በጃን ሜዳ እንዲሰሩ የተደረጉ የአትክልት ነጋዴዎች በቅርብ ቀን ወደ ተዘጋጀላቸው የገበያ ማዕከላት ይዘዋወራሉ ተባለ

0
665

የሕዝብ መተፋፈግን በመቀነስ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽን ለመከላከል ከአትክልት ተራ ተነስተዉ በጃን ሜዳ እንዲሰሩ የተደረጉ የአትክልት ነጋዴዎች በቅርብ ቀን ወደ ተዘጋጀላቸው የገበያ ማዕከላት ይዘዋወራሉ ሲሉ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታወቁ።

ዛሬ በከተማችን በግንባታ ላይ ያሉና ተገንብተው ያለአገልግሎት የቆዩ የገበያ ማዕከላትን ጎብኝተናል ያሉት ምክትል ከንቲባዋ፤  በሃይሌ ጋርመንት፣ በጀሞ አበባባይ፣ ኮልፌ እና በሌሎችም አካባቢዎች ባደረግነው ጉብኘት ግንባታዎቹ ያሉበትን ደረጃ እና ጥራት ገምግመናል ብለዋል።

እነዚህ ማዕከላት እድሳታቸው ተጠናቆ ቅድሚያ በጃን ሜዳ ላሉ የአትክልት ተራ ነጋዴዎች እንዲሰጡ ይደረጋል፤ ለስራ ክፍት ሲሆኑም ለአምራቹ ለነጋዴው እና ለሸማቹ የተሻለ የገበያ አቅረቦትና ትስስር እንደሚፈጥሩ አያጠራጥርም ሲሉ በቲውተር ገጻቸው ላይ ይፋ አድርገዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here