አውታር ያመጣው ለውጥ?

0
1033

እጅግ ፈታኝ ከሚባሉ እና የሙዚቃው ኢንደስትሪ እንዳያድግ እንቅፋት ሆኗል – ስርቆት ። የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያመላክቱት ከሆነም 80 በመቶ የሚሆኑ የሙዚቃ ስራዎች በሕገወጥ ነጋዴዎች ይቸበቻበሉ። ታዲያ ይህንን ችግር ለመቅረፍ ጥቁት የሚባሉ አርቲስቶች ቴክኖሎጂን በመጠቀም እንዲሁም ኢንርኔትን በመጠቀም የሚሰራ መተግበሪያ (አፕሊኬሽን ) ለመስራት ያስባሉ። ሥራውም የተለያዩ አርቲስቶችን ያካተተ ነበር። ሃሳቡን ወደ ተግባር ለማስገባት ከተንቀሳቀሱ አርቲስቶች መካከል በሞት የተለየን የሙዚቃ ባለሙያ አልያስ መልካ ይጠቀሳል። ከኤልያስ በተጨማሪም ኃይሌ ሩትስ፣ዳዊት ንጉሱ እና ጆኒ ራጋ በጋራ በመሰባሰብ የሞባይል መተግበሪያ ለመስራት በመወሰን እና የተለያዩ ሙዚቃዎችን በማከማቸትም ማንኛውም ሠው ከመተግበሪያው ላይ ሙዚቃዎችን ዳውንሎድ በማድግ (በማውረድ) የሚሠራ መተግበሪያ መስራት ችለዋል። መተግበሪያውም የሙዚቃ ስርቆትን ለመከላከል እና ሙዚቃዎችን ለመሸጥ የሚያችል ፍቱን መፍትሔ ነው ተብሎለታል። የኢትዮጵያን ቢዝነስ ሪቪው (ኢቢአር) መጽሔት ዘጋቢ የነበረችው በረድኤት ገበዩሁ ቴክሎጂ የሙዚቃውን ኢንደስትሪ ምን ያህል እንደቀየረው ሊያሳይ የሚችለው የተጻፈውን ጽሑፍ ለአዲስ ማለዳ አንባቢያን በሚመጥን መልኩ በአዲስ ማለዳዋ እየሩስ ተስፋዬ እንደሚከተለው ተተርጉሞ ቀርቧል።

ካለፉት ዐሥርት ዓመታት ጀምሮ የኤሌክትሮኒክስ መተግበሪያዎች የመዝናኛውን ኢንዱስትሪ እየተቆጣጠሩት ከመጡ ሰነባብተዋል።
ነገሮችን በንጽጽር ያየን እንደሆነም በፈጠራ ሥራ ለተሰማሩ ሰዎች ቴክኖሎጂ ስራዎቻቸው እንዲሰረቅ በማጋለጥ በኩል ሚናው ቀላል የሚባል አይደለም። በሌላ በኩል ደግሞ ለአድማጭ ተመልካቾች የሚዝናኑበት አንድ አማራጭ ሆኗል። ከዚህ በተቃራኒው ደግሞ የሙዚቃው ኢንደስትሪ በሕገወጥ መንገድ እንዲዘዋወር አድርጎታል።ቴክኖሎጂው ከዕለት ዕለት እየተቀያየረ በመምጣቱም ድሮው የነበረው የሲዲ ሽያጭም አሁን ላይ አከተመለት በሚባል ደረጃ ላይ ደርሷል።

ተዋበች ማስተማል ትባላለች ሙዚቀኛ ናት። በ2011 ነበር የመጀመሪያዋን ነጠላ ዜማ መልቀቅ የቻለችው። የሙዚቃው ኢንደስትሪ ላይ ስላለው ነገር ስትናገርም እንዲህ በማለት ነበር ‹‹ቪዲዮ ሾፕ፣ ዩቱዩብ እና ጓደኞች የተለያዩ ሙዚቃችን እንዳገኝ ይረዱኛል።የእኔ ሙዚቃ ያለ ፈቃዴ በዩቱዩብ ላይ እስከሚለቀቀበት ጊዜ ድረስ አንድም ቀን የሙዚቀኞችን ጉዳት ምን እንደሆነ አስቤ አላውቅም።››ትላለች ቀጠል አድርጋም ‹‹አሁን ላይ ብዙ ነገሮችን መማር ችያለሁ። ሙዚቃ ለመስራት ብለው ብዙ ብር መድበው የሚሰሩ ሙዚቀኞችንምአደንቃለሁ። እንደውም አንዳንድ ሙዚቀኞች ቤታቸውን እስከመሸጥ ደርሰዋል። የሙዚቃ ሥራዎቻቸውም ሕጋዊ ባልሆነ መንግድ በመሰራጨታቸው ምክንያት ለኪሳራ ተዳርገዋል።›› በማለትም ትገልጻለች።

በመሆኑም ኢትዮጵያ ይህን ችግር ለመቅረፍ በ1996 የቅጂ እና ተዛማቾች አዋጅ አስተዋውቃለች። አዋጁንም በባለቤትነት የኢትዮጵያ አእመሯዊ ንብረት ጽሕፈት ቤት ያስተዳድረዋል።

