በአዲስ አበባ በደረሱ ሁለት የእሳት አደጋዎች ከ3.5 ሚሊየን ብር በላይ ንብረት ወደመ

0
655

በአዲስ አበባ የበዓል እለት የመጀመሪያው የእሳት አደጋ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው መሻለኪያ ቄስ ሰፈር ዛሬ ረፋድ ላይ መድረሱነን እና በደረሰው የእሳት አደጋ 3 ሚሊየን አምስት መቶ ሺ ብር የሚያወጣ ንብረት መውደሙን የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቃል።
የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከፌደራል ፓሊስ፣አዲስ አበባ ፓሊስ እና ከሕብረተሰቡ ጋር በመሆን እሳቱን መቆጣጠር የቻለ ሲሆን 30 ሚሊየን ብር የሚያወጣ ንብረት ከውድመት መታደግ መቻሉን በኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ አቶ ጉልላት ጌታነህ ተናግረዋል።
አደጋው በሱቆች እና በመኖሪያ ቤት ላይ ውድመት ያደረሰ ሲሆን መነሻ ምክንያቱ ግን በውል አልታወቀም።አደጋውን በቁጥጥር ስር ለማዋል 2 ሰዓት ከ15 ደቂቃ ወስዷል። 109 የእሳት አደጋ ሰራተኞች 24 ተሽከርካሪዎች እና 145 ሺ ሊትር ውሀ ጥቅም ላይ ውሏል።
ኹለተኛው የእሳት አደጋ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ቦታው 93 ቁጥር ማዞሪያ ነው።አደጋው የተነሳው በተለኮሰ ሻማ ምክንያት እንደሆነ ሲገለፅ 50ሺ ብር የሚያወጣ ንብረት ማውደሙን አቶ ጉልላት ጨምረው ተናግረዋል።
የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ባለሙያዎች ባደረጉት ርብርብ 2 ሚሊየን ብር የሚያወጣ ንብረት በእሳት እንዳይወድም ማድርግ ችለዋል ።በመቀሌ ከተማ አሽከርካሪዎች በነዳጅ እጥረት ምክንያት መንቀሳቀስ መቸገራቸውን አመለከቱ

ቅጽ 2 ቁጥር 114 ጥር 1 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here