስታዝ ሀሠን ታጁ:- መዉሊድ መፅሀፍ
ሞሀመድ አል ባርባንቂ:-ሀያቱ ሶሀባ( የነብዩ መሀመድ ጓደኞች ታሪክ)
ረሂቀተል መኽቱም….የነብዩ መሀመድ ታሪክ
ዶር ላጴሶ ጌታሁን ደሊቦ….የኢትይጵያ ታሪክ
J S Trimingham :- Islam in Ethiopia
Simon Taristani :- Mawlid Celebrating the birth of the prophet in Islamic ritual and weeding ceremonies in Harar.
ቅጽ 2 ቁጥር 103 ጥቅምት 14 2013



