የማይክሮሶፍት ካምፓኒ (Maicro soft 4afrika) በተሰኘ ፕሮግራም በአራት ዘርፎች ከባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲውት ጋር በጋራ በመሆን ስልጠናዎችን ሊሰጥ እነደሆነ የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲውት ለአዲስ ማለዳ አስታወቀ።
በአራት አይነት ዘርፎች (artificial intelligence ‚ cyber security ‚ cloud ‚ data since) በሚባሉ ስልጠናው እንደሚሰጥ ከባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲውቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻው በባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲውት መምህር ፣ የጎግል ዲቨሎፕ ቡድን የባህር ዳር ቻፕተር ሊድ ኦርጋናይዘር ፣ በማይክሮሶፍት ስኪል ላብ ቴክኒካል ሜንቶር ሙሉአዳም ተመስገን እንደተናገሩት ማይክሮሶፍት በአፍሪካ የተለያዩ አገራት ላይ እንደዚህ አይነት ስልጠናዎችን ይሰጣል ብለዋል።
በማይክሮሶፍት ያቋቋመው (Maicro soft 4afrika) የተሰኘ ፕሮግራም እንዳለና ይህም ፕሮግራም በተለያዩ የአፍሪካ አገሮች የቴክኒካል ስልጣና በመስጠት በቴክኒክ ብቁ የማድረግ እንዲሁም በገንዘብ ድጋፍ በማድረግ በቴክኖሎጂ ማብቃት ላይ የሚሰራ ተቋም እንደሆነ ተናግረዋል።
በዚህም ማይክሮሶፍት (Maicrosoft 4afrika) በሚለው ፕሮግራሙ ከባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲውት ጋር ስኪል ላብ በሚባል ፕሮግራም የብቃት ክፍተት ስልጠና ለመስጠት እንደታሰበ ተናግረዋል።
ስልጠናው የሚሰጠው በፍላጎት እንደሆነ እና ስልጠናውን ለመውሰድ ፍላጎት ያላቸው ሰዎች ሊወስዱት እንደሚችሉ ተናግረዋል የአሁኑ የመጀመሪያ ዙር ስለሆነ መሰረታዊ ፕሮግራሚንግ የሚችሉ ሰዎች እንደሚወስዱት ተናግረው በዚህም ፐሮግራሚንግ መቻል አለመቻላቸውን የሚመዝን ፈተና እንደሚዘጋጅም አክለው ተናግረዋል።
በዚህም ውድድሩ ጠንካራ ከሆነ ማወዳደሪያ ነጥብ ሊጨምር እንደሚችል ምክንያቱም መማር የሚፈልገው ሰው በርካታ ነው ብለዋል።
ማይክሮሶፍት ስልጠናውን የሚሰጠው በነፃ እንደሆነ ነግረውናል። ነገር ግን ሰዎች ስልጠናውን ሲወስዱ የተወሰነ ክፍያ መክፈል እንዳለባቸው እንደታሰበ ምክንያቱም ከፍተኛ ዋጋ ያለው ስልጠና ስለሆነ እንዲሁም የሚያገኙት ሰርተፍኬት አለም አቀፋዊ በመሆኑ ትኩረት ሰጥተው እንዲማሩት ያስችላል ተብሎ ስለታመነበት ክፍያ እንዲከፍሉ እንደሚደረግ ነግረውናል።
ስልጠናዎቹም ሦሥት ወራትን የሚቆይ ስድስት ወራትን የሚቆይ እያሉ እንደ አይነታቸው እንደሚለያዩ በአመትም 60 የሚሆን ሰልጣኞችን ብቻ እንደሚያሰለጥኑ ነግረውናል።
የሚሰጠው ስልጠና በቨርቿል እንደሆነ የተናገሩት ሙሉአዳም ከኹለት ወራት በኋላ ሙሉ ለሙሉ ስልጠናው ይጀመራል ተብሎ እንዳሰበ ነግረውናል በዚህም አሁን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በማከናወን ላይ መሆናቸውን አክለው ነግረውናል።
ሙሉ በሙሉ ስልጠና የሚሰጠው በማይክሮሶፍት ካምፓኒ መሆኑን አክለው ተናግረዋል።
የስልጠናው ዋና ግቡ ሰልጣኞችን ኢንደስትሪ ላይ እንዲሰሩ አድርጎ ተግባራዊ ክህሎት ማስያዝ ነው እሱን ከጨረሱ በኋላ ደግሞ ሰርተፍኬት የሚሰጥ ሲሆን የሚሰጠው ሰርተፍኬትም በፈተና እንደሆነ እና ፈተናውም አለም አቀፍ ደረጃ ያለው እንደሆነ ተናረዋል።
በዚህም ስልጠናው የሚሰጠው በአለም አቀፍ ነው። ሰርተፊኬቱም አለም አቀፍ ነው ስለዚህም ተወዳደሪ እንዲሁም በተግባር ንቁ የሆኑ እንዲሁም የራሳቸውን ስራ መፍጠር የሚችሉ ሰልጣኞች ይፈጠራሉ ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።
ማይክሮሶፍት ስልጠናውን ለመስጠት ኢትዮጵያ ውስጥ ከባህር ዳር ዩንቨርስቲ ጋር ሲስማማ ለመጀሚያ ጊዜ እንዳልሆነ እና ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያን አየር መንገዶች እና ገበያ ትሬኒንግ ሴንተር ጋር በጋራ እንደሚሰራ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
(Maicrosoft 4afrika) በአፍሪካ እንደ አውሮፒያን አቆጣጠር 2013 የጀመረ ሲሆን በዚህም የአፍሪካን ኢኮኖሚ ልማት ለማፋጠን ለቢዝነስ መጀመሪያ ፣ በአጋርነት ለሚሰሩ ፣ በትንንሽ መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ላይ በገንዘብ እንዲሁም ስልጠና መስጠት መጀመሩን አዲስ ማለዳ ካየቻቸው መረጃዎች ለማግኘት ችላለች።
ቅጽ 2 ቁጥር 116 ጥር 15 2013



