ጥቅምት 30 ይጀመራል የተባለው የ2013 የትምህርት ዘመን ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ

0
926

በመጪው ሳምንት ጥቅምት 30/2013 ይጀመራል የተባለው የ2013 የትምህርት ዘመን የገጽ ለገጽ የመማር ማስተማር ሂደት ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

ከ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ውጪ በተቀሩን ክፍሎች ትምህርት ከመጀመሩ በፊት በኮቪድ-19 የቀውስ ጊዜ የትምህርት አመራርና አስተዳደር ስትራቴጂ እቅድ ላይ የተቀመጡ ስታንዳርዶችን ሟሟላት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ አስፈላጊ ዝግጅቶች በተሟላ ደረጃ እስኪጠናቀቁ ድረስ በከተማዋ ለመጀመር የታቀደው የገጽ ለገጽ ትምህርት ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን ቢሮው አስታውቋል፡፡

ከባለፈው ጥቅምት 16 /2013 በመሰጠት የጀመረው የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል የገጽ ለገጽ የክለሳ ትምህርት የመማር ማስተማር ሂደት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ቢሮው መግለጹን ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬታሪያት የተገኘ መረጃ ያመለክታል።

 

በአዲስ አበባ ከተማ የ2013 የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ በማያጋልጥ ሁኔታ ጥቅምት 30/2013 ትምህርት ለመጀመር በርካታ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በማከናወን ላይ እደሆነ መግለጹም ይታወሳል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here