ወመዘክር አቋርጦት የነበረውን አገልግሎት ታህሳስ 12 ይጀምራል

0
508

የብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መፅሐፍት ኤጀንሲ (ወመዘክር) በኮቪድ- 19 ምክንያት አቋርጦት የነበረውን አገልግሎት ከታህሳስ 12 /2013 ጀምሮ መስጠት እንደሚጀምር ገለጸ፡፡
ኤጀንሲው የኮቪድ-19 ፕሮቶኮል መመሪያን ጠብቆ ቤተ መፅሐፍቱን ለሕዝብ ክፍት ለማድረግ ዝግጅት ማጠናቀቁን ያስታወቀ ሲሆን ከታህሳስ 12 ቀን ጀምሮም የህጻናትና አካል ጉዳተኞች ቤተ መፅሐፍትን ሳይጨምር እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት አገልግሎት እንደሚሰጥ ገልጿል፡፡
መመሪያው ከኅብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩትና ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመሆን ከተቋሙ የሥራ ባህሪ ጋር በማናበብ እና በማቀናጀት የተዘጋጀ መሆኑም ተገልጿል፡፡
ወረርሽኙን ለመግታት እንዲያስችልም በፊት ያስተናግድ ከነበረው 1 ሺሕ 200 ተገልጋይ በመቀነስ 326 ተገልጋዮችን ብቻ እንደሚያስተናግድ ኤጀንሲው ገልጿል፡፡
የመፅሐፍት ውሰት እንደማይኖርና አንድ ተገልጋይ የተጠቀመበትን መጽሃፍ ከተጠቀመ በኋላ ከሦስት እስከ አምስት ቀናት ተለይቶ እንደሚቀመጥም ተነግሯል፡፡
በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው አገልግሎቱ መመሪያ በማዘጋጀትና የመመሪያውን አተገባበር ለአገልግሎት ሰጪ ሰራተኞቹ ስልጠና በመስጠት መፈተሹንም ኤጀንሲው አስታውቋል። ኤጀንሲው በተቋሙ ድረ-ገጽ ላይም ለተገልጋይ አብራሪ በሆነ መልኩ ተደራሽ ያደርጋልም ተብሏል።

ቅጽ 2 ቁጥር 111 ታህሳስ 10 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here