በአዲስ አበባ ከተማ ትርምስ ለመፍጠር የህወሃት ቡድን ያሰማራቸው 242 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

0
534

በአዲስ አበባ ከተማ ትርምስ ለመፍጠር የህወሃት ቡድን ያሰማራቸው 242 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም የህወሃት ጁንታ ቡድን ያሰማራቸው 242 ግለሰቦች በከተማዋ ትርምስ ለመፍጠር ሲንቀሳቀሱ ተደርሶባቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኮሚሽነር ጌቱ ገልጸዋል።
ግለሰቦቹ 18 ያህል ቦምብ፣ 2 ፈንጂ፣ ላውንቸር ፣ ከ174 በላይ ሽጉጥና ከ4 ሺህ በላይ ጥይቶችና 4 ወታደራዊ የጦር ሜዳ መነጽሮችም በጥፋት ሃይሉ እጅ የተለያዩ አካባቢዎች በቁጥጥር ስር እንደዋለም ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል።
በተጨማሪም 23 የረጅም ርቀት መገናኛ ሬድዮ በሱር ኮንስትራክሽን በተደረገ ብርበራ ማግኘቱን ኮሚሽነር ጌቱ በመግለጫቸው አንስተዋል።
ከዚህ በተጨማሪም 350 የተለያዩ ሃገራት ሲም ካርዶች ከአንድ ግለሰብ የተገኙ ሲሆን 7 የተለያዩ ሃገራት ፓስፓርት፣ 74 የተለያዩ የደንብ ልብሶችና የውጭ ሃገር ስልክ መጥለፊያ በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም አስታውቀዋል።
ከወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ ጋር ተያይዞ በከተማዋ ምንም አይነት ችግሮች እንዳይከሰቱ ህብረተሰቡ አካባቢውን በንቃት ከመጠበቁ በተጨማሪ መረጃና ጥቆማ በመስጠት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን አስቀድሞ በማምከን እያደረገ ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል ኮሚሽነር ጌቱ ጥሪ አቅርበዋል።

ቅጽ 2 ቁጥር 106 ኅዳር 5 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here