ሕብረት ኢንሹራንስ ከፍተኛውን የካሳ ክፍያ ከፈለ

0
980

ሕብረት ኢንሹራንስ አክሲዮን ማኅበር በታሪኩ ከፍተኛ የተባለውን ካሳ ክፍያ መከፍሉን አስታወቀ።
ኢንሹራንሱ ለአዲስ ማለዳ በላከው መረጃ ጥበብ ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ ተወሰነ የግል ማኅበር ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ጋር በገባው የነሳንጃ ቀራቅር መንገድ ግንባታ ፕሮጄክት ውል መሰረት በጊዜው ባለመከናወኑ እንደሆነ ታውቋል።
ከዚህም ጋር ተያይዞ ሕብረረት ኢንሹራንስ ለኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የመልካም ስራ መስፈጸሚያ ዋስትና በሰጠው ውል መሰረት ታኅሳስ 27/2013 ከ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ ካሳ መክፈሉ ተረጋግጧል።
ሕብረት ኢንሹራንስ ከዚህ ቀደምም ለደንበኞቹ በገባው የቃልኪዳን ውል መሰረት ቀደም ሲልም ተመሳሳይ ካሳ ክፍያዎችን ሲከፍል ቆየ እንደነበር አስታውሶ በቀጣይም ደንበኞቹ ኩራት በመሆን እንደሚቀጥል ለአዲስ ማለዳ በላከው መልዕክት ጨምሮ ገልጿል።
የመንገድ ግንባታው የሚገኘው በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ጎንደር ዞን ሲሆን በቅርቡ ፌደራል መንግሥት ሕግ ማስከበር እርምጃዎችን በወሰደ ጊዜ ከፍተኛ ውጊያ የተካሔደባቸው ስፍራዎች መሆናቸውም አይዘነጋም።

ቅጽ 2 ቁጥር 114 ጥር 1 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here