በ13 ከተሞች አዲስ የወባ በሽታ ተህዋስ አስተላላፊ ትንኝ መሰራጨቱ ተገለፀ

0
890

በኢትዮጵያ 13 ከተሞች አዲስ የወባ በሽታ ተህዋስ አስተላላፊ ትንኝ መሠራጨቱን አርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት አስታወቀ። ከዚህ ቀደም ከነበሩት ትንኞች የሚለየው ለመራባት የሚመርጠው አካባቢ ከተሞችን መሰረት ያደረገ መሆኑ ተገልጿል።
ኢንስትትዩቱ ባካሄደው የዳሰሳ ጥናት መሰረት አዲስ የወባ በሽታ ተህዋስ አስተላላፊ ትንኝ በሶማሌ፣ አፋር፣ አማራና ምሥራቅ ኦሮሚያ ክልሎች መስፋፋቱን አመላክቷል። አዲስ የወባ በሽታ ተህዋስ አስተላላፊ ትንኝ ከተሰራጨባቸው ከተሞች ሰመራ፣ ገዋኔ፣ አዋሽ፣ ኤረር፣ ጅግጅጋ፣ ቀብሪደሃር፣ ጎዴ፣ ደጋሃቦር፣ ደሬደዋና መታሃራ እንዲሁም ባቱ ፣ መቂ እና ሞጆ ተጠቅሰዋል።
የተጣሉ ጎማዎች፣ የፕላስቲክ ዕቃዎች፣ የተለያየ ስሪት ያላቸው የውሃ ማጠራቀሚያዎች ለመራባት የሚመርጣቸው ቦታዎች መሆናቸው በእስካሁኑ ጥናት ተደርሶበታል። አዲሱ የወባ በሽታ አስተላላፊ ትንኝ ዝርያ በኢትዮጵያ በ2008 የታየ ሲሆን ከዚያ ቀደም ባሉት ጊዚያት በምሥራቅ አረብ ፔንሱላ እና አፍሪካ ቀንድ አካባቢዎች ይታይ እንደነበር ነው የተገለጸው። በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ለመጀመሪያ ጊዜም በ2004 በጅቡቲ ተገኝቶ እንደነበር ተነግሯል።

ቅጽ 2 ቁጥር 118 ጥር 29 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here