ከጣና የራቀው – “ጣና ፎረም”

0
1134

በአፍሪካ ደረጃ የሚከሰቱ ችግሮችን አሕጉራዊ መፍትሔ ለመስጠት ከአፍሪካ ሰሜናዊ ጫፍ አገረ ቱኒዚያ እስከ ደቡባዊ አሕጉሪቱ ጫፍ ደቡብ አፍሪካዊቷ አገር ስዋዚላንድ ለምክክር ይቀመጣሉ፤ በምሑራኖቿ አስተያየትም ለነገዋ የጥይት ድምጽ የማይሰማባት አፍሪካን ለመፍጠር እልህ አስጨራሽ ውይይቶች ይደረጋሉ። ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሰው መድረክ በአፍሪካ ደኅንነት ጉዳዮች ላይ መሰረት አድርጎ የሚመክረው የ‹‹ጣና የከፍተኛ ባለሥልጣናት ምክክር ጉባዔ›› አንደኛው ነው።

ዘንድሮ ለዘጠነኛ ጊዜ ከጥቅምት 9-14/2013 የተካሔደው ይኸው ጉባዔ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተውን የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ተከትሎ ለስምንት ዓመታት በተከታታይ ሲካሔድ በነበረበት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መናገሻ ባህር ዳር ወደ አፍሪካ መዲና ወደ ሆነችው አዲስ አበባ ሸራተን ሆቴል በጊዜያዊነት ተዛውሯል።

በዚህም ኹነትም ዘንድሮ በቴክኖሎጂ የታገዘ ‹‹ቨርቹዋል›› ዝግጅት የተካሔደ ሲሆን የኢፌዴሪ ፕሬዘዳንት ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና የኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ገዱ አንዳርጋቸው በይፋ አስጀምረውታል።

ቅጽ 2 ቁጥር 103 ጥቅምት 14 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here