የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካበቢ ጥበቃ እና አረንጓዴ ልማት ኮሚሽን በከተማዉ ዉስጥ ከሚገኙ የማዕድን አልሚዎች እና ባለሀብቶች ጋር በኮንስትራክሽን ማዕድን አሰራር ዙሪያ ዉይይት አድርጓል፡፡
በምክክር መድረኩ ላይም ከባለሀብቶች በኩል ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን በመሬት አጠቃቀም ዙሪያ ካባ ድንጋይ የሚወጣባቸዉ ቦታዎች ከከተማ መስፋፋት ጋር ተያይዞ ቦታዎች እያለቁ ስለሆነ በቀጣይ የከተማዉን የኮንስትራክሽን ሥራዎች ለማሳለጥ የጀርባ አጥንት የሆነዉን የድንጋይ ማዉጣት ሥራ መንግስት በሰፊዉ እንዲያስብበት አሳስበዋል፡፡
የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ሲሳይ ጌታቸዉ እና ምክትል ኮሚሽነር ዋለልኝ ደሳለኝ ምላሽ እና ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን በማዕድን እና ኮንስትራክሽን ዘርፍ ባለሀብቶች የጋራ ፎረም እንደሚያስፈልግ የተገለፅ ሲሆን ዘርፉን ለማዘመን የፖሊሲ ዝግጅትና የተለያዩ ዘመናዊ አሰራሮች መዘርጋት አስፈላጊ እንደሆነና ይህን ሃብት በእውቀት፣ በኃላፊነትና በግልጽነት ሊመራ ይገባል ብለዋል።
በአዲስ አበባ ዉስጥ 269 በማዕድን ዘርፍ ህጋዊ ፍቃድ ወስደዉ የሚሰሩ አልሚዎች ይገኛሉም ተብሏል ።
መረጃውን ያገኘነው ከኮሚሽኑ የፌስቡክ ገጽ ላይ ነው።



