የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሰራተኞች የሰንደቅ አላማ ስነ-ስርዓትን ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ

0
663

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር  ከዛሬ ኀዳር 07/2013 ጀምሮ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ በስራ መግቢያ እና መውጫ ሰአት ላይ ለሰንደቅ አላማ ተገቢውን ክብር ለመስጠት በመወሰን ተግባራዊ ማድረግ መጀመራቸው ተነግሯል።

 

በማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት ላይ በመገኘት ሰንደቅ አላማ የሰቀሉት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯሂሩት ካሳው (ዶ/ር )፤ ባህልን እንደሚመራ መስሪያ ቤት ይህንን የአገር ፍቅር ማሳያ የሆነ ተግባር ከራሳችን በመጀመር ሌላውም እንዲከተለው ማድረግ ተገቢ ነው ብለዋል፡፡

 

‹‹በተለይም በዚህ ወቅት የሀገር መከላከያ ሰራዊታችን የሚዋደቅለትና ለዘመናትም በጉድጓድ ውስጥ የሚኖርለት ይህን ሰንደቅ ዓላማ ማክበር ሀገራችንን ማክበር ነው›› ማለታቸውን ከሚንስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here