ከአንደኛ እስከ አራተኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች የፊታችን ሰኞ ትምህርት ይጀምራሉ

0
350

ከሰኞ ከታህሳስ 12 ቀን 2013 ጀምሮ በአራተኛ ዙር ወደ ገጽ ለገጽ የመማር ማስተማር ስራ የሚገቡ የክፍል ደረጃዎች በግል ትምህርት ቤቶች የቅድመ መጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች እና በመንግስት ትምህርት ቤቶች ከአንደኛ እስከ አራተኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች ትምህርት እንደሚጀምሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ገለጸ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኀላፊ ዘላለም ሙላቱ በዛሬዉ እለት በሰጡት መግለጫ እንዳሳወቁት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን በመከላከል የገጽ ለገጽ የመማር ማስተማር ስራዉ በተለያየ ዙር እንዲጀምር ተደርጓል።
በከተማዉ ትምህርት ለማስጀመር በተቀመጠዉ ውሳኔ መሰረት ቀደም ሲል ህዳር 16 ቀን 2013 የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎቸ በክለሳ ትምህርት ውስጥ እንዲያልፉ መደረጉን አስታውሰዋል።
ህዳር 28 ቀን 2013ደግሞ በግል ትምህርት ቤቶች ከ1ኛ ክፍል ጀምሮ በመንግሰት ትምህርት ቤቶች ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ በሶስት ዙሮች ትምህርት መጀመሩን ገልጸዋል።
ከሰኞ ከታህሳስ 12 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በ4ኛ ዙር ወደ ገጽ ለገጽ የመማር ማስተማር ስራ የሚገቡ የክፍል ደረጃዎች በግል ትምህርት ቤቶች የቅድመ መጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች እና በመንግስት ትምህርት ቤቶች ከ1ኛ እስከ 4ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች መሆናቸዉን ሀላፊዉ አሳውቀዋል።
“ህጻናት ተማሪዎችን ወደ ገጽ ለገጽ የመማር ማስተማሩ ስራ እያመጣን በመሆኑ የተዘጋጀዉን የኮቪድ-19 ፕሮቶኮልን በአግባቡ መተግበር እንዲቻል የትምህርት ባለድርሻ አካላት የበኩላቸዉን ሚና መወጣት አለባቸው” ብለዋል።

ቅጽ 2 ቁጥር 111 ታህሳስ 10 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here