አውታር መልቲ ሚዲያ የሙዚቃ ሥራዎችን ለገበያ የሚያቀርብ ነው እንዲሁም አዳዲስ ሙዚቃዎች ከሙዚቀኞች በመቀበል በኦን ላይን በመጫን የሚሠራ ነው። ማንኛውም አድማጭ የሆነ ሠው በእጅ ስልኩ አማካኝነት ኢንተርኔትን በመጠቀም ሙዚቃዎችን አውርዶ ለመስማትም ያስችለዋል። ዋጋውም አንድ ሙዚቃን አውርዶ ለመስማት ሦስት ብር ሲሆን አንድ አልበም ከሆነ ደግሞ 15 ብር ነው። መተግበሪው የወረደውን ሙዚቃ ለሌሎች ለማጋራት እና ኮፒ ራይትን መከላል የሚቻል እደሆነም ይመሰከርለታል።

በአውታር መተግበሪ ላይ ተጭነው ከሚለቀቁ ሙዚቃዎች ኢትዮ ቴሎኮም የ30 በመቶ የገቢ ድርሻ አለው። 54 በመቶ ድርሻው ደግሞ ለሙዚቃው ባለቤት ይውላል።ቀሪው ድርሻ ደግሞ ለአውታር አስተዳደራዊ ወጪ እንደሚውልም ለማወቅ ተችሏል።

ይህ ብዙ ተስፋ የተጣለበት መተግበሪያ በይፋ ወደ ስራ መግባቱን ተከትሎም ባለፉት አምስት ወራት ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሠዎች ሙዚቃዎችን ማውዳቸውም ይጠቀሳል። እስከ አሁን ድረስም ቁጥራቸው በዛ ያሉ ነጠላ ዜማዎች እና አልበሞችም ተለቀውበታል፡፡ ከነዚህ የሙዚቃ ሥራዎች ውስጥም በቅርቡ የወጣው የኃይሌ ሩስት ‹‹የታመነ ››የተሠኘው የሙዚቃ አልበሙም በመተግበሪያው ላይ መለለቀቅ ችሏል።

እዮብ መውደድ ይባላል (በራሱ ፍላጎት ስሙ የተቀየረ) እንደ ዮቱዩብ እና መሰል የመገናኛ አማራጭ ዘዴዎችን ወደ ጎን በመተው የሙዚቃ አልበሙ በአውታር መተግበሪያ ላይ እንሊቀቅ ካደረጉ ሙዚቀኞች መካከል አንዱ ነበር። የእርሱ የሙዚቃ ሥራዎች በአውታር መተግበሪያ ላይ ከተጫነ ከአምስት ወር በኋላም ነበር አምስት ሺህ ብር የተቀበለው። አሁን ግን የሙዚቃ አልበሙን በሌሎች የመገኛኛ ዘዴዎችን ለመልቀቅ ወስኗል።‹‹አውታር የእኔን ሙዚቃ ለአድማጮች በሚገባ አላደረሰልኝም።ከአምስት ወራት በኋላ ምንም የገኙት ለውጥ ባለመኖሩ የሙዚቃ አልበሜን በመገኛኛ ብዘሁን ላይ ለመልቀቅ ወስኛለሁ ምክንያቱም ሙዚቃዎቼ በብዙ ሠዎች እንዲደመጡ እና እዲደርሱ ስለምፈልግ ነው።በተጨማሪም ምንም ገቢም አያስገኝም›› በማለት እየብ ያለውን ሃሳብ አካፍሏል።

እዮብ እንደሚናገረው ከሆንም በአሁነ ወቅት ሙዚቃ መሥራት በጣም ከባድ እና በዋጋ ደረጃም ውድ እንደሆነ ይገልጸላ እንዲህ ሲል ‹‹አሁን ላይ አልበም ብቻ በመሸጥ ከዘራፊዎች ለመዳን አይቻልም። አልበም ከወጣ በኋላ በገቢ ደረጃ ለማገገም ብቸኛው አማራጭም የሙዚቃ ኮንርቶችን ማዘጋት ነው። ይሁን እንጂ አሁን ላይ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ይህን ማዘጋጀት አይቻልም።አውታር ላይ ተስፋ አድርጌ ነበር ግን በሙዚቃዬ በሚገባ መደመጥ አልቻለም።በሕጋዊ መንገድ የሚለቀቁ ሙዚቃዎች ገቢ እንኳን ባያመጡም የመደመጥን ዕድልን ግን ይጨምራሉ ።››

ከአማራጭ መገኛኛ ብዙሃን መካከል አንዱ የሆነው ዩቱዩብ ፤ሙዚቀኞች ስራዎችቸውን ብዙ ሠዎች ጋር እንዲደርስ ከሚያርጉት መካከል አንዱ እንደሆነ ይጠቀሳል። አሁን ላይ ሙዚቀኞችም ቢሆኑ በቀላሉ የራሳቸውን ዩቱዩብ ቻናል በመክፈትም የራሳቸውን ሙዚቃ በመልቀቀ ብዙ ሠዎች ጋር ድርሶ እና ተመለክተውት የራሳቸውን ገቢም እንዲያገኙ አስችሏቸዋል።

