ከ25 ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸዉ የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

0
652

በአፋር ክልል ዞን ሦስት ሀሩካ ወረዳ ብዙ ጊዜ በኮንትሮባንድ ክምችት የምትታወቀዉ ገዳማይቱ ከተማ ጥቅምት 18 2013 በተደረገ የአንድ ቀን የኦፕሬሽን ሥራ በብዙ መጋዘኖች ውስጥ ተከማችተው የነበሩ እና ግምታዊ ዋጋቸው 25,904,640 /ሃያ አምስት ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።
ከተያዙት የኮንትሮባንድ እቃዎች ውስጥ ዋና ዋናዎቹ፥ ሲጋራዎች ፣ ሺሻዎች፣ መድኃኒት ፣ ቴሌቭዥን ፣ሪሲቨሮች ፣ የኤሌክትሮኒክ እቃዎች ፣ የልብስ ማጠቢያ ማሽኖች ፣ የፊት ቀለም ፣ አሮጌ ልባሽ። ጨርቅ፣ አዳዲስ አልባሳት ፣ ጫማዎች እና ልዩ ልዩ እቃዎች እንደሆኑም ተገልጿል።
ጥቅምት 18 2013 ከጧቱ 12፡00 ላይ በጉምሩክ መረጃ ሰራተኞች ፣ በፌዴራል ፖሊስ እና በአገር መከላከያ ሠራዊት ጋር በመሆን ተከማችቶ ባለበት ቦታ በመያዝ በዛዉ እለት በስድስት የተሽከርካሪዎች ተጭኖ አዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ማታ 1፡00 አከባቢ ላይ እንዲገባ ተደርጓል።
የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽንም ኮንትሮባንዱን ለያዘው ለአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት አመራር እና ሠራተኞች እንዲሁም ሥራው ያለምንም ችግር እንዲሳካ ከፍተኛ ሚና ለተጫወቱ የፀጥታ አካላት ምስጋና ማቅረባቸውን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ቅጽ 2 ቁጥር 105 ጥቅምት 28 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here