የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና እስከ ታህሳስ 30 ተሰጥቶ እንደሚጠናቀቅ ተገለፀ

0
1971
የትምህርት ሚኒስቴር ባስቀመጠው የግዜ ሰሌዳ መሰረት የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በሁሉም ክልሎች እስከ ታህሳስ 30 ተሰጥቶ እንደሚጠናቀቅ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ይህንንም ተከትሎ የክልል ትምህርት ቢሮዎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመወያየትና አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ ፈተናውን በተያዘለት የግዜ ገደብ ለመስጠት የራሳቸውን የግዜ ሰሌዳ እያወጡእንደሚገኙ ተገልጿል።

በዚህም መሰረት የሀረሪ ክልል ከ ታህሳስ 7-9፣ የአማራ ክልል ከታህሳስ 12-14 ፈተናውን ለመስጠት መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከትላንት ጀምሮ መሰጠት የተጀመረ ሲሆን ሌሎች ክልሎችም በቀጣይ ቀናት ፈተናው የሚሰጥበትን ቀን ይፋ የሚያደርጉ መሆኑን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here