የአዲስ ማለዳ ዋና አዘጋጅ ከሰዓታት እስር በኋላ ተለቋል

0
904

የአዲስ ማለዳ ዋና አዘጋጅ የሆነው ባለደረባችን ኤርሚያስ ሙሉጌታ ትናንት ጥቅምት 16/2013 ረፋድ 5 ሰዓት ላይ ከቢሮው ሲቪል በለበሱ የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ተወስዶ የነበረ ቢሆንም በዛኑ ቀን ምሽት 2 ሰዓት ላይ መለቀቁን እናስታውቃለን ።

የባልደረባችን በቁጥጥር ሥር ለመዋል በጋዜጣችን ላይ የተጻፈም ሆነ የታተም ምንም ዓይነት ምክንያት እንዳልሆነ እና ተጨባጭ ምክንያትም አለመቅረቡን እናስታውቃለን።

በዚህ አጋጣሚ ዋና አዘጋጁ በቁጥጥር ሥር በዋለበት ወቅት ከጎናችን ሆናችሁ የሚዲያ ሽፋን ለመስጠት እና በጉዳዩ ላይ በኃላፊነት ስሜት አብራችሁን ለነበራችሁ የሚዲያ ባለሙያዎች እና አጋሮቻችን ምስጋናችንን እናቀርባለን ።

አዲስ ማለዳ ዝግጅት ክፍል

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here