የነዋሪነት መታወቂያ የአገልግሎት ዘመን ወደ አራት ዓመት ከፍ ማለቱን የአዲስ አበባ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ አስታወቀ።
ከኅዳር 24 ጀምሮ በከተማዋ የሚሰጡ የነዋሪነት መታወቂያዎች ሳይታደሱ ማገልግል የሚችሉበት ዘመን ከኹለት ወደ አራት ዓመት ከፍ እንዲል ተወስኗል።
ኤጀንሲው የባለጉዳይ ምልልስ እንዲሁም በሌሎች አገራት ያለውን ተሞክሮ ከግምት ውስጥ በማስገባት ማስተካከያ ማድረጉን ገልጿል።
የዲጂታል መታወቂያውን በሁሉም ወረዳዎች ለማዳረስ የመብራት ብሎም የብይነ መረብ አገልግሎት መቆራረጥ እና ተደራሽ ያለሆነባቸው ወረዳዎች መኖር ወጥ አሰራር እንዳይኖር እንቅፋት ፈጥሮብኛል ብሏል።
ዘገባው የአሐዱ ቴሌቪዥን ነው