እዮብ አከሎ ሲናገርም የእርሱ ሙዚቃ በአውታር ላይ መጫኑ ብዙ ሰዎች ጋር እንዳይደርስ ካደረጉት መካከል ኹለት ምክንያተቹን ይጠቅሳል ‹‹ አስተማማኝ እና ፈጣን ኔትዎክ የለም።መተግበሪያውም ቢሆን አስተማማኝ አይለም። ሌላው ደግሞ የአውታር ባለቤቶች የማስተዋወቁን ሥራ በሚገባ ለመስራት ቃል የገቡልኝ ቢሆንም ይህንን ግን አላደረጉም።›› ሲል የጠበቀውና በተግባር የሆነው ነገር ስለመለያየቱ ያስረዳል።

የአውታርን መተግበሪያ ከመሰረት መካከከል አንዱ እንደሆ ይታወቃል።በቅርቡም የሙዚቃ አልበሙን በመተግበሪያው ላይ መልቀቅም ችላልሏ- ኃይሌሩትስ። ‹‹አውታር በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሕጋዊ የሙዚቃ መተግበሪያ ነው። እርግጥ መተግበሪው ላይ የተወሰኑ ክፍተቶች አሉ።በአሁን ወቅትም እሱን ለማስተካል እየሰራን እንገኛለን። ሌላው ክፍተታችን ደግሞ መተግበሪያውን ለማስተዋወቅ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ሥራዎችን አልተሠራም።›› ሲል ክፍተቶች ስለመኖራቸው ያስረዳል።

አውታርን ለመክፈት ብዙ ገንዘብ እንደሚጠይቅ የሚገልጸው ኃይሌሩትስ የተሻለ የሚባለውን መተግበሪያ ለመጠቀም የውጭ ምንዛሬ እጥረት አንዱ ፈተና መሆነን ይጠቅሳል።

ያሬድ አድማሴ ይባለል። የሙዚቀኛ ዳዊት ጽጌ ማናጀር ነው እርሱ ሲናገርም ‹‹ የአውታር መተግበሪያ ኮፒራይትን በመከላከል በኩል ጥሩ የሚባል ጥቅም አለው።በዚህም በጣም ጥሩ የሚባል ለውጥ በኢንዱስሪው ላይ ማምጣት ችሏል። መተግበሪያው አዲስ እንደመሆኑ መጠን በሚገባ ማስተዋወቅ ያስፈልጋል። የኢንተርኔት ግንኙነቱም እንደ አገር ተያይዞ በሚመጣው መሻሻል አብሮ የሚሻሸል ይሆናል›› ሲል ያለውን ተስፋ ይናገራል።

‹‹አውታር መተግበሪያ ይፋ በተደረገ አምስት ወራት ውስጥ 25 ነጠላ ዜማዎችን አውርጃለሁ።መተግበሪያው ስርቆጥን በመከካለል እና ሙዚቀኞችን ለመደገፍ ስለሚረዳ ይህንን ነገር አደንቃለሁ።›› ሲል የሚናገረው የሙዚቃ አፍቃሪ አሸናፊ ፀጋዬ ነው። አክሎም ይህንን ብሏል ‹‹ይሁን እንጂ መተግበሪያው መዚቃን በቀላሉ ለማውረድ እንዲያስቀችል ለሁሉም ሠው ቀላል መሆን አለበት።››

የኢትዮጵያ የሙዚቃ ዘርፎች ማሕበራት ኀብረት ፕሬዝዳት የሆኑት ዳዊት ይፍሩ በበኩላቸው ለኮፒ ራይት ትኩረት በመስጠት የሙዚቃውን ኢንዱስትሪ በድጋሚ የማዋቀር ሥር እንደሚሰራ ነው የገለጹት። የሙዚቃ አልበም ብዙም እየተሰራ አይደልም ብዙዎቹ አልበም ከምስራት ይልቅም ነጠላ ዜማዎችን እየሰሩ እንደሚገኙም የሙዚቃ አቀናባሪ፣ኪቦርዲስት እና የሮሃ ባንድ መስራች ዳዊት ይፍሩ ይገልጻሉ።

ማህበሩ ቁጥራቸው ወደ 2ሺህ200 ገዳማ የሚሆኑ አባለት ያሉት ሲሆን በአሁን ወቅትም የሮያሊቲ ክፍያ ለማስጨመር ሥራዎች መጠናቀቃቸውን እንዲሁም መገናኛ ብዙሃን ለሚያስደምጧቸው ሙዚቃ የሮያሊቲ ክፍያ እንዲፈፅሙ ሥርዓት እየተዘረጋ እንደሆነም ከአንጋፈው የሙዚቃ ባለሙያ ዳዊት ይፍሩ ለማወቅ ተችሏል።

ቅጽ 2 ቁጥር 116 ጥር 15 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